መሠረታዊ የሆኑ የባሃኢ መርሆዎች
የባሃኢ እምነት ከአምላክ የተገለፀና ራሱን የቻለ ሐይማኖት ሲሆን ዓላማው ሁሉንም የሰው ዘሮችና ህዝቦች በአንድ ሁሉን አቀፍ የአምላክ እቅድና ሃይማኖት ለማዋሃድ ነው፡፡ ባሃኡላህ የባሃኢ እምነት መስራች ሲሆን ተከታዮችም ባሃኢዎች ይባላሉ፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
እ.ኤ.አ. በ 2019 በዓለም ዙሪያ ያሉ ሰዎች በ 1844 የሰው ልጅ ወደ አዲስ ዘመን እየገባ መሆኑን የገለፀው የእግዚአብሔር መልእክተኛ ባብ የተወለደበትን 200ኛ የልደት ክብረ በዓል አከበሩ ፡፡ ባብ ፍትህ እና ዘላቂ ሰላም ለመፍጠር ዓለም ሁሉ አንድ የሚያደርግበትን አዲስ ትምህርት ከእግዚአብሔር እንዲቀበሉ ሰዎችን ያዘጋጃቸው ነበር ፡፡
ባሃኢዎች መንፈሳዊና ማሕበራዊ ዕድገት ለማምጣት የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ያደርጋሉ። በዚህ መሠረትም የሁሉንም ሃይማኖት ተከታዮች የሚያሳትፉ የጋራ ፀሎተ-አምልኮ ጉባዔዎች፣ የሕፃናት፣ የታዳጊ ወጣቶች፤ የወጣቶችና የጎልማሶች የስነ-ምግባር ትምህርትና የጥናት ክፍለ-ጊዜዎችን ያካሂዳሉ።
የባሃኢ ሃይማኖት ወደ ኢትዮጵያ የገባው ሳብሪ ኤሊያስ በሚባሉ ግብፃዊ አማኝ አማካኝነት ነው። እኝህ ሰው በወጣትነታቸው እ.ኤ.አ 1933 ዓ.ም ያለምንም ቅድመ ዝግጅት ፣በውስን አቅማቸውና የኢትዮጰያን ቋንቋዎችን ባለማወቃቸው ሳይገቱ የባሃኢ ሃይማኖትን ለማስተማር ወደ ኢትዮጵያ መጡ።
ህዳር 28 ቀን 1921 እ.ኤ.አ. አብዱል-ባሃ በቅድስት ሀገር ከዚህ አለም አለፈ ። ህይወቱና ትሩፋቱ በዚህ መቶኛ አመት ዝክረ በዓሉ በመላው አለም ይታወሳል።ተጨማሪ ያንብቡ
© 2024 የኢትዮጵያ ባሃኢዎች