የባሃኢ እምነት ምንድን ነው?
"እናንተ ሁላችሁም የአንድ ዛፍ ፍሬዎች፥ የአንድ ቅርንጫፍ ቅጠሎች፥ የአንድ አትክልት ሥፍራ አበቦች ናችሁ።” ባሃኡላህ
የባሃኢ ሃይማኖት ከ 200 ሃገራት እና ግዛቶች በላይ ውደ 5 ሚልዮን በላይ ተከታዮች ያሉት ራሱን የቻለ ሀይማኖት ነው። የተመሰረተውም ለዚህ ዘመን የመጣው የእግዜአብሔር መልእክተኛ በሆነው በባሃኡላህ መንፈሳዊ እና ማህበራዊ እስተምህሮቶች ላይ ነው። በታሪክ እንደምንረዳው እግዜአብሔር ለሰው ልጆች ተከታታይ መለኮታዊ መምህራንን ልኳል። እነዚህ መምህራን የእግዜአብሔር ግልጸቶች በመባል ሲታውቁ የገለጹትም ትምህርት ለሰው ልጆች አዲስ አድገት እና ስልጣኔ መሰረት ነው። ከነዚህም መልእክትኞች መካከል አብርሃም፣ ክሪሽና፣ ዞራስተር፣ ሙሴ፣ ቡድሃ፣ እየሱስ ክርስቶስ እና ነቢዩ ሞሐመድ ይገኙበታል። ከነዚህ ተከታታይ ግልጸቶች በኋላ ለዚሀ ዘመን የተገለጸው ደግሞ ባሃኡላህ ነው። የባሃኡላህ አስተምህሮት እንደሚያስረዳው ሀይማኖቶች ከአንድ ምንጭ እንደመጡ እና በባህሪያቸውም የአንድ የእግዚአብሔር ሀይማኖት ተከታታይ ምእራፎች እንደሆኑ ነው። ወንዞች በውቅያኖሶች ውስጥ እንደሚዋሐዱ ሁሉ ከአሁን በፊት ለነበሩት ሃይማኖቶችም አዋሐጅ መሆኑን ደጋግሞ በግልጽ አስታውቋል።
በተላያዩ ሃይማኖቶች ቃል የተገባለት የአለም ሰላም በሚከተሉት መሰረታዊ አስተምህሮቶች ላይ መመስርት እንደሚኖርበት ባሃኡላህ ያስራዳል፡ እውነትን በቅንነት መፈለግ፤ የሰው ልጅ አንድነት፤ በምሥራቅም ሆነ በምዕራብ የሚገኙ ሃይማኖቶች፤ ዘሮችና ሕዝቦች አንድነት፤ የሃይማኖትና የሳይንስ መስማማት፤ የጥላቻና የከንቱ እምነት መደምሰስ፤ የሴቶችና የወንዶች እኩልነት፤ የፍትህና የጽድቅ መቋቋም፤ የጭፍን ጥላቻ እና የዘረኝነት መወገድ፣ ከልክ ያለፈ ድህነት እና ሀብት መወገድ፣ የመንፈሳዊ እና የቁሳዊ እድገት መስማማት፣ ማህበረሰብን የማገልገል ቁርጠኝነት አና ሌሎችም።
የባሃኢ እምነት መሰረታዊ አስተምህሮት አንድነት ነው። ይህም የአንድነት አስተምህሮት መሰረቱን ያደረገው አንድ እግዚአብሔር፡ አንድ የሰው ዘር፡ እና እንደየዘመኑ ፍላጎት የሰው ልጆች ላሉበት እድገት የሚገለጹ ተከታታይ ነገር ግን አንድ ሀይማኖት በሚለው ላይ ነው። አሁን ያለንበት ዘመን በዋነኝነት የሚፈልገው እያንዳንዱን ሰው ሊያሳትፍ የሚችል ፍትሀዊ፣ ሰላማዊ እና እያደገ የሚሄድ አለም አቀፋዊ ስልጣኔ ሊያስገነባ የሚያስችል የጋራ ራእይ ነው።
በሃኡላህ እንደሚያስርዳን “አግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥር ዓላማው፥ እስከ አሁንም ሆነ ለወደፊት፥ ፈጣሪውን ለማወቅና እፊቱም ለመቅረብ ለማስቻል ነው"። በተጨማሪም “ሟች ሰው ከፍጹም ምንምነት ወደ ኀልውና ግዛት አንዲሻገሩ የተደረገበት ዓላማ ለአለም መሻሻል እንዲሰሩና በስምምነትና በውህደት እንዲኖሩ ነው” በማለት ተናግሯል። ስለዚህ በአለም ዙሪያ ያሉ ባሃኢዎች ተመሳሳይ ራእይ ካላችው ሰዎች ጋር በመሆን መንፈሳዊ እና ማህበራዊ አስተምህሮቶችን በህይውታቸው ላይ እንዴት እንደሚተገብሩና ለሰው ልጆች እድገትም እንዴት እንደሚያውሉት በመማር ላይ ተጠምደዋል።
ስለ ሀይማኖቶች አንድነት ተጨማሪ ያንብቡ
Interesting blog? Like it on Facebook, +1 on Google, Tweet it or share this article on other bookmarking websites.