የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
  • የባሃኢ እምነት
    • የባሃኢ እምነት ምንድን ነው
    • የባሃኢ እምነት መነሻዎች
    • ባሃኡላህ
    • የባሃኢ እምነት አስተዳደር
    • የባሃኢ እምነት በኢትዮጵያ
  • ማህበረሰባዊ ተሳትፎ
    • ንቁ ማህበረሰብ መገንባት
      • የአምልኮ ሕይወት
      • የህፃናት ትምህርት
      • የታዳጊ ወጣቶች ፕሮግራም
      • የጥናት ክበባት
      • የወጣቶች እንቅስቃሴ
  • የባሃኢ አስተምህሮቶች
    • መርሆዎች
    • አምላክና ሐይማኖቶች
    • ህግጋቶችና ደንቦች
  • የባሃኢ መጽሐፍት
    • ቅዱሳን ጽሑፎች
    • ሌሎች
  • ለበለጠ መረጃ
    • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች
    • ቪዲዮዎች
  • ENGLISH

የባሃኢ እምነት ምንድን ነው

 "እናንተ ሁላችሁም የአንድ ዛፍ ፍሬዎች፥ የአንድ ቅርንጫፍ ቅጠሎች፥ የአንድ አትክልት ሥፍራ አበቦች ናችሁ።”  ባሃኡላህ

የባሃኢ ሃይማኖት የተመሰረተው  በባሃኡላህ መንፈሳዊ እና ማህበራዊ እስተምህሮቶች ላይ ነው። ባሃኡላህ ለዚህ ዘመን የመጣው የእግዜአብሔር መልእክተኛ እንደሆነ ባሃኢዎች ያምናሉ። በታሪክ እንደምንረዳው እግዜአብሔር ለሰው ልጆች ተከታታይ መለኮታዊ መምህራንን ልኳል። እነዚህ መምህራን የእግዜአብሔር ግልጸቶች ወይም የእግዜአብሔር መልእክተኞች በመባል ሲታውቁ የገለጹትም ትምህርት ለሰው ልጆች አዲስ አድገት እና ስልጣኔ መሰረት ነው። ከነዚህም መልእክትኞች መካከል፥ አብርሃም፣ ክሪሽና፣ ዞራስተር፣ ሙሴ፣ ቡድሃ፣ እየሱስ ክርስቶስ እና ነቢዩ ሞሐመድ ይገኙበታል። ከነዚህ ተከታታይ ግልጸቶች በኋላ ለዚሀ ዘመን የተገለጸው ደግሞ ባሃኡላህ ነው። 

የባሃኡላህ አስተምህሮት እንደሚያስረዳው ሀይማኖቶች ከአንድ ምንጭ እንደመጡ እና በባህሪያቸውም የአንድ የእግዚአብሔር ሀይማኖት ተከታታይ ምእራፎች እንደሆኑ ነው። ወንዞች በውቅያኖሶች ውስጥ እንደሚዋሐዱ ሁሉ ከአሁን በፊት ለነበሩት ሃይማኖቶችም አዋሐጅ መሆኑን ደጋግሞ በግልጽ አስታውቋል።

በተላያዩ ሃይማኖቶች ቃል የተገባለት የአለም ሰላም በሚከተሉት መሰረታዊ አስተምህሮቶች ላይ መመስርት እንደሚኖርበት ባሃኡላህ ያስራዳል፡ እውነትን በቅንነት መፈለግ፤ የሰው ልጅ አንድነት፤ በምሥራቅም ሆነ በምዕራብ የሚገኙ ሃይማኖቶች፤ ዘሮችና ሕዝቦች አንድነት፤ የሃይማኖትና የሳይንስ መስማማት፤ የጥላቻና የከንቱ እምነት መደምሰስ፤ የሴቶችና የወንዶች እኩልነት፤ የፍትህና የጽድቅ መቋቋም፤ የጭፍን ጥላቻ እና የዘረኝነት መወገድ፣  ከልክ ያለፈ ድህነት እና ሀብት መወገድ፣ የመንፈሳዊ እና የቁሳዊ እድገት መስማማት፣ ማህበረሰብን የማገልገል ቁርጠኝነት አና ሌሎችም። 

የባሃኢ እምነት መሰረታዊ አስተምህሮት አንድነት ነው። ይህም የአንድነት አስተምህሮት መሰረቱን ያደረገው  “አንድ እግዚአብሔር”፡ “አንድ የሰው ዘር”፡ እና እንደየዘመኑ ፍላጎት የሰው ልጆች ላሉበት የእድገት ደረጃ የሚገለጹ ተከታታይ ነገር ግን “አንድ ሀይማኖት” በሚለው ላይ ነው። አሁን ያለንበት ዘመን በዋነኝነት የሚፈልገው እያንዳንዱን ሰው ሊያሳትፍ የሚችል ፍትሀዊ፣ ሰላማዊ እና እያደገ የሚሄድ አለም አቀፋዊ ስልጣኔ ሊያስገነባ የሚያስችል የጋራ ራእይ ነው። 

በሃኡላህ እንደሚያስርዳን “አግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥር ዓላማው፥ እስከ አሁንም ሆነ ለወደፊት፥ ፈጣሪውን ለማወቅና እፊቱም ለመቅረብ ለማስቻል ነው"። በተጨማሪም “ሟች ሰው ከፍጹም ምንምነት ወደ ኀልውና ግዛት አንዲሻገሩ የተደረገበት ዓላማ ለአለም መሻሻል እንዲሰሩና በስምምነትና በውህደት እንዲኖሩ ነው” በማለት ተናግሯል። ስለዚህ በአለም ዙሪያ ያሉ ባሃኢዎች  ተመሳሳይ ራእይ ካላችው ሰዎች ጋር በመሆን መንፈሳዊ እና ማህበራዊ አስተምህሮቶችን በህይውታቸው ላይ እንዴት እንደሚተገብሩና ለሰው ልጆች እድገትም እንዴት እንደሚያውሉት በመማር ላይ ተጠምደዋል።

Interesting blog? Like it on Facebook, +1 on Google, Tweet it or share this article on other bookmarking websites.

  • Follow via Facebook
  • Follow via Youtube

አለም አንድ ሀገር ናት

እርሱ አገሩን ስለወደደ መኩራራት የለበትም፥ ይልቁንም መላውን አለም እንጂ።  ምድር አንድ አገር ናት የሰው ልጆችም ዜጎቿ ናቸው።

ባሃኡላህ

የሰው ዘር አንድነት

እናንተ ሁላችሁም የአንድ ዛፍ ፍሬዎች፥ የአንድ ቅርንጫፍ ቅጠሎች፥ የአንድ አትክልት ሥፍራ አበቦች ናችሁ።

ባሃኡላህ

© 2025 የኢትዮጵያ ባሃኢዎች

Go Top