የባሃኢ አስተዳደር ስርዓት በመመካከር ላይ የተመሰረተ ነው፡፡
“ማንም ምዕመን ከመንፈሳዊ ጉባኤው ጋር ሳይወያይ ምንም ዓይነት የባሃኢሥራ ሊሠራ አይፈቀድለትም። ማንኛቸውም ነገር ሥርዓትን የያዘና የተደራጀ ይሆን ዘንድ ምዕመናኑ በልብና በመንፈስ የጉባኤውን ውሳኔ አለአንዳች ቅሬታ መቀበል አለባቸው። ይህ ካልሆነ ግን እያንዳንዱ ሰው በግሉ በመሄድ የራሱን አስተያየትና ምኞት ስለሚከተል ለሃይማኖቱ ጉዳትን ያስከትላል።
“ለሚመካከሩ ሁሉ መሠረታዊና አስፈላጊ ነገሮች የሃሳብ ቀናነት፥ የመንፈስ ንጽሕና፥ ከሁሉም የግል ፍላጎቶች ርቆ የእግዚአብሕርን ብቻ መከተል፥ በመለኮታዊ ማዓዛው መማረክ፥ በምዕመናኑም መካከል ትሕትናና ዝቅተኝነትን ማሳየትና እግዚአብሔርን በማገልገል ላይ በሚደርሰው ረጅም ሥቃይና ችግር መታገስ ናቸው። የእግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ እነዚህን ጸጋዎች ከታደሉ ከማይታየው የባሃ መንግሥት አሸናፊነት ለእነርሱ ይወርድላቸዋል። በዚህ ዘመን የጉባኤዎች መመካከር አንገብጋቢና እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። ለእነርሱም መታዘዝ አስፈላጊና ግዴታም ነው። አባሎቹ አንዳች ቅሬታና አለመግባባት በማይፈጠርበት መንገድ መነጋገርና መወያየት አለባቸው። ይህም የሚሆነው እያንዳንዱ አባል ሃሳቡን በሙሉ ነፃነት አቅርቦ ምክንያቶቹን በግልጽ ሲደረድር ነው። ማንም ሰው ሃሳቡን ቢቃወም ጉዳዩን አጣርተው እስከተወያዩበት ድረስ እውነተኛው መንገድ ስለማይገለጥ መቀየም የለበትም። የእውነት ብልጭታ የሚታየው ልዩ ልዩ ሃሳቦች ከተጋጩ በኋላ ነው። ከውይይቱ በኋላ አንድ ሃሳብ በሁሉም ከተደገፈ መልካም ነው፤ ግን የእግዚአብሔር ፈቃድ ባይሆንና ልዩነት ቢፈጠር የድምፅ ብልጫ ያገኘው ሃሳብ መጽደቅ አለበት። ...
“የመጀመሪያው ሁኔታ በጉባኤው አባሎች መካከል ፍጹም ፍቅርና ስምምነት መፍጠር ነው። የአንድ ባሕር ውሃ፥ የአንድ ወንዝ ፏፏቴዎች የአንድ ሰማይ ከዋክብት፥ የአንድ ፀሀይ ብርሃን፥ የአንድ ቦታ ዛፎች የአንድ ተክል ሥፍራ አበቦች በመሆናቸው የልዩነትን መንፈስ ማስወገድና የእግዚአብሔርን አንድነት ማሳየት አለባቸው። ፍጹም አንድነትና ስምምነት ከሌለ ያ ስብሰባ መበተን፥ ጉባኤውም እንደሌለ መቆጠር አለበት። “ሁለተኛው ሁኔታ ወደ ስብሰባው በሚመጡበት ጊዜ ፊታቸውን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መመለስና ከእግዚአብሔርም ዕርዳታን መጠየቅ አለባቸው። ... ውይይቱ ነፍስ የምትዳብርበት፥ ሕፃናት የሚማሩበት፤ የድሆች ችግር የሚቃለልበት፤ በዓለም ያሉ በማንኛቸውም ክፍል የሚገኙ ድኩማን የሚረዱበት፤ ለሰው ሁሉ ችሮታ የሚደረግበት፤ የእግዚአብሔር መዓዛ የሚሰራጭበትና ቅዱስ ቃሉ የሚስፋፋበትን የመሳሰሉ መንፈሳዊ ጉዳዮችን የሚመለከት መሆን አለበት። እነዚህን ሁኔታዎች ለማሟላት ከቻሉ የመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ይወርድላቸውና ጉባኤው የመለኮታዊ ቡራኬ ማዕድ ይሆናል። የሰማይ መላእክት ለእርዳታ ይደርሱላቸዋል። በየዕለቱም በአዲስ መንፈስ ይሞላሉ።”
Interesting blog? Like it on Facebook, +1 on Google, Tweet it or share this article on other bookmarking websites.