ኢንተር ካለሪ ዴይስ (ጷጉሜ) ከተባሉ የልገሳ ቀናት የሚለጥቀው አሥራ ዘጠነኛው ወር የጾም ጊዜ ነው። በዚህ ወቅት ከጀንበር መውጣት እስከ ጀምበር መጥለቅ ከምግብ በመከልከል ለአሥራ ዘጠኝ ቀናት ይጾማል። ጾሙ የሚያልቀው በመጋቢት ኤኳኖክስ ስለሆነ ሁልጊዜ በዚያው ወር ይውላል። ይህም ማለት በሰሜን አገሮች በጸደይ፥ በደቡብ አገሮች ደግሞ በበልግ ስለሚሆን ችግርን ሊያስከትል በሚችለው በኃይለኛው የበጋ ወራት ወቅት ወይንም በኃይለኛው የክረምት ወቅዝቃዜ ወራት አይውልም ማለት ነው። በዚያን ቀን ሰው ሊኖርበት በሚችለው የዓለም ክፍል ቀንና ሌሊቱ እኩል ይሆናል። ይኸውም ከጠዋቱ አሥራ ሁለት ሰዓት ገደማ ጀምሮ እስከ ምሽቱ አሥራ ሁለት ሰዓት ድረስ ማለት ነው።
ሕፃናት፥ በሽተኞች፥ መንገደኞች፥ በጣም ደካሞች የሆኑ ሽማግሌዎች እንዲሁም ነፍሰጡሮችና የሚያጠቡ ሴቶች ላይጾሙ ይችላሉ።
በባሃኢ ትምህርት የተሰጠውን የሚመስል አልፎ አልፎ የሚደረግ ጾም ለሥጋዊ ጤንነታችን ጠቃሚ ለመሆኑ በቂ መረጃ አለ። የባሃኢ ጾም ሥጋዊ ምግብን ብቻ የሚመለከት ሳይሆን መንፈሳዊ ምግብ የሆነውን እግዚአብሔርን የምናስታውስበት ጊዜ በመሆኑ፥ ጾም ሥጋዊ ሰውነትን የሚያጠራ መሆኑን ብናውቅም፥ እግዚአብሔርን ከማስታወስ ሌላ ከሥጋዊ ምኞትና ፍላጎት መጠበቅ ይገባናል።
አብዱል-ባሃ እንዲህ ይላል፦
“ጾም ምሳሌ ነው። ጾም ከሥጋዊ ፍላጎት የመጠበቅ ምልክት ነው። ሥጋዊ ጾም የዚያ ምሳሌና አስታዋሽ ነው። ይህም ማለት ሰው ከምግብ ፍላጎት እንደሚከለከል ሁሉ ከግላዊ ምኞትና ፍላጎትም መጠበቅ ይገባዋል ማለት ነው። ይሁን እንጂ ከምግብ መከልከል ብቻ ለመንፈስ ዋጋ አይሰጥም። ምልክትና ማሳሰቢያ ብቻ ነው። ያለበለዚያ ምንም ዋጋ የለውም። ስለዚህ ጾም ማለት ጨርሶ ከምግብ መከልከል ማለት አይደለም። ለምግብ አወሳሰድ ወርቃዊው ሕግ በመጠኑ መብላት ነው። በልክ መሆን አስፈላጊ ነው። በሕንድ አገር ከምግብ ለመከልከል ሙከራ በማድረግ ጨርሶ ለመተው ጥቂት እስኪቀራቸው፥ ቀስ በቀስ ምግባቸውን የሚቀንሱ ክፍሎች አሉ። ይሁን እንጂ አእምሮአቸው ይሰቃያል። ሰው በምግብ ማነስ ከተሰቃየ በአእምሮም ሆነ በአካል ለእግዚአብሔር ሊያገለግል አይችልም። በግልጽ ለማየትም አይችልም።” (ፎርት ናይትሊ ሪቪዩ ሚስ ኢ. ስቲፈንስ። እ.ኤ.አ. ሰኔ 1911)
Interesting blog? Like it on Facebook, +1 on Google, Tweet it or share this article on other bookmarking websites.