የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
  • የባሃኢ ትምህርቶች
    • አምላክና ሐይማኖቶች
    • የአምላክ መልእክተኞች
    • የባሃኢ ትምህርቶች
    • ህግጋቶችና ደንቦች
    • አስተዳደር
  • ማህበረሰባዊ ተሳትፎ
    • ማህበረሰብ ግንባታ
    • የወጣቶች እንቅስቃሴ
  • የባሃኢ ማህበረሰብ
    • የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
    • የአለም ዓቀፍ ማህበረሰብ
    • የባሃኢ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ - አዲስ አበባ ጽ / ቤት
    • ባሃኢዎችን እናስተዋውቃችሁ
  • የባሃኢ መጽሐፍት
    • ቅዱሳን ጽሑፎች
    • ሌሎች
  • ለበለጠ መረጃ
    • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች
    • መልእክት ይላኩልን
    • ቪዲዮዎች
  • ENGLISH

በዓላትን ማክበር

የባሃኢ ሃይማኖት መሠረታዊ ደስታ የሚገለጸው በዓመቱ ውስጥ በሚከበሩ በርከት ባሉ ዓውደ ዓመታትና ክብረ በዓላት ነው።

አብዱል-ባሃ እ.ኤ.አ.በ1912 ዓ.ም. በእስክንድሪያ ግብፅ ውስጥ በናውሩዝ ክብረ በዓል ዕለት ባደረገው ንግግር እንዲህ ብሏል፦
“ቅዱስ በሆኑት በእግዚአብሔር ሕጎች ውስጥ በእያንዳንዱ ዑደትና ግልጸት የእረፍት ዓመታት በዓላት ቀናት አሉ። በእነዚህ በዓላት ሁሉም የንግድ፥ የኢንዱስትሪ፥ ግብርናና የመሳሰሉ ሥራዎች መቆም አለባቸው።


“ሰዎች ፊት የብሔራዊ አንድነት፥ ስምምነትና ፍቅር ይገለጽ ዘንድ ሁሉም በአንድ ላይ መደሰት፥ ጠቅላላ ስብሰባዎችን ማድረግ፥ እንደ አንድ ጉባኤ መሆን አለባቸው።


“የተቀደሰ ቀን እንደመሆኑ መጠን የፍጹም ፈንጠዝያ ቀን ብቻ በማድረግና ችላ በማለት ሊያስገኝ የሚገባውን ውጤት ማስቀረት የለበትም።
“በእንደዚህ ያሉ ዕለታት ለሰው ልጅ ዘላቂ ጥቅምና ዋጋ የሚያስገኝ ተቋማት መቋቋም ይኖርባቸዋል።


“በአሁኑ ጊዜ ሰውን በትክክለኛው መንገድ ከመምራት የበለጠ ፍሬ ያለው ወይንም ውጤት የሚያስገኝ ተግባር የለም። በእንዲህ ያለው ጊዜ የእግዚአብሔር ወዳጆች ለባሃኢዎች ብቻ ሳይሆን ለሰው ልጆች በሙሉ የሚጠቅም የተጨበጠ ትሩፋት ለትውልድ መተው ይገባቸዋል። በዚህ በድንቅ ግልጸት የበጎ አድራጎት ሥራ የእግዚአብሔር ቸርነት መግለጫ በመሆኑ ማንንም ሳይለይ ሰዎች ሁሉ ሊፈጽሙት የሚገባ ተግባር ነው። ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው ለሌላው እንደ እግዚአብሔር ምህረት እንዲሆነው እምነቴ ነው።”


የናውሩዝ (አዲስ ዓመት) የሪዝቫን፥ የባሃኦላህ ልደት፥ እንዲሁም ባብ መልእክቱን ያወጀበት (የአብዱል-ባሃ ልደት) ዓመት በዓላት በባሃኢዎች ዘንድ ታላቅ የደስታ ቀናት ናቸው።  እነዚህ በዓላት በክብረ በዓሉ ላይ በሚገኙት ምዕመናን አዘጋጅነት በመዝሙር፥ ከባሃኢ ጽሑፎች ልዩ ልዩ ንባብ በማንበብ፥ በሽርሽርና በፈንጠዝያ እንዲሁም ለእለቱ ተስማሚ የሆኑ አጫጭር መግለጫዎችን በማቅረብ ይከበራሉ። በአሥራ ስምንተኛውና በአሥራ ዘጠነኛው ወሮች መካካል ያሉት ትርፍ ቀናት (ከየካቲት ሃያ ስድስት እስከ መጋቢት አንድ) ወዳጆችን ለማስተናገድ፥ ስጦታዎችን ለማበርከት፥ ድሆችን ለመመጽወትና ሕሙማንን ለመጎብኘት የተመደቡ ቀናት ናቸው።


ባብ የተሰዋበት፥ ባሃኦላህና አብዱል-ባሃ ከዚህ ዓለም የተለዩበት ዕለታት በተገቢ ስብሰባዎችና ሥነ ሥርዓቶች፥ ጸሎቶችንና መልእክቶችን በማንበብ በጸጥታ ይከበራሉ።

Interesting blog? Like it on Facebook, +1 on Google, Tweet it or share this article on other bookmarking websites.

ህግጋት

  • ሥራ ስግደት ነው
  • በዓላትን ማክበር
  • ባሃኢ ምንድን ነው?
  • አልኮልና አደንዛዥ ዕፆች መከልከል
  • ጋብቻ
  • ፀሎት
  • ፆም
  • Follow via Facebook
  • Follow via Youtube
unity

© 2023 የኢትዮጵያ ባሃኢዎች

Go Top