የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
  • የባሃኢ ትምህርቶች
    • አምላክና ሐይማኖቶች
    • የአምላክ መልእክተኞች
    • የባሃኢ ትምህርቶች
    • ህግጋቶችና ደንቦች
    • አስተዳደር
  • ማህበረሰባዊ ተሳትፎ
    • ማህበረሰብ ግንባታ
    • የወጣቶች እንቅስቃሴ
  • የባሃኢ ማህበረሰብ
    • የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
    • የአለም ዓቀፍ ማህበረሰብ
    • የባሃኢ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ - አዲስ አበባ ጽ / ቤት
    • ባሃኢዎችን እናስተዋውቃችሁ
  • የባሃኢ መጽሐፍት
    • ቅዱሳን ጽሑፎች
    • ሌሎች
  • ለበለጠ መረጃ
    • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች
    • መልእክት ይላኩልን
    • ቪዲዮዎች
  • ENGLISH

ፀሎት

አብዱል-ብሃ፦ “ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ነው” ይላል። እግዚአብሔር፥ ሰዎች ሃሳቡና ፈቃዱ ይገባቸው ዘንድ፥ እነርሱ በሚገባቸው ቋንቋ ይናገራል። ይህንንም በቅዱሳን ነቢያት አንደበት ያሰማል። እነዚህም ነቢያት በሕይወታቸው ሳሉ በሰዎች መካከል ተገኘተው በቀጥታ የእግዚአብሔርን መልእክት ለሰዎች ያስተላልፋሉ። ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ በኋላ ትምህርታቸው በጽሑፍ ተቀርጾ ለሰው ልጆች ያለማቋረጥ ይተላለፋል። ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ከሰዎች ጋር የሚነጋግርበት መንገድ ይህ ብቻ አይደለም። እግዚአብሔር በየትም ቦታ ዘርንና ቋንቋን ሳይለይ ልበ-ንጹሐን እውነት ፈላጊዎችን የሚያነጋግርበት ጽሕፈትና ንግግር የማይሻ የመንፈስ ቋንቋ አለ። በዚህም ቋንቋ ማንኛውም ክስተት ከምድራዊው ዓለም ከተለየ በኋላ ከምዕመናኑ ጋር ግንኙነቱን ይቀጥላል። ክርስቶስ ከስቅለቱ በኋላ ደቀ መዛሙርቱን እያነጋገረ የመንፈስ ብርታት ይሰጣቸው ነበር። እንዲያውም በሥጋዊ ሕይወት ከነበረበት ጊዜ ይልቅ በይበልጥ እምነታቸውን አጠበቀው። በሌሎቹም ነቢያት ዘንድ ይህን መሰል ሁኔታ ተፈጽሟል።

 አብዱል-ባሃ ብዙውን ጊዜ ስለዚህ መንፈሳዊ ቋንቋ ሲናገር እንዲህ ሲል ጽፎአል፦
“መንግሥተ-ሰማያዊ ቋንቋ በሆነው መንፈሳዊ ቋንቋ መነጋገር ይገባናል። የልብና የመንፈስ ቋንቋ አለና። የኛ ቋንቋ በጩኸትና በልዩ ልዩ ድምጽ ከሚነጋገሩት ከእንስሣት ቋንቋ የሚለየውን ያህል፥ እንደዚሁም መንፈሳዊ ቋንቋ ከኛ ቋንቋ የተለየ ነው። ከእግዚአብሔር ጋር የሚነጋገረው መንፈሳዊ ቋንቋ ነው።
“በምንጸልይበት ጊዜ ከማንኛውም ዓለማዊ ነገር ርቀን ሃሳባችንን ወደ እግዚአብሔር ስናቀና በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔርን ድምጽ በልባችን እንደምንሰማ ይሰማናል። ያለቃላት እንነጋገራለን፥ በሐሳብ እንገንኛለን፥ በማነጋገርም ከእግዚአብሔ መልሱን እናገኛለን።…

“ሁላችንም ወደ እውነተኛው መፈሳዊ ደረጃ ስንደርስ የእግዚአብሄርን ድምጽ ለመስማት እንችላለን።” (ሚስ ኤቴል ጂ. ሮስንበርግ ካቀረቡት ንግግር)
ከከፍተኛው የመንፈሳዊ እውነት ጋር ለመነጋገር የሚቻለው በዚሁ ቋንቋ ብቻ መሆኑን ባሃኦላህ አስረድቷል። ለጽሑፍ ወይንም ለንግር የምንጠቀምባቸው ቃላት በቂ አይሆኑም። ባሃኦላህ “ዘ ሰቨን ቫሊስ” በምትባለው ትንሽ መጽሐፉ ከምድራዊ ኑሮ ወደ መንፈሳዊ ቤታቸው ስለሚሔዱ መንገደኞች ከፍተኛ የጉዞ ደረጃ ሁኔታ ሲናገር እንደሚከተለው ጽፎአል።

“አንደበት ይህን ሁኔታ ለመግለጽ ችሎታ ይሳነዋል፥ ቃላትም እጅግ በጣም ያጥራሉ፥ በዚህም ደረጃ ብዕር ጠቃሚ አይሆንም፥ ቀለምም ከማጥቆር በስተቀር ውጤት አያስገኝም። ... ይህ በቃላት ሊጠቃላል የማይችል ወይም የመልእክተኛ ሥራ ያልሆነ፥ ልብ ብቻ ከልብ በማነጋገር ሊገለጽ የሚቻል የመንፈሳዊነት ሁኔታ ነው።

የአምልኮት ሁኔታ

 ከእግዚአብሔር ጋር ለመነጋገር የሚያበቃንን መንፈሳዊ ደረጃ ለመደረስ እንችል ዘንድ አብዱል-ባሃ እንደዚህ ይላል፦
“ከዓለማዊ ሰዎችና ከዓለማዊ ነገሮች እየራቅን የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ብቻ በማክበር መንፈሳዊ ደረጃ ለመድረስ መጣር አለብን። ከዚህ ደረጃ ለመድረስ ጥረት ይጠይቃል። ቢሆንም ሰዎች ከዚህ ግብ ለመድረስ መሥራትና መድከም ይኖርባቸውል። ለዓለማዊ ነገር ያለንን ፍላጎት በመጠኑ አድርገን ለመንፈሳዊ ነገር በበለጠ ብንደክም ልንደርስበት እንችላለን። ከአንደኛው መራቅ ወደ ሌላው መቅረብ ነው። ሆኖም ምርጫው የኛው ነው። የእግዚአብሔርን መንፈስ ምልክት በፍጡራን ላይ ለማየት እንድንችል፥ ውስጣዊ ዓይናችንን መክፈትና መንፈሳዊ ስሜት እንዲኖረን ይገባል። ፍጥረት ሁሉ መንፈሳዊ ብርሃንን ሊያሳየን ይችላል።” (ሚስ ኤስል ጄ ሮዘንበርግ ከአቀረቡት ዘገባ)

ባሃኦላህ እንዲህ ሲል ጽፎአል፦

“ያ እውነት ፈላጊ ... በየዕለቱ ጎሕ ሲቀድ ... ከእግዚአብሔር ጋር በጸሎት መነጋገር ይገባዋል። በሙሉ ልቡም ተውዳንጁን ለመግኘት ሳይታክት መጣር ያስፈልገዋል፥ ክፉ ሐሳቡንም የተወዳጁን ስም በመጥራት በሚገኘው የፍቅር እሳት ማቃጠል ይገባዋል።” (ግሊኒንግስ ገጽ 285)
አብዱል-ባሃም በተመሳሳይ ሁኔታ እንዲህ ይላል፦

“ሰው፡ በነፍሱ አማካይነት፡ ግንዛቤውን መንፈስ እንዲያብራራለት ሲፈቅድ ፍጥረትን ሁሉ በውስጡ ይከስታል/ ይይዛል። ነገር ግን በሌላ በኩል ደግሞ ሃሳቡንና ልቡን ከመንፈስ ቅዱስ ቡራኬ በማራቅ ዝንባሌውን ሁሉ ወደ ዓለማዊ ነገር ካደረገ ከከፍተኛ ደረጃው ወርዶ ከእንስሳት ሁሉ ያነሰ ይሆናል።” (ዊዝደም ኦፍ አብዱል-ባሃ)
ባሃኦላህ በተጨማሪ ሲጽፍ፦

“ሰዎች ሆይ! ራስን ከመውደድ እስረኝነት እራሳችሁን ነፃ አውጡ፤ ነፍሶቻችሁንም ከኔ በስተቀር ከማንኛውም ነገር ሁሉ ቁራኝነት አንጿቸው፥ የምትረዱስ ከሆነ እኔን ማስታወስ ሁሉንም ነገሮች ከርኩሰት ያነፃዋልና። …

“... አገልጋይ ሆይ! የዝማሬህ ጣዕም ነፍስህን ያረካና የሰዎችንም ልብ ይማርክ ዘንድ ከአምላክ የተቀበልካቸውን ጥቅሶች አዚማቸው። ማንም በመንፈስ ቅዱስ የተገለጹትን ጥቅሶች በመድገም በብቸኝነት ቢዘምር የሰማይ መላእክት ይህንኑ ከአንደበቱ የሚፈልቁትን የቃላት ማዓዛ በማስተጋባት ያሰራጩታል።” (ግሊኒንግስ ገጽ 294-295)

 

የአገናኝ አስፈላጊነት

አብዱል-ባሃ እንደሚያስረደው፦
“በሰውና በፈጣሪው መካከል አገናኝ አስፈላጊ ነው። ምድር የፀሐይን ጮራ ሙቀት ተቀብላ እንደምታሠራጨው ሁሉ እርሱም እንዲሁ የእግዚአብሔርን ሙሉ የጸጋ ብርሃን ተቀብሎ ለምድራዊ ዓለም የሚያሰራጭ ነው።” (ዲቭይን ፊሎሶፊ ገጽ 8)

“ለመጸለይ ስንሻ ሃሣባችንን የምንሰበስብበት ዓላማ እንዲኖረን ያስፈልጋል። ወደ እግዚአብሔር ፊታችንን ስንመልስ ልባችን ወደ ተወሰነ ማዕከል እንዲያመራ ማድረግ አለብን። ሰው በነቢያት አማካይነት ሳይሆን በሌላ መንገድ እግዚአብሔርን ማምለክ ቢሻ አስቀድሞ ስለአምላክ ያለውን ጽንሰ ሃሳብ በአዕምሮው መቅረጽ ይኖርበታል። ይሁን እንጂ ይህ በሰውዬው አእምሮ የተፈጠረ ነው። ውስን ፥ ወሰን አልባውን ሊገነዘበው እንደማይችል ሁሉ፥ እግዚአብሔርንም በዚህ ሁኔታ ልንገነዘበው አንችልም። ሰው በአእምሮው ያነጸውን ለመረዳት አያዳግተውም። ይህ ስሜታዊ ጽንሰ ሃሳብ ግን እግዚአብሔር አይደለም። ሰው በሃሳቡ እግዚአብሔርን በማስመሰል የሚፈጥረው ስዕላዊ ቅርጽ እግዚአብሔር ሳይሆን አምሣልና የሐሳብ ቅዠት ነው። ስሜታዊ ጽንሰ ሃሳብ ከኃያሉ አምላክ ጋር ግንኙነት የለውም።

“ሰው እግዚአብሔርን ለማወቅ ቢፈልግ በፍጹም መስታወት በሚመሰሉት በክርስቶስ፤ በባሃኦላህና እንዲሁም እነርሱን በሚመስሉት በኩል ሊያውቅ ይገባል። በነዚህ መስተዋቶች መለኮታዊ ፀሐይ ሲያንጸባርቅ ይታየዋል።

“ፀሐይን በድምቀቹ፥ በብርሃኗና በሙቀቷ እንደምንለየው ሁሉ፥ መንፈሳዊ ፀሕይ የሆነውን አምላክንም ለማወቅ የምንችለው በፍጹምነት፥ በባህርያቱ ውበትና በብርሃኑ ግርማ ከክስተቱ መቅደስ ሲያበራ ነው።” (ውድ ኮክ በአካ 1እ.ኤ.አ. 909 ዓ.ም. )

እንደገናም እንዲህ ይላል፦

“ያለ መንፈስ ቅዱስ አገናኝነት ሰው የእግዚአብሔርን ጸጋ በቀጥታ ሊያገኝ አይችልም። ልናስታውሰው የሚገባንን ግልጽ ማስረጃ ብንወስድ፡ ሕፃን ያለአስተማሪ ዕውቀትን ለማግኘት አይችልም፥ ዕውቀትም ከእግዚአብሔር በረከት አንዱ ነው። ደመና ዝናብን ባያመጣ ምድር በዕፅዋት ባልተሸፈነች ነገር፡፤ ስለዚህም ደመናው የእግዚአብሔርን ጸጋ ወደ ምድር ያመጣ አገናኝ ማለት ነው። ብርሃን የሚፈልቅበት ምንጭ አለው፥ ይህንንም ብርሃን የሚሻ ከምንጩ እንጂ ከሌላ ሥፍራ ለማግኘት ፈጽሞ አይችልም... ወደ ክርስቶስ ዘመን መለስ ብላችሁ ብታስተውሉ፥ ጥቂት ሰዎች ያለክርስቶስ ትምህርት ራሳቸውን ወደ ዕውነተኛው ምንጭ እንደሚያደርሱ አምነው ነበር። ይህም እምነት ከዕውነት ለመራቅ ምክንያት ሆናቸው።” (ታብሌትስ ኦፍ አብዱል-ባሃ ቮል. 3 ገጽ 591-592)

መልእክተኞቹን ሳያውቅ እግዚአብሔርን ለማምለክ የሚፈልግ በዋሻ ውስጥ ሆኖ በምናቡ የፀሐይን ሙሉ በረከት እያሰበ እንደሚፈነጥዝ ሰው ይመሰላል።

 ጸሎት አስፈላጊና ግዴታ ነው

ጸሎት ለባሃኢዎች እንዲፈጽሙት በማያጠራጥር ሁኔታ የተሰጠ ግዴታ ነው። ባሃኦላህ ኪታቢ አቅዳስ በተባለው መጽሐፉ እንዲህ ይላል፦
“የእግዚአብሔርን ቃል በየዕለቱ ጥዋትና ማታ ድገሙ (አዚሙ)። ይህንን ያልፈጸመ ለእግዚአብሔር ትዕዛዝና ለፈቃዱም ታማኝ አልሆነም። እስከዛሬ ይህንን ያልፈጸመ ከእግዚአብሔር ከራቁት ወገን ነው። አገልጋይ ሰራዊቶቼ ሆይ! እግዚአብሔርን ፍሩ።

“ቀንም ሆነ ሌሊት በብዛት ስለምትፈጽሙት የቅዱሳን መጻሕፍት ንባብና ስለመልካም ተግባራቸሁም አትመኩ። በአደጋ ጊዜ ረዳቱና በገዛ ራሱ ፈቃድ ነዋሪው እግዚአብሔር የተገለጹትን ቅዱሳን መጻሕፍት ሁሉ ለግብር ይውጣ ያህል ከማንበብ ይልቅ በደስታና በአንጸባራቂ መንፈስ ጥቂት ጥቅሶችን መድገም የበለጠ ነው። የእግዚአብሔርን ቃል በምታነቡበት ጊዜ የድካምና የመሰልቸት ስሜት እንዳይሰማችሁ ይሁን። ነፍሳችሁን በድካም መንፈስ አታጎሳቅሉት፥ ይልቁንም በመገለጽ ክንፍ ዕውነት ወደሚመነጭበት ቦታ እንዲያንዣብብ አድሱት እንጂ። የምትረዱስ ከሆነ ይህ ነው ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርባችሁ።”
አብዱል-ባሃ ለአንድ ጠያቂ ሲጽፍ እንዲህ ይላል፦

“መንፈሳዊ ወዳጄ ሆይ! ... ጸሎት እጅግ በጣም አስፈላጊና ግዴታ መሆኑን እወቅ። ማንም የአእምሮ መታወክ ወይንም የማይታለፍ መሰናክል ካልደረሰበት በስተቀር በምንም ምክንያት ላለመጸለይ ይቅርታ አይደረግለትም።” (ታብሌትስ ኦፍ አብዱል-ባሃ ቮል. 3፤ ገጽ 683)

ከሌላ ጠያቂ ደግሞ፤ “እግዚአብሔር ሕግና ሥርዓትን በሚገባ መሥርቶ ሁሉም ነገር በዚያ እንዲመራ ካደረገ ለምን እንጸልያለን? የጸሎቱስ ሚስጢር ምን ይሆን! ለምንስ ይህንን ሰጠን! ይህንን አድርግልን! ብለን ፍላጎታችንን በመግለጽ መለመን አስፈለገን?” ሲል ላቀረበለት ጥያቄ አብዱል-ባሃ እንዲህ ሲል መልሷል፦
“ደካማ ብርቱውን መጠጋት እንደሚገባው ሁሉ እንዲሁም ጸጋን የሚሻ ከለጋሱና ከኃያሉ አምላክ መማጸን ይኖርበታል። ሰው አምላኩን ሲማልድ፥ ከቸርነቱም ውቅያኖስ ስጦታን ሲለምን ይህ ጸሎት ለልቡ ብሩህነትን ፥ ለዓይኑ ብርሃንን፤ ለነፍሱ ሕይወትን፥ ለሰውነቱም ክብርን ያስገኝለታል።

“በምትጸልዩበትና አምላክን በምትለምኑበት ጊዜ ‘ስምህ መፈወሻዬ ነው’ ስትሉ የቱን ያህል ልባችሁ እንደሚደሰት፥ነፍሳችሁ በእግዚአብሔር ፍቅር መንፈስ እንደሚረካና አእምሮአችሁም ወደ መንግሥቱ እንደሚሳብ ተገንዘቡ! በዚህም ምስሐብ የአንድ ሰው ችሎታና መጠን ይጨምራል። የጽዋው መጠን ሲያድግ ውሃ የመያዝ ችሎታው በዚያው መጠን ይጨምራል። እንዲሁም ጥም ሲበዛ የደመናው በረከት ለሰው ልጅ ጣዕም ፍላጎት ተስማሚ ይሆናል። የጸሎትና የፍላጎት ግልጽ ሚስጢር ይህ ነው።” (ለአንድ አሜሪካዊ ምዕመን ከተላከው መልእክት አሊ ኩሊ ክሃን እ.ኤ.አ.በጥቅምት ወር 1908 ዓ.ም. እንደተተረጎመው)
ባሃኦላህ ሦስት የግዴታ ጸሎቶችን ገልጿል። አማኙ ከሦስቱ ጸሎቶች አንዱን ሊመርጥ ይችላል። ነገር ግን በየቀኑ ባሃኦላህ በሰጠው መመሪያ መሠረት ጸሎቱን የማድረሱ ግዴታ አለበት።

ጸሎት የፍቅር ቋንቋ
እግዚአብሔር የሰውን ልብ ፍላጎት አስቀድሞ ስለሚያውቅ ጸሎት ለምን አስፈላጊ ሆነ? ብሎ ለጠየቀ አንድ ሰው ደግሞ አብዱል-ባሃ እንዲህ ሲል መለሰ፦
“አንድ ሰው ጓደኛውን ቢያፈቅር ይህን ፍቅሩን ሊገልጽ ይወዳል። ተወዳጁም መወደዱን ቢያውቅም ቅሉ አፍቃሪው ፍቅሩን ሊገልጽ ይፈልጋል። እግዚአብሔር የልቦችን ሁሉ ምኞት ያውቃል፥ የመጸላይ ፍላጎት መነሳሳት ግን ሰው ለእግዚአብሔር ካለው ፍቅር የሚመነጭ ተፈጥሮአዊ ባሕርይ ነው።…
“ጸሎት በቃላት ብቻ ሳይሆን በሃሳብና በሁኔታም ጭምር መሆን አለበት። ይህ ፍቅርና ትላጎት ከሌለ ግን እራስን ለማስገደድ መሞከር ጥቅም የለውም። ቃላት ያለፍቅር ትርጉም የላቸውም። አንድ ሰው ያለፍቅርና ደስታ ከአንተ ጋር ሲነጋገርና እንደማያስደስት ሥራ አድርርጎ የሚቆጥረው ከሆነ ከእርሱ ጋር መነጋገር ትወዳለህን?” (ከፎርትናይትሊ ሬቪው ጁን 1911 በሚስ ኤ. ኤስ እስቴቨንስ)

በሌላ ጊዜ ሲናገር ደግሞ እንዲህ ይላል፦
“በእውነተኛ ጸሎት ሰዎች የሚጸልዩት ለእግዚአብሔር ፍቅር ብቻ እንጂ እርሱም ወይንም ሲኦልን በመፍራት፥ ወይም ሲሳይና በመንግሥተ ሰማያት ወሮታ ለማግኘት አይደለም። ... አንድ ሰው ሌላውን ሲያፈቅር የተወዳጁን ስም ከመጥራት ሊቆጠብ አይችልም። እግዚአብሔርን ለሚወድማ የእርሱን ስም ከማንሳት መታገድ ምንኛ አስቸጋሪ ነው ... መንፈሳዊ ሰው እግዚአብሔርን ከማሰብ በስተቀር ሌላ ደስታ የለውም።” (ፎሮም ኖትስ ኦፍ ሚስ አልማ ሮበርት

Interesting blog? Like it on Facebook, +1 on Google, Tweet it or share this article on other bookmarking websites.

ህግጋት

  • ሥራ ስግደት ነው
  • በዓላትን ማክበር
  • ባሃኢ ምንድን ነው?
  • አልኮልና አደንዛዥ ዕፆች መከልከል
  • ጋብቻ
  • ፀሎት
  • ፆም
  • Follow via Facebook
  • Follow via Youtube
unity

© 2023 የኢትዮጵያ ባሃኢዎች

Go Top