የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
  • የባሃኢ ትምህርቶች
    • አምላክና ሐይማኖቶች
    • የአምላክ መልእክተኞች
    • የባሃኢ ትምህርቶች
    • ህግጋቶችና ደንቦች
    • አስተዳደር
  • ማህበረሰባዊ ተሳትፎ
    • ማህበረሰብ ግንባታ
    • የወጣቶች እንቅስቃሴ
  • የባሃኢ ማህበረሰብ
    • የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
    • የአለም ዓቀፍ ማህበረሰብ
    • የባሃኢ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ - አዲስ አበባ ጽ / ቤት
    • ባሃኢዎችን እናስተዋውቃችሁ
  • የባሃኢ መጽሐፍት
    • ቅዱሳን ጽሑፎች
    • ሌሎች
  • ለበለጠ መረጃ
    • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች
    • መልእክት ይላኩልን
    • ቪዲዮዎች
  • ENGLISH

ሥራ ስግደት ነው


ኤኮኖሚ ነክ ከሆኑት ከባሃኦላህ ጠቃሚ ትዕዛዛት አንዱ ማንኛውም ሰው ጠቃሚ ሥራ ላይ እንዲሠማራ ነው። በማኅበራዊ ኑሮ ቀፎ ውስጥ ሳይሠራ የሚጠቀም አውራ መኖር የለበትም፤ ሙሉ ጤንነት ኖሮት የህብረተ ሰቡን ሀብት የሚመጥ ጥገኛ አካል መኖር የለበትም።

እንዲህም ይላል፦
“እያንዳንዳችሁ በኪነ ጥበብ፥ በንግድና በመሳሰሉት ሥራ ላይ እንድትሠማሩ ታዛችኋል። ይህንንም ሥራችሁን ለእውነተኛው አምላክ ከምታቀርቡት ስግደት ጋር ተመሳሳይ አድርገንላችኋል። ሕዝቦች ሆይ! ስለ እግዚአብሔር ምህረትና ደግነት በማሰብ ጠዋትና ማታ አመስግኑት።

“በስንፍና ጊዜአችሁን አታባክኑት፤ እናንተንና ሌሎችን በሚጠቅም ሥራ ላይ ተሠማሩ። በአድማሱ የዕውቀት ፀሐይና መለኮታዊ ቃላት በሚያንጸባርቁት በዚህ መልእክት የታወጀው ይህ ነው! በእግዚአብሔር ፊት ከሁሉም ይበልጥ የተናቀ ቁጭ ብሎ የሚለምን ነው። የምክንያቶች ምክንያት የሆነውን እግዚአብሔርን አምናችሁ በሥራ ላይ የምትሠማሩበትን መንገድ ፈልጉ።” (ግላድ ታይዲንግስ)

ለአሁኑ ጊዜ የሥራ ዓለም ከሚጠፋው ኃይል የሌሎችን ሰዎች ሙከራ ለመሠረዝና ፍሬቢስ ለማድረግ በሥልጣን ሽሚያና በውድድር የሚባክነው ጉልበት የቱን ያህል ነው! ስንቱስ ነው በይበልጥ ጉዳት በሚያስከትል መንገድ የሚጠፋው! ሁሉም ቢሠራና፥ በአእምሮ ሆነ በእጅ የሚከናወነው ሥራ ሁሉ፥ ባሃኦላህ እንደሚያዘው፥ ሥራ ለሰው ዘር ጥቅም ሲውል ጤነኛ፥ ምቹና ከፍተኛ ለሆነ ኑሮ የሚያስፈልገው ነገር በሙሉ ለሁሉም በደንብ በተዳረሰ ነበር። ደሳሳ ቤቶችና ያልጸዱ ሠፈሮች፥ ችጋር፥ ድህነት፥ የኢንዱስትሪ ባርነትና ለጤና ጠንቅ የሆኑ ጎጂ ሥራዎችም ባልኖሩ ነበር።

Interesting blog? Like it on Facebook, +1 on Google, Tweet it or share this article on other bookmarking websites.

ህግጋት

  • ሥራ ስግደት ነው
  • በዓላትን ማክበር
  • ባሃኢ ምንድን ነው?
  • አልኮልና አደንዛዥ ዕፆች መከልከል
  • ጋብቻ
  • ፀሎት
  • ፆም
  • Follow via Facebook
  • Follow via Youtube
unity

© 2023 የኢትዮጵያ ባሃኢዎች

Go Top