የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
  • የባሃኢ ትምህርቶች
    • አምላክና ሐይማኖቶች
    • የአምላክ መልእክተኞች
    • የባሃኢ ትምህርቶች
    • ህግጋቶችና ደንቦች
    • አስተዳደር
  • ማህበረሰባዊ ተሳትፎ
    • ማህበረሰብ ግንባታ
    • የወጣቶች እንቅስቃሴ
  • የባሃኢ ማህበረሰብ
    • የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
    • የአለም ዓቀፍ ማህበረሰብ
    • የባሃኢ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ - አዲስ አበባ ጽ / ቤት
    • ባሃኢዎችን እናስተዋውቃችሁ
  • የባሃኢ መጽሐፍት
    • ቅዱሳን ጽሑፎች
    • ሌሎች
  • ለበለጠ መረጃ
    • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች
    • መልእክት ይላኩልን
    • ቪዲዮዎች
  • ENGLISH
ተደጋጋሚ ጥያቄዎች
  • ይህ ዝርዝር የኢትዮጵያ ባሃይ የፌስቡክ አካውንትን የሚጎበኙ ፈላጊዎች የሚጠይቋቸውን ጥያቄዎች ቀጣይነት ያለው ስብስብ ነው

የባሃኢ እምነት ምንድነው?

በ18 መቶዎቹ ኣጋማሽ ላይ የተመሰረተው የባሃኢ ሃይማኖት በአሁኑ ወቅት በፍጥነት በማደግ ላይ ከሚገኙት የዓለም ሃይማኖቶች መካክል አንዱ ነው። በዓለም ዙሪያ ከ5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ተከታዮች ያሉት ሲሆን በስርጭት ፍጥነት ከክርስትና ቀጥሎ የሁለተኝነት ደረጃን ይዞ ይገኛል። ባሃኢዎች በመላው ዓለም ከ100,00 በሚሆኑ ከተሞችና ክልሎች ውስጥ መገኘታቸው በራሱ የምድራችንን አንድ ሃገር መሆን መልዕክት የሚጋሩ በርካታ ስዎች በዓለም ዙሪያ እንደሚገኙና ለዚህ ዓላማም ተግተው የሚሰሩ መሆናቸውን ይመሰክራል።

ለበለጠ መረጃ: የባሃኢ እምነት ምንድነው?

የባሃኢ ሃይማኖት እንደ መጽሐፍ ቅዱስ እና ቁርዓን ዓይነት የራሱ የሆነ ቅዱስ መጽሐፍ አለው?

የባሃኢ እምነት እጅግ ታላቁ ቅዱስ መጽሐፍ በባሃኦላህ የተገለጸው የሕግጋት መጽሐፍ ሲሆን፤ ኪታቢ አቅዳስ ተብሎ ይጠራል። ይህ መጽሐፍ ከ100 ጥራዞች በላይ ከሆኑት የባሃኦላህ ጽሑፎች መካከል አንዱ ነው።

ለበለጠ መረጃ: የባሃኢ ቅዱሳን ጽሑፎች

የባሃኢዎች ዓላማ ምንድን ነው?

ባሃኢዎች የባሃኦላህ ተከታይ እንደመሆናቸው መጠን ዓላማቸውም ባሃኦላህ የተላከበትን መለኮታዊ ተልዕኮ ማራመድ ነው። የባሃኢ ሃይማኖት የጥሩ አስተሳሰቦች ጥርቅም ሳይሆን ራሱን የቻለ፣ በደንብ የተደራጀ ሥርዓት፣ ሕግና ዓላማ ያለው ሃይማኖት ነው። የባሃኢ እምነት ህይወትም መንገድም የሆነ፣ ለዚህ ዘመን የተገለጸ ፈቃደ- እግዚአብሔር ነው። የባሃኢ ሃይማኖት እምነት በተግባር የሚተረጎምበት በእውቀት ላይ የተመሠረተ ሕይወት ነው። ከላይ እንደተባለው፣ ዓላማውም የመላው የሰው ዘር አንድነትን መመስረት ነው። በህግዚአብሔር ፈቃድ ላይ የተመሠረተው ይህ ትጋት፣ ተስፋ የተሰጣት የእግዚአበር መንግስት በሰማይ እንደሆነች ሁሉ እንዲሁም በምድርም እንድትሆን ያስችላል። በዚህ ሥራ ሶስት ተሳታፊዎች እንዳሉ የእምነቱ የአስተዳደር ከፍተኛ አካል የሆነው ተቋም ዓለም አቀፍ ቤተ-ፍትሕ ይነግረናል። እያንዳንዱ ተሳታፊ በጣም ጠቃሚ ሚና ይጫወታል። እነዚህም ሦስት ተሳታፊዎች፦ ግለሰቡ፥ ማህበረሰቡ፣ እና የእምነቱ ተቋማት ናቸው።

ለበለጠ መረጃ: የባሃኢዎች ዓላማ ምንድን ነው?

ባሃኦላህ ማን ነው?

ባሃኦላህ በኢራን ዋና ከተማ በቴህራን እ.ኤ.አ በ1817 ተወለደ። ከልጅነቱ ጀምሮ የታላቅነት ምልክቶች ይታዩበት ነበር። ትምህርት ቤት መግባት አላስፈለገውም ነበር። ምክንያቱም አምላክ መለኮታዊ ዕውቀት አጐናጽፎታልና። ባሃኦላህ ታላቅና ታዋቂ ከሆነ ቤተሰብ ነበር የተወለደው። ወጣት በነበረበት ጊዜ ንጉሱ ከፍተኛ ሹመት ሰጥቶት ነበር። እርሱ ግን አልተቀበለውም። ጊዜውን የተጨቆኑትን፣ ሕሙማንና ድሆችን በመርዳት እንዲሁም ፍትህን በማራማድ ሊያውለው ፈለገ። የባሃኦላህ መከራ የጀመረው ወዲያው የአምላክን እምነት ለማወጅ እንደተነሳ ነበር። ሕይወቱን ሁሉ የኖረው በግዞት፣ በእስራትና በጭቆና ነበር። መጀመሪያ በቴህራን ከተማ አንድ ጨለማና ፀሐይ የማይደርስበት ጉርጓድ ውስጥ በሠንሰለት ታሰረ። ከዚያም ከአንዱ አገር ወደ ሌላው አገር አራት ጊዜ በግዞት ተንከራተተ። በመጨረሻም በዚያ ዘመን በኦቶማን ግዛት ውስጥ የእስር ከተማ ወደነበረች በእስራኤል አገር ወዳለችው አቆር ከተማ ተጋዘ። በዚች ከተማ ስቃዩ ከመብዛቱ የተነሳ አቆርን እጅግ በጣም ታላቁ እስር ቤት ብሎ ጠራት። ሁለቱ ኃያላን መንግስታት፤ ማለትም የኢራን ንጉሥና የኦቶማን ንጉሠነገሥት፣ ባሃኦላህንና ትምህርቶቹን ለመቃወም ከፍተኛ ጥረት አደረጉ። ነገር ግን የእውነት ብርሃን በቀላሉ የሚጠፋ አይደለም። ይህን እንደእሳት የሆነውን እውነታ ለማጥፋት በላዩ ላይ የሚደፋው ውሃ ወደ ነዳጅነት ተለውጦ የበለጠ እሳቱን አፋፋመው። እያደገ የሄደውን የባሃኦላህን ታዋቂነት ለማቆም ምንም ማድረግ አልተቻለም። ባለስልጣኖቹ የበለጠ ሩቅ ቦታ ባጋዙት ቁጥር ወደ ትምህርቶቹ የሚሳቡና ብርታቱንና ግርማውን የሚያውቁ ሰዎች ቁጥር እየበዛ ሄደ። የማያቋርጥ ጭቆና ቢደርስበትም ከአርባ ዓመታት ለበለጠ ጊዜ ባሃኦላህ የእግዚአብሔርን ቃል መግለጽን ቀጠለ። ወደ እዚህ ዓለምም እጅግ በጣም ከፍተኛ ፍቅርና መንፈሳዊ ኃይል ከማምጣቱ የተነሳ የእምነቱ ድል የተረጋገጠ ሆኗል። እ.ኤ.አ 1892 ባሃኦላህ ከዚህ ዓለም ተለየ። ባሃኢዎች በምድር ላይ እጅግ በጣም ቅዱስ ቦታ ነው የምንለው መካነ መቃብሩ እስራኤል አገር በአቆር ከተማ አቅራቢያ ይገኛል። ባሃኦላህ ስለደረሰበት መከራ እንደሚከተለው ጽፏል፡- “... የሰው ልጅ ከእስረኝነት ነፃ ይወጣ ዘንድ በብረት ሰንሰለት ለመታሰር ፈቀደ፤ መለው ዓለም እውነተኛ ነፃነት ይቀዳጅ ዘንድ በዚህ እጅግ በጣም ብርቱ ምሽግ ውስጥ እስረኛ መሆንን ተቀበለ። የምድር ሕዝቦች ዘላቂ ፍስሐን ይቀዳጁ፣ በደስታም የተሞሉ ይሆኑ ዘንደ የኃዘንን ጽዋ እስከ መጨረሻው ጠብታ ጨለጠ። ይህ ከሩኀሩኁ፣ ከእጅግ በጣም መሐሪው፤ ጌታችሁ ምህረት የተነሳ ነው። በአምላክ አንድነት አማኞች ሆይ፣ እናንተ ትከበሩ ዘንድ መዋረድን፣ እናንተ ትበለጽጉና ታብቡ ዘንድ ብዙ ከባድ መከራዎችን ተቀብለናል። እርሱን፤ መላውን ዓለም በአዲስ ይገነባ ዘንድ የመጣውን፣ እነዚያ ከአምላክ ጋር ራሳቸውን ያወዳደሩት፣ ከከተሞች እጅግ በጣም ባድማ በሆነው ከተማ ውስጥ እንዲኖር እንዴት እንዳስገደዱት ተመልከቱ!”

ለበለጠ መረጃ: ባሃኦላህ ማን ነው?

በእግዚአብሔር/በአላህ ታምናላችሁ?

የፍጡራን ሁሉ ፈጣሪና ጌታ የሆነ አንድ አምላክ እንዳለ፣ የአምላክ ሕላዌ ግን በሰው ልቦና የማይደረስበት እንደሆነ ባሃኦላህ ያስተምረናል። ይህ ማለት ስለአምላክ በአእምሮአችን የምንቀርጸው ነገር የአምላክን ሕላዌ ወይም እውነተኛ ምንነት በምልዕነት አያስጨብጠንም ማለት ነው። በአጠቃላይ መልኩ ስናየው፣ ልክ ወንበር አናጺውን ሊገነዘብ እንደማይችል ሁሉ፣ የተፈጠረ ነገር ሁሉ ስለፈጣሪው በምልዐት ሊገነዘብ አይችልም። አምላክ የሁሉም ነገሮች ፈጣሪ ነው። መላውን ምድር ከነፍጥረቷ፣ ሕዋን ከነፈለኮቿ ፈጥሯል። አምላክ ፍጥረትን ካለመኖር ወደመኖር ያመጣው ለፍጡራኑ ባለው ፍቅር ምክንያት መሆኑን፣ የፍጥረት ሕልውናም ከአምላክ ፍቅር መገለጫዎች አንዱ እንደሆነ፣ ባሃኦላህ ያስተምረናል ። በባሃኦላህ አማካኝነት የተገለፀው ቃለእግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሰው ልጅ ሆይ! ያንተን መፈጠር ወደድሁ፣ ስለዚህም ፈጠርሁህ። ስለዚህም ስምህን እንዳነሳና ነፍስህን በህይወት እስትንፋስ እሞላት ዘንድ አንተም አፍቅረኝ። ስለዚህ ምንም እንኳ የአምላክ ሕላዌ ከግንዛቤያችን የላቀ ቢሆንም ፍቅሩ ሕይወታችንንና ሕልውናችንን ሳያቋርጥ ይዳስሳል። ይህ ፍቅርም ወደ እኛም የሚደርሰው በቃልኪዳኑ አማካኝነት ነው። በዚህ ዘለዓለማዊ ቃልኪዳን መሠረት አምላክ ብቻችንን ያለመመሪያ ፈጽሞ አይተወንም። የሰው ልጅ ከእርሱ በራቀ ቁጥር በመልዕክተኛው አማካኝነት ይገለጽና ፍቃዱንና ዓላማውን ያሳውቀናል። መገለጽ ወይንም ግልጸት ማለት ከዚህ ቀደም የማይታወቅን ነገር ማሳወቅ ማለት ነው። የአምላክ ግልጸቶች የአምላክን ቃልና ፍቃድ ለሰው ልጅ የሚገልጹ ሰብዕናዎች ናቸው። በየዘመኑ የአምላክን ፈቃድ (ሃይማኖት) የሚገልጹ መልዕክተኞቹ ከዚህ በተጨማሪ በሌሎች ስሞችም ይጠራሉ፡ ክስተት፣ ወይም ነቢይ፣ ወይም መልዕክተኛም ይባላሉ። እነዚህን የአምላክ ግልጸቶች ካዳመጥን አምላክን አዳመጥን ማለት ነው። አምላክ እነዚህን መልዕክተኞቹን ሊታወስ ከማይችል ጊዜ ጀምሮ ለፍጡሮቹ ሲልክ ነብር። ወደፊትም መላኩን አያቋርጥም። ታሪክ ከሚያስታውሳቸው የአምላክ ግልጸቶች መካከል አብርሃም፣ ሙሴ፣ ኢየሱስ፣ እና ነብዩ መሐመድ ይገኙበታል። ለዚህ ዘመን ከአምላክ የተላኩት ግልጸቶች ደግሞ ባብ እና ባሃኦላህ ናቸው። ከላይ እንደተባለው አምላክን በቀጥታ ልንደርሰበት አንችልም። እነኝህ ፍጹም የሆኑ ሰብዕናዎች ግን በየዘመኑ ወደ እኛ ይላካሉ። በመካከላችን ይኖራሉ። መመሪያ ይሰጡናል። ቁሳዊና መንፈሳዊ ዕድገትን (መዳንን) ለመቀዳጀት በሚያስችለን ኃይል (በመንፈስቅዱስ ሃይል) ይሞሉናል። ስለዚህ የባሃኦላህ ትምህርቶች ከሌሎች የአምላክ ሃይማኖት ትምህርቶች ጋር ይስማማሉ። ትምህርቶቹም ለዘመናችን የሰው ልጅ ሁኔታ መፍትሄ የሚሆኑ ናቸው። የሰውን ልጅ ሁኔታ ብናጤነው ሌላ የአምላክ ግልጸት መምጣት ያለበት ትክክለኛው ጊዜ አሁን መሆኑን እንስማማለን። ስለምንኖርበት ዘመን ሁኔታ ከሚናገሩ የባሃኦላህ ቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ የሚከተለውን እናገኛለን፡ “ይህ ቀን፣ የእግዚአብሔር እጅግ በጣም የላቁ ችሮታዎች በሰዎች ላይ የፈሰሱበት፣ የእርሱ እጅግ በጣም ታላቅ ፀጋ በተፈጠሩት ነገሮች ሁሉ ውስጥ የተናኙበት ቀን ነው። የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ልዩነቶቻቸውን በማስወገድ፣ በእርሱ እንክብካቤና ፍቅራዊ ደግነት ዛፍ ጥላ ሥር፣ በፍጽም አንድነትና ሰላም መኖር አለባቸው።”

ለበለጠ መረጃ: በእግዚአብሔር/በአላህ ታምናላችሁ?

ነፍስ ከሥጋዊ አካላችን ጋር ያላት ግንኙነት ምንድነው?

የባሃኢ ቅዱሳን ጽሑፎች፥ ሞት አዲስ እንደመወለድ የሚቆጠር፥ ከሥጋዊ ኑሮ እስረኛነት አምልጦ ወደ ሰፊው መንፈሳዊ ኑሮ መሸጋገር መሆኑንና ከዚያም በኋላ ያለው የኑሮ ዕድገት ወሰን እንደሌለው ያስተምራሉ።

ለበለጠ መረጃ: ነፍስ ከሥጋዊ አካላችን ጋር ያላት ግንኙነት ምንድነው?

ባሃኢ ያልሆኑ ሰዎች በባሃኢ እንቅስቃሴዎች ውስጥ መሳተፍ ይችላሉ?

ለሁሉም የኅብረተሰብ ክፍልና የሃይማኖት ተከታዮች ክፍት የሆኑ፥ተሳታፊዎቹ መንፈሣዊ ትምህርቶችን በግልና በጋራ ሕይወታቸው ሊተገበሩባቸው ስለሚችሉባቸው መንገዶች አብረው የሚፈትሹበት፥ እንዲሁም የሠውን ዘር ለማገልገል የተነሳሳ አዲስ ማኅበረሰብን በሂደት ለመገንባት የሚጥሩበት መድረክ በባሃኢዎች ዘንድ የጥናት ክበብ በመባል ይታወቃሉ። ከጥናት ክበባት በተጨማሪም፥ የተለያዩ ሃይማኖቶች፥ ባህል፥ ጎሳ፥ ዘር፥ አመለካከት፥ እና የኑሮ ደረጃ ያላቸው ሠዎች በወዳጅነት መንፈስ በአንድ ላይ ተሰባስበው ለማኅበረሰቡም ሆነ ለግል ሕይወታቸው መሻሻል ጸሎት የሚያደርሱባቸው ስብሰባዎች በየሰፈሩ ይካሄዳሉ። በቤተሰብ ጉዳዮች ደግሞ የህጻናትን ለጋ ልቦችና አዕምሮዎች ተንከባክበው የሚያሣድጉና በጸሎት፣በመዝሙር፣ በተረት፣ በጨዋታ፣ በሥዕልና በሥነ-ጥበብ አማካኝነት እንደ ደግነት፣ እውነተኝነት፥ እና ትዕግሥት የመሣሠሉ መንፈሣዊ ባኅሪያትን ለማዳበርና በሕይወታቸው ለመተግበር የሚያግዙኣቸው ክፍለ ጊዜዎች በየአካባቢው ይካሄዳሉ። በተጨማሪ፥ ዕድሜያቸው ከ11-15 ያሉ ታዳጊ ወጣቶች በጥናትና የኣገልግሎት ፕሮ ክቶች ኣማካኝነት ባኅሪያቸውን በማዳበርና ኣቅማቸውን በመገንባት ኣፍላ ጉልበታቸውን ኣስተባብረው በየኣካባቢያቸው ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ በቡድን በንቃት ይሳተፋሉ። ከላይ ከተጠቀሱት እንቅስቃሴዎች በአንዱ ወይም በሁሉም ለመሳተፍ እርስዎም ተጋብዘዋል።

ለበለጠ መረጃ: ባሃኢ ያልሆኑ ሰዎች በባሃኢ እንቅስቃሴዎች ውስጥ መሳተፍ ይችላሉ?

የባሃኢ በዓላት የትኞቹ ናቸው?

ባሃኢዎች በዓመት ውስጥ ስራ የማይሰሩባቸው 9 በዓላት አሉ።

ለበለጠ መረጃ: የባሃኢ በዓላት የትኞቹ ናቸው?

እምነቱ የሚገኝባቸው ሃገራት የትኞቹ ናቸው?

ባሃኢዎች፥ ከ200 በሚበልጡ ሃገራትና ግዛቶች፥ ከ100 ሺህ በላይ በሆኑ ከተማዎችና ክልሎች ውስጥ በዓለም ዙሪያ ይገኛሉ።

ለበለጠ መረጃ: እምነቱ የሚገኝባቸው ሃገራት የትኞቹ ናቸው?

ተጨማሪ ጥያቄዎች ካሉኝስ? የበለጠ መረጃ እንዴት ማግኝት እችላለሁ?

https://bahai.et
መልእክት ይላኩልን
0962-080808
0962-232323
የኢትዮጰያ ባሃኢዎች ብሔራዊ መንፈሳዊ ጉባዔ
ፖ.ሣ.ቁጥር 102፤
አዲስ አበባ ፤ኢትዮጵያ
ስልክ 0116181372
ኢሜል: nsa.bahai.ethiopia@gmail.com
አዲስ አበባ ባሃኢ ማዕከል ቦሌ ሩዋንዳ፤
ወደ ደሳለኝ ሆቴል በሚወስደው መንገድ 100 ሜትር ገባ ብሎ

ባሃኢ መሆን የምችለው እንዴት ነው?

ባሃኢ ለመሆን አስፈላጊ የሆነው ነገር ባሃኦላህ ለዚህ ዘመን የአምላክ ግልጸት ወይም መልዕክተኛ እንደሆነ በነፃነት መርምሮ ማረጋገጥ፣ ከዚያም የአምላክ ቃላትና መመሪያ በባሃኦላህ በኩል እንደተገለጹ መቀበልና ማመን ነው። አንድ ባሃኢ ባሃኦላህን ከተቀበለ በኋላ በንቃት ትምህርቶቹን በሕይወቱ ላይ ተግባራዊ ማድረግ መጀመርና በየዕለቱ ቅዱሳን ቃላትን በማንብ ስለ ባሃኢ እምነት ያለውን እውቀት ለመጨመር መጣር፣ ስለእምነቱ ላልሰሙ ሰዎችም ማሳወቅ አለበት።

ለበለጠ መረጃ: ባሃኢ መሆን የምችለው እንዴት ነው?

የማህበረሰብ ግንባታ

  • የህፃናት ትምህርት
  • የማህበረሰብ ግንባታ
  • የታዳጊ ወጣቶች ፕሮግራም
  • የጋራ ፀሎተ-አምልኮ
  • የጥናት ክበባት
  • Follow via Facebook
  • Follow via Youtube

ወጣቶች በማህበረሰብ ግንባታ ላይ እንዴት መሳተፍ ይችላሉ?

  • ህፃናትን በማስተማር

    የባሃኢ ሃይማኖት ሕፃናት የማሕበረሰቡ እንቁ እንደሆኑ ያምናል። በእነርሱ ውስጥ የወደፊቱ መልካም ተስፋ ተደብቆ ይገኛል። ይህ መልካም ተስፋ እውን እንዲሆን ግን ሕፃናትን በመንፈሳዊ ሕይወት ተንከባክቦና ኮትኩቶ ማሳደግ ያሻል።

  • የማህበረሰብ የጋራ ፀሎትን በማካሄድ

    ከባሃኢ ሃይማኖት ዋና ዋና መርሆዎች አንዱ ከሁሉም ሃይማኖት ተከታዮች ጋር በወዳጅነት መቀላቀል ሲሆን፤ የዚህም የተግባር መገለጫ የሁሉንም የሃይማኖት ተከታዮች የሚያሳትፉ የጋራ ፀሎተ አምልኮ ክፍለ ጊዜዎችን ማካሄድ ነው።

  • የታዳጊ ወጣቶች ክፍለ ጊዜዎችን በማካሄድ

    በየታዳጊ ወጣቶች የትምህርት ፕሮግራም ውስጥ የሚሳተፉት እድሜያቸው ከ12 እስከ 15 ዓመት የሆኑ ልጆች ናቸው።

  • የጥናት ክበባትን በመክፈት

    የጥናት ክበቦች በቤት ውስጥ ወይንም እንደሁኔታው በሚመች ቦታና አካባቢ ቁጥራቸው ለመወያየት በሚመች መልኩ የሚወሰን ጎልማሶች በሳምንት የሚፈልጉትን ቀን ያህል ወስነው የሚወያዩብትና የሚያጠኑበት መድረክ ነው።

© 2023 የኢትዮጵያ ባሃኢዎች

Go Top