ለእግዚአብሔር ማደር መሰል ፍጡራንን ማገልገል ማለት ነው። ከዚህ በስተቀር በምንም መንገድ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ልንሆን አንችልም። ለመሰል ወንድሞቻችን ጀርባችንን ብንሰጥ ለእግዚአብሔርም እንዲሁ ማድረጋችን ነው።
“የሰው ልጅ ሆይ! ምህረትን ብትሻ እራስህን የሚጠቅምህን አትፈልግ፤ ግን መሰል ወንድሞችህን የሚጠቅመውን እንጂ። አይንህን ወደ ፍትህ የምታዞር ከሆነ ለራስህ የምትመርጠውን ለጎረቤትህ ምረጥ።” ባሃኡላህ
ስለዚህ ባሃኢዎች በግላቸውም ሆነ በጋራ በመሆን የሚኖሩባቸውን ማህበረሰብ ለማገልገል ከጓደኞቻቸውና ከጎረቤቶቿቸው ጋር ትከሻ ለትከሻ ሆነው የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ያደርጋሉ። ከእንቅስቃሴዎቻቸው ውስጥ ትልቁን ቦታ የሚሰጡት ትምህርትን ለህፃናት፥ ለታዳጊ ወጣቶች፥ወጣቶችና ጎልማሶች ማስፋፋትን ነው። ምክንያቱም ሰዎችን የሚያሰለጥንና የሚመራ እንዲሁም በተፈጥሮ የተሰጣቸውን እምቅ ችሎታ እንዲያወጡ የሚያደርገው ትምህርት ነው፥ እንዲሁም ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተላኩ ነቢያቶች ሁሉ ከፍተኛ ዓላማ ትምህርት ነው። በባሃኢ ሃይማኖት ትምህርት በመሰረቱ ተፈላጊና ማለቂያ የሌለው መሆኑ በግልፅ ታውጇል። ባሃኡላህ እንዲህ ይመክረናል “በክብር ብእር አማካይነት የተገለፀውን ለልጆቻችሁ አስተምሩ። ከታላቅነትና ከኃይል ሰማይ የወረደላችሁን አስተምሯቸው። የመሃሪውን መልእክት በቃላቸው አጥንተው፥ ጣእም በተመላው ዜማ በየቤተ መቅደሱ አዳራሽ እንዲያሰሙ አድርጋቸው።”
በዚህ መሠረትም ባሃኢዎች በግላቸውም ሆነ በጋራ በመሆን የሁሉንም ሃይማኖት ተከታዮች የሚያሳትፉ የጋራ ፀሎተ-አምልኮ ጉባዔዎች፣ የሕፃናት መንፈሳዊ ትምህርት፣ የታዳጊ ወጣቶች ፕሮግራም፤ የወጣቶችና የጎልማሶች የጥናት ክበባትን ያካሂዳሉ። የነዚህም እንቅስቃሴቆች መሰረታዊ አላማ መንፈሳዊና ቁሳዊ እድገት ለማህበረሰቦቻችን ለማምጣት ነው።
“የእግዚያብሔር ህዝቦች ሆይ! ስለራሳችሁ ብቻ አትባክኑ ፥ ስለ ዓለም መሻሻልና ስለ ህዝቦቿም መሰልጠን አስቡ” ባሃኡላህ
እንደነዚህ አይነት ሁሉን አሳታፊ እና አነቃቂ እንቅስቃሴዎች ላይ መሳተፍ ይፈልጋሉ?
መልዕክት ይላኩልን
Interesting blog? Like it on Facebook, +1 on Google, Tweet it or share this article on other bookmarking websites.