በታዳጊ ወጣቶች የትምህርት ፕሮግራም ውስጥ የሚሳተፉት እድሜአቸው ከ12 እስከ 15 ዓመት የሆኑ ልጆች ናቸው። ይህ የእድሜ ክልል ከልጅነት ወደ ሙሉ ወጣትነት የመሸጋገሪያ ወሳኝ የእድሜ ክፍል ሲሆን ፈጣን አካላዊ ፥ አእምሮእዊና ስሜታዊ ለውጦች ይካሄዱበታል። መንፈሳዊና አእምሮአዊ አመለካከታቸውም መስፋት ይጀምራል። በራሳቸው ውስጥ አዲስ የሆነ ጥያቄዎችንና እይታን፥ አቅምንና ችሎታን የሚያስተናግዱበትም ጊዜም ነው። ህብረተሰቡ ብዙውን ጊዜ ይህንን የዕድሜ ክልል በአንድ ሰው ሕይወት ውስጥ እንደ ሁከት ጊዜ ሊያየው ይችላል። ነገር ግን የታዳጊ ወጣቶች የትምህርት ፕሮግራም በእነዚህ ወጣቶች ላይ ርህራሄን፣ የፍትህ ስሜትን፣ ስለ አለም ለማወቅ ጉጉት እና ለተሻለ አለም ግንባታ የበኩላቸውን አስተዋፅዖ ለማድረግ ያላቸውን ፍላጎት ይመለከታል።
የታዳጊ ወጣቶች የትምህርት ፕሮግራም በዚህ የእድሜ ክልል የሚገኙ ታዳጊዎችን የመግለፅ አቅማቸውን የሚያሳድግ፣ ጠንካራ የሞራል ማንነትእንዲመሰርቱ የሚያደርግ እንዲሁም ያላቸውን ጉልበት ማህበረሰባቸውን ለማሳደግ እንዲጠቀሙበት አቅምን የሚፈጥር ትምህርታዊ ፕሮግራም ነው። በዋናነት የስነ-ምግባር (የግብረገብ) ትምህርት ሆኖ የቋንቋ ፥ የሂሳብ ፥ የሳይንስ ችሎታቸውንም የሚያዳብር፥ ኪነ-ጥበብ እና መዝናኛዎችን ፈጠራ በተሞላው ሁኔታ መጠቀምን የሚያስችል ነው። በተጨማሪም የተለያዩ የአገልግሎት ውጥኖችን (ፕሮጀክቶችን) በመቅረፅ መተግበር የሚያስችል አካሔድ አክሏል። አብዛኛውን ጊዜ በመርሀ-ግብሩ ውስጥ የሚሳተፉ የታዳጊ ወጣቶች ቡድኖች በየሳምንቱ በመገናኘት ከላይ የተጠቀሱትን እንቅስቃሴዎች በተከታታይነት ያካሂዳሉ።
በታዳጊ ወጣቶች ፕሮግራም ላይ ለማገልገል ከፈለጉ መልእከት ይላኩልን
Interesting blog? Like it on Facebook, +1 on Google, Tweet it or share this article on other bookmarking websites.