የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
  • የባሃኢ እምነት
    • የባሃኢ እምነት ምንድን ነው
    • የባሃኢ እምነት መነሻዎች
    • ባሃኡላህ
    • የባሃኢ እምነት አስተዳደር
    • የባሃኢ እምነት በኢትዮጵያ
  • ማህበረሰባዊ ተሳትፎ
    • ንቁ ማህበረሰብ መገንባት
      • የአምልኮ ሕይወት
      • የህፃናት ትምህርት
      • የታዳጊ ወጣቶች ፕሮግራም
      • የጥናት ክበባት
      • የወጣቶች እንቅስቃሴ
  • የባሃኢ አስተምህሮቶች
    • መርሆዎች
    • አምላክና ሐይማኖቶች
    • ህግጋቶችና ደንቦች
  • የባሃኢ መጽሐፍት
    • ቅዱሳን ጽሑፎች
    • ሌሎች
  • ለበለጠ መረጃ
    • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች
    • ቪዲዮዎች
  • ENGLISH

የጥናት ክበባት

 የጥናት ክበብ አንድ ላይ ለማጥናት፣ ለማሰላሰል እና ለመስራት በየጊዜው የሚሰበሰብ አነስተኛ የሰዎች ስብስብ ነው።  አስራ አምስት አመት ወይም ከዚያ በላይ የሆነ ማንኛውም ሰው፣  ጾታም  ሆነ ሀይማኖት ሳይገድበው ለመሳተፍ የሚችልበት ሂደት ነው። የጥናት ክበቦች አላማ የተሳታፊዎችን መንፈሳዊ እና አእምሮአዊ ክህሎት በማዳበር ከራሳቸው ሰፈር ጀምሮ ማህበረሰባቸውን ለመለወጥ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ለማበርከት የሚያስችላቸውን አቅም ማሳደግ ነው። የጥናት ክበብ የሚከናወነው ተከታታይ የሆኑ ኮርሶችን አሳታፊ በሆነ እና ተከታታይነት ባለው መንገድ በማጥናት ነው።የጥናት ክበባት በቤት ውስጥ ወይንም እንደየሁኔታው በሌሎች በሚመች ቦዎች ውስጥ መካሄድ ይችላሉ።

የመጀመሪያው መጽሐፍ (መጽሐፍ 1)  "በመንፈስዊ ሕይወት ላይ እሰብታዎች" ይባላል።  እንደ ጸሎት፣ ተመስጦ፣ ህይወት እና ሞት እና የነፍስ እድገትን የመሳሰሉ መንፈሳዊ ጉዳዮችን ይመረምራል። በአሁኑ ጊዜ እስከ መፅሃፍ 14 ድረስ የተለያዩ ጭብጦችን የሚዳስሱ ዋና ዋና ተከታታይ ኮርሶች በአግልግሎት ላይ እየዋሉ የገኛሉ። የተከታታይ ኮርሶቹ ዋና ዓላማ ተሳታፊዎች ለማህበራዊና መንፈሳዊ አገልግሎት እንዲነሳሱ ማስቻል ሲሆን አጥኚዎችም በጥናት ክፍለ-ጊዜያቸው ለአገልግሎት የሚያስፈልጓቸውን ሃሳቦች በጥናት ይወያያሉ በጥልቀትም ያስቡበታል፥ እንዲሁም ለመተግበር ይነሳሳሉ። 

በተጨማሪም ለወጣቶችና ለሕፃናት አእምሮአዊና መንፈሳዊ እድገት ምቹ ሁኔታዎችን የመፍጠርና በቤተሰብ ውስጥም የመንፈሳዊና የቁሳዊ እድገት ጥምረት እውን ሊሆኑ የሚችሉበትን ሁኔታዎች የማመቻችትና በዘላቂነትም የማራመድ ብቃቶች ሁሉ በጥናት ክበባቱ አማካኝነት እንዲዳብሩና እንዲተገበሩ ጥረት ይደረጋል።

ለአንድ የጥናት ክበብ እንደ አስጠኚ በመሆን የሚያገለግል አንድ ግለሰብ ይኖረዋል። ይህ አስጠኚ የጥናት ከበቡ ውይይት አስተባባሪ እንጂ እንደ መምህር አይደለም። ከተሳታፊዎቹ ቀደም ብሎ ተከታታይ መፅሃፍቶቹን ቀድሞ ያጠና ሲሆን  በሌላ የጥናት ክበብ ደግሞ ተሳታፊ ሊሆን ይችላል።  የአስጠኚው ተግባር የጥናት ክፍለ-ጊዜው ሁሌ በሰመረ መልኩ መካሄዱን፥ ሁሉም በውይይቱም በጥናቱም መሳተፋቸውን ማረጋገጥ፥ አሳታፊ እንዲሆን ሁኔታዎችን ማመቻቻት፣ ተሳታፊዎችን  ማበረታታት ሲሆን እያንዳንዱ ተሳታፊ ደግሞ የትምህርታዊ  ሂደቱ ባለቤት መሆን በሚችልበት ሁኔታ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ይኖርበታል። 

የጥናት ክበባቱ ተሳታፊዎች ከእያንዳንዱ ከሚያጠኑት መፃሕፍት ጋር የተጎዳኘ የአገልግሎት ተግባርም ለማህበረሰባቸው እንዲሰጡ ይጠበቃል። የሚያጠኗቸው ተከታታይ መፅሃፎች እያንዳንዳቸው ማለትም ወጣት፥ ጎልማሳ፥ አዛውንት፥ ወንድ፥ ሴት ሁሉም አካባቢያቸውን፥ ማህበረሰባቸውን፥ አገራቸውንና ዓለምን በተሻለ መልኩ ለማነፅ አቅም እንዳላቸው ያስገነዝቡአቸውል። የጥናት ክበባቱ እየበዙ በመጡ ቁጥር ተሳታፊዎች ለህይወት ያላቸው አመለካከት ያድጋል፥ ለማገልገል ያላቸው አቅምና መነሳሳትም ይጎለብታል፥ በማህበረሰብ ደረጃም በንቃት የሚወያዩና ማገልገልና ማምለክ የተያያዙ የሕይወታቸው ገፅታዎች እንደሆኑ ማጤን ይጀምራሉ።

በእንደዚህ አይነት አነቃቂ የጥናት ከበባት ላይ መሳተፍ ከፈለጉ መልእክት ይላኩልን

Interesting blog? Like it on Facebook, +1 on Google, Tweet it or share this article on other bookmarking websites.

የማህበረሰብ ግንባታ

  • የህፃናት ትምህርት
  • የታዳጊ ወጣቶች ፕሮግራም
  • የአምልኮ ሕይወት
  • የጥናት ክበባት
  • Follow via Facebook
  • Follow via Youtube

sc

© 2025 የኢትዮጵያ ባሃኢዎች

Go Top