“ወጣቶች አለምን ማንቀሳቀስ ይችላሉ!”
የመጡበት ማህበረሰብ ሁኔታ ምንም አይነት ይሁን ወጣቶች መንፈሳዊና አዕምሯዊ እድገትንና ለሰው ዘር ብልፅግና አስተዋእፆ ማበርከትን ይመኛሉ። ብዙ አስደናቂ ኃይሎች አላቸው። እነዚህን ኃይሎች በተገቢው ሁኔታ አቅጣጫ ማስያዝ አስፈላጊ ጉዳይ ነው። በተሳሳተ መንገድ የተመሩ እንደሆነ አልያም በሌሎች አግባብ ባልሆነ ሁኔታ መጠቀሚያ የሆኑ እንደሆነ ብዙ ማህበራዊ ቀውሶቹን ሊያስከትሉ ይችላሉ።
ወጣቱ ትውልድ በተወሰኑ ባህሪያት ተለይቶ ይታወቃል። ህይወታቸውም በተለያዩ ሃይሎች የተቀረፀ ነው። ብዙዎች ወጣቶች በተለያዩ የትምህርት ደረጃ በማለፍ እንዲሁም በቤተሰብና በማህበረሰብ ህይወት አልፈው ለጎልማሳነት ተግባራት ማለትም ለትዳርና ለስራ በመዘጋጀት ላይ ያሉ ናቸው። ለአንዳንዶቹ ደግሞ የወጣትነት ህይወት ከእነሱ በእድሜ በጣም የበለጡ ሰዎች ሊሰሯቸው የሚገባ የስራ ሃላፊነቶች የተጣሉባቸው ሊሆኑ ይችላሉ። እንዲሁም የቤተሰባቸው ህልውና በእነርሱ ትከሻ ላይ ያረፈ ይሆናል። ተወላጅነታቸውም ከዓለም ትንሹ ገጠር መንደር እስከ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን የያዙ ትልልቅ የከተማ ማእከሎች ውስጥ ባሉ ሰፈሮች ድረስ የተለያዩ ናቸው።
የባሃኢ ፅሁፎች እንደሚገልፁት በዓለም ላይ “የጋራ ደህንነትን ለማምጣት ከሚደረግ ግልጋሎት የበለጠ” የተከበረ ተግባር እንደሌለና “መነሳትና ብዙሃኑን ለማገልገል በሙሉ ሃይላቸው ራሳቸውን ማትጋታቸው” መሆኑን ይገነዘባሉ። ለማህበረሰቡ የሚደረግ ከእኔነት የፀዳ አገልግሎት ግለሰባዊ እድገትና ለማህበረሰብ መሻሻል አስተዋፅኦ የማበርከት አቅምን ማጎልበት ያስችላቸዋል። “ምክንያቱም “ለሰው ልጅ የሚሰጥ አገልግሎት ለአምላክ የሚሰጥ አገልግሎት ነው።” ተሰጥኦአቸውንና ችሎታዎቻቸውን ማህበረሰቡን ወደተሻለ ደረጃ ከፍ እንዲል ካዋሉ እነሱ “የፍጥረት ዓለም የሰላምና የመረጋጋት ምክንያት ይሆናሉ።” የእለት ተዕለት እንቅስቃሴዎቻቸውን በልግስና የመስጠት መንፈስ ሲያላብሱና ለሌሎች ደህንነት ለበጎ ፈቃደኝነት ሲሰሩ የአምላክን እርዳታና ማረጋገጫዎች ይስባሉ።
ለማህበረሰብ ደህንነት አስተዋዕፆ የማድረግ ታላቅ ሃላፊነትን የተጋፈጠው የአሁኑ ወጣት ትውልድ ነው። ከዚህም በተጨማሪ በማህበረሰቡ ውስጥ ከእነሱ በእድሜ ለሚያንሱት ወጣቶች የአዲሱ ስልጣኔ ገንቢዎች ለመሆን የሚያስችላቸውን መንፈሳዊና አእምሯዊ ሃይሎች ለመቀዳጀት የሚያስችሏቸውን ምቹ አካባቢዎች (ኢነቫይሮመንት) የማመቻቸቱ ሃላፊነትም በእነሱ (በአሁኑ ወጣት ትውልድ) ላይ የተጣለ ነው። ሃላፊነቱ በእርግጥ እጅግ ትልቅ ነው። እራሳቸውን ከጎጂ ሃይሎች ለመመከት ፥ ወጣቶች በአምላክ የማይቀር እርዳታ ላይ እምነታቸውን ሊያሳድሩ ይገባል።
READ MORE: http://www.bahai.org/
Interesting blog? Like it on Facebook, +1 on Google, Tweet it or share this article on other bookmarking websites.