የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
  • የባሃኢ ትምህርቶች
    • አምላክና ሐይማኖቶች
    • የአምላክ መልእክተኞች
    • የባሃኢ ትምህርቶች
    • ህግጋቶችና ደንቦች
    • አስተዳደር
  • ማህበረሰባዊ ተሳትፎ
    • ማህበረሰብ ግንባታ
    • የወጣቶች እንቅስቃሴ
  • የባሃኢ ማህበረሰብ
    • የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
    • የአለም ዓቀፍ ማህበረሰብ
    • የባሃኢ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ - አዲስ አበባ ጽ / ቤት
    • ባሃኢዎችን እናስተዋውቃችሁ
  • የባሃኢ መጽሐፍት
    • ቅዱሳን ጽሑፎች
    • ሌሎች
  • ለበለጠ መረጃ
    • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች
    • መልእክት ይላኩልን
    • ቪዲዮዎች
  • ENGLISH

የህፃናት ትምህርት

 

የባሃኢ ሃይማኖት ሕፃናት የማሕበረሰቡ እንቁ እንደሆኑ ያምናል። በእነሱ ውስጥ የወደፊቱ መልካም ተስፋ ተደብቆ ይገኛል ። ይህ መልካም ተስፋ እውን እንዲሆን ግን ህፃናትን በመንፈሳዊ ህይወት ተንከባክቦና ኮትኩቶ ማሳደግ ያሻል። ይህ ዓለም በሚያግበሰብሳቸው ቁሳዊ ጥቅሞችና እምቢተኝነት አማካኝነት የህፃናት ደስታና ንፁነት ሊነፈግ ወይንም በቀላሉ በእሱ ሊሸነፍ አይገባም። ስልሆነ በሞራል ስነምግባር ትምህርት መታነፃቸው የወቅቱ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው።

አስተማሪዎች

የባሃኢ ሃይማኖት ለሁሉም ህፃናት ያዘጋጀው ትምህርትን የሚያስተምሩ አስተማሪዎች በባሃኢ የስልጠና ተቋማት የሰለጠኑ አስተማሪዎች ናቸው። ማንኛውም ወጣት ሆነ ጎልማሳ የዚህን ስልጠና በመውሰድ በየአካባቢው ህፃናትን በማስተማር የእግዚአብሔርን ግዴታ መወጣት ይችላሉ።

ተማሪዎች

የሕፃናት ትምህርቱን የሚወስዱት ሕፃናትም እድሜያቸው ከ11 ዓመት በታች የሆኑት ሲሆኑ እንደያስፈላጊነቱም በእድሜያቸው የሚከፋፈሉበት ሁኔታም ይኖራል። ትምህርቱም የሚስጠው እንደየአካባቢው ፍላጎት በሳምንት ለተወሰነ ጊዜ ይሆናል።

የትምህርቱ ይዘት

እያንዳንዱ የትምህርት ክፍለጊዜ የተቀረፀው በአንድ መንፈሳዊ ባህሪ ላይ እንዲያተኩር ተደርጎ ነው። ለምሳሌ በአንዱ ክፍለጊዜ የሚማሩት ስለፍቅር ወይም ስለፍትህ ከሆነ በፍቅር ወይም በፍትሕ ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ፀሎቶችን ያደርጋሉ፥ ቅዱሳን ጥቅሶችን በቃል ያጠናሉ፥ መዝሙሮችን ይዘምራሉ፥ ትረካዎችን ያዳምጣሉ፥ ጨዋታዎችን ይጫወታሉ ፥ ስእሎችን ይስላሉ። የባሃኢ የህፃናት ትምህርት በልጆች የትምህርት ክፍለጊዜ ስለሃይማኖት ህግና ቀኖና አያስተምርም። በአሁኑ ጊዜ ዓለማችን ያጣችው ሁሉንም ሊያሳትፍ የሚችል ከሃይማኖት ሰበካ ነፃ የሆነ በመንፈሳዊ ባህሪያት ላይ ብቻ የሚያተኩር የሞራል ስነምግባር ትምህርት ነውና።

የሚያስተምረው መንፈሳዊ ባህሪያትን ማለትም እውነተኝነትን፥ ታማኝነትን፥ ፍቅርን፥ አንድነትን ፍትሃዊነትንና የመሳሰሉትን ባህሪያትን ማዳበርን ነው። እነዚህ ባህሪያት ደግሞ በሁሉም ሃይማኖት ትምህርቶች ውስጥ እንድናዳብራቸው የታዘዙ ናቸው። ይህም የባሃኢ የህፃናት ትምህርት ክፍለጊዜን ማንም ሰው ከየትኛውም የሃይማኖትንና የአኗኗር ሁኔታ ውስጥም ቢሆንም ሊያከናውነው የሚችል እንዲሆን አድርጎታል። ትምህርቱ የሚሰጥበትም ስፍራ እንደየአካባቢው ሁኔታ በቤት ውስጥ ፥ በዛፍ ጥላ ስር፥ በትምህርት ቤት ውስጥና በሌሎች ምቹ አካባቢዎች ሊሆን ይችላል።

ለበለጠ መረጃ፤ www.bahai.org

Interesting blog? Like it on Facebook, +1 on Google, Tweet it or share this article on other bookmarking websites.

የማህበረሰብ ግንባታ

  • የህፃናት ትምህርት
  • የማህበረሰብ ግንባታ
  • የታዳጊ ወጣቶች ፕሮግራም
  • የጋራ ፀሎተ-አምልኮ
  • የጥናት ክበባት
  • Follow via Facebook
  • Follow via Youtube
unity

© 2023 የኢትዮጵያ ባሃኢዎች

Go Top