ከባሃኢ ሃይማኖት ዋና ዋና መርሆዎች አንዱ ከሁሉም ሃይማኖት ተከታዮች ጋር በወዳጅነት መቀላቀል ሲሆን፤ የዚህም የተግባር መገለጫ የሁሉንም የሃይማኖት ተከታዮች የሚያሳትፉ የጋራ ፀሎተ አምልኮ ክፍለ-ጊዜዎችን ማካሄድ ነው። ባሃኢዎች የጋራ ፀሎት የአንድ ማህበረሰብ ህብራዊ አብሮ መኖር ዋነኛ መገለጫ መሆኑን በመረዳት ይህ በሁሉም ቦታ እንዲተገበር ሁኔታዎችን ያመቻቻል። በዚህ የፀሎት ክፍለ-ጊዜም ሁሉም እንደየእምነቱ ፀሎቱ እንዲያደርግ፥ ከየቅዱሳን መፅሀፎቹ እንዲያነብ ይበረታታል።
ይህ ክፍለ-ጊዜ በየቤቱና እንደየሁኔታው በየአመቺ ቦታው የሚካሄድ ሲሆን ሁሉም በጋራ ሃላፊነት የሚወስዱበት እንቅስቃሴ እንጂ የግለሰብ ወይንም የአንዱ ሃይማኖት የበላይነት የሚኖረው አይደለም። የዚህ ክፍለ-ጊዜ ዓላማ በሁሉም ሰዎችና ሃይማኖቶች መካከል አንድነትን ለማጠንከር፥ መቻቻልን ለማጎልበት፥ ሰላማዊ ህይወትን ለመምራትና ጥላቻን ለመቋቋም ማስቻል ነው።
ይህን እንቅስቃሴ በአገራችን በተለያዩ የክልል ከተሞች መንደሮች ፥ ሰፈሮችና ቦታዎች እየተተገበረ ይገኛል። በዓለም ዙሪያ በተለያዩ ሃይማኖቶች ተከታዮች መካከል ካለው መቃቃርና የእርስ በእርስ ጥላቻ አንፃር፥ የተለያዩ ሃይማኖት ተከታዮች በአንድ መንፈሳዊ ማእድ ዙሪያ በፍቅርና በወዳጅነት መንፈስ ሲፀልዩ ማየት በእውነቱ ልብን በተስፋ የሚሞላ ነው።
ለበለጠ መረጃ፤ www.bahai.org
Interesting blog? Like it on Facebook, +1 on Google, Tweet it or share this article on other bookmarking websites.