የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
  • የባሃኢ ትምህርቶች
    • አምላክና ሐይማኖቶች
    • የአምላክ መልእክተኞች
    • የባሃኢ ትምህርቶች
    • ህግጋቶችና ደንቦች
    • አስተዳደር
  • ማህበረሰባዊ ተሳትፎ
    • ማህበረሰብ ግንባታ
    • የወጣቶች እንቅስቃሴ
  • የባሃኢ ማህበረሰብ
    • የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
    • የአለም ዓቀፍ ማህበረሰብ
    • የባሃኢ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ - አዲስ አበባ ጽ / ቤት
    • ባሃኢዎችን እናስተዋውቃችሁ
  • የባሃኢ መጽሐፍት
    • ቅዱሳን ጽሑፎች
    • ሌሎች
  • ለበለጠ መረጃ
    • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች
    • መልእክት ይላኩልን
    • ቪዲዮዎች
  • ENGLISH

የታዳጊ ወጣቶች ፕሮግራም

 

በታዳጊ ወጣቶች የትምህርት ፕሮግራም ውስጥ የሚሳተፉት እድሜአቸው ከ12 እስከ 15 ዓመት የሆኑ ልጆች ናቸው። ይህ የእድሜ ክልልም ወደ ሙሉ ወጣትነት የመሸጋገሪያ ወሳኝ የእድሜ ክፍል ነው።

በዚህ የእድሜ ክልል ፈጣን አካላዊ ፥ አእምሮእዊና ስሜታዊ ለውጦች ይካሄዳሉ። መንፈሳዊና አእምሮአዊ አመለካከታቸውም መስፋት ይጀምራል። በራሳቸው ውስጥ አዲስ የሆነ ጥያቄዎችንና እይታን፥ አቅምንና ችሎታን የሚያስተናግዱበትም ጊዜም ነው።

በእነዚህ አጭር ሶስት ዓመታት ውስጥ ስለራሳቸውና ስለማሕበረሰባቸው የሚኖራቸውን ዕይታና ልምድ ለቀጣዩ ህይወታቸው እንደ ዋና ሁኔታ ይወስዱታል። ሕይወታቸውም ከዚያ በሚያገኙት ሁኔታ ይቀረፃል። ይህ እይታቸው ስርዓት ባለው አግባብ እንዲቀረፅና እንዲመራ ዕድሉ ካልተመቻቸ ግን ስጋት፥ ተስፋ መቁረጥ፥ ያለመስማማትና የአመፅኝነት ስሜት ስለሚፈጥርባቸው የፀባይ ግራ መጋባት ሊታይባቸው ይችላል።

ስለ ታዳጊ ወጣቶች በሚታሰብበት ጊዜ በወላጆችም ሆነ በአስተማሪዎችም አእምሮዎች ውስጥ ብዙውን ጊዜ የሚመላለሱት ሃሳቦች አመፀኞች ናቸው፥ ትክክለኛ አስተሳሰብን ወይም ምክንያትን አይከተሉም፥ ከቁም-ነገረኝነትና ከበጎ ተግባራት የራቁ ናቸው፥ ወዘተ የሚሉ አፍራሽ ሃሳቦች ናቸው። ምንም እንኳን ታዳጊ ወጣቶች ከላይ የተጠቀሱት ባህሪያት በዚህ የእድሜ ክልል የሚታይባቸው ቢሆንም ፥ ከላይ እንደተባለው፥ የስሜታቸውንና የአስተሳሰባቸውን የለውጥ ሂደት በአግባቡ ተረድቶት የሚመራቸውና የሚንከባከባቸው ካገኙ ይህን ሁኔታንና የእድሜ ክልልን በስኬታማነት ይወጡታል፥ በቀጣዩ የህይወታቸው ዘመን ለሚጠበቅባቸው ሃላፊነቶችና ግዴታዎች የሚያስፈልጉ ብቃቶችን ያዳብሩበታል።

የታዳጊ ወጣቶች ቡድን መርሐ-ግብ በዋናነት የስነ-ምግባር (የግብረገብ) ትምህርት ሆኖ ቋንቋ ፥ ሂሳብ ፥ ሳይንስ ፥ የመሳሰሉ የቀለም ትምህርትንም የሚያካትቱ መፅሀፍትን ማጥናትን ፥ የአገልግሎት ውጥኖችን (እንቅስቃሴዎች) መቅረፅን፥ ኪነ-ጥበብ እና መዝናኛዎችን ፈጠራ በተሞላው ሁኔታ መጠቀምን፥ የሚያቅፍ ነው ። አብዛኛውን ጊዜ በመርሀ-ግብሩ ውስጥ የሚሳተፉ የታዳጊ ወጣቶች ቡድኖች በየሳምንቱ በመገናኘት ከላይ የተጠቀሱትን አራቱን አበይት እንቅስቃሴዎች በፕሮግራም ያካሂዳሉ።

አንድ ቡድን ከ2 እስከ 15 ታዳጊ ወጣቶችን ሊይዝ ይችላል። የመርሃ-ግብሩ ተከታታይ መፅሐፎች ከ11 ዓምት እስከ 13 ዓመት፥ ከ12 እስከ 14 ዓመት እና ከ13 እስከ 15 ዓመት ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉትን ታዳጊዎች እንዲረዱ ተደርገው የተዘጋጁ ናቸው።

READ MORE: http://www.bahai.org/

Interesting blog? Like it on Facebook, +1 on Google, Tweet it or share this article on other bookmarking websites.

የማህበረሰብ ግንባታ

  • የህፃናት ትምህርት
  • የማህበረሰብ ግንባታ
  • የታዳጊ ወጣቶች ፕሮግራም
  • የጋራ ፀሎተ-አምልኮ
  • የጥናት ክበባት
  • Follow via Facebook
  • Follow via Youtube
unity

© 2023 የኢትዮጵያ ባሃኢዎች

Go Top