የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
  • የባሃኢ ትምህርቶች
    • አምላክና ሐይማኖቶች
    • የአምላክ መልእክተኞች
    • የባሃኢ ትምህርቶች
    • ህግጋቶችና ደንቦች
    • አስተዳደር
  • ማህበረሰባዊ ተሳትፎ
    • ማህበረሰብ ግንባታ
    • የወጣቶች እንቅስቃሴ
  • የባሃኢ ማህበረሰብ
    • የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
    • የአለም ዓቀፍ ማህበረሰብ
    • የባሃኢ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ - አዲስ አበባ ጽ / ቤት
    • ባሃኢዎችን እናስተዋውቃችሁ
  • የባሃኢ መጽሐፍት
    • ቅዱሳን ጽሑፎች
    • ሌሎች
  • ለበለጠ መረጃ
    • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች
    • መልእክት ይላኩልን
    • ቪዲዮዎች
  • ENGLISH

የጥናት ክበባት

 

የጥናት ክበባት በቤት ውስጥ ወይንም እንደሁኔታው በሚመች ቦታና አካባቢ ቁጥራቸው ለመወያየት በሚመች መልኩ የሚወሰን ጎልማሶች በሳምንት የሚፈልጉትን ቀን ያህል ወስነው የሚወያዩበትን የሚያጠኑበት መድረክ ነው። የሚያጠኑአቸው መፅሐፎች በጥንቃቄና በባለሞያ የተዘጋጁ አለምአቀፋዊ ይዘት ያላቸው ተከታታይ ኮርሶች ናቸው።

ይዘታቸውም በዋነኛነት ከባሃኢ ቅዱሳን ፅሁፎች የተወጣጡ ሲሆኑ ከሌሎች ቅዱሳን ፅሁፎችም የሚጠቀስበት ሁኔታም አለ። የተከታታይ ኮርሱ ዋና ዓላማ ተሳታፊዎች ለማህበራዊና መንፈሳዊ አገልግሎት እንዲነሳሱ ማስቻል ሲሆን አጥኚዎችም በጥናት ክፍለ-ጊዜያቸው ለአገልግሎት የሚያስፈልጓቸውን ሃሳቦች በጥናት ይወያያሉ በጥልቀትም ያስቡበታል።

ጥናቱ በተሳታፊዎች ውስጥ ለማሳደግ ከሚያልማቸው ብቃቶች በከፊሉ፦ የአምላክን መንፈሳዊ ኃይል ፥ ፀጋውንና ረድኤቱን ፥ በፀሎትና በሱባዔ አማካኝነት ወደራስ የማምጣት ብቃት ፥ በአገልግሎት መንፈስ ከእያንዳንዱ ሰዎች ጋር በጋራ አካባቢውን የማገልገል ብቃትና መነሳሳትን ፥ ሕፃናቶችንና ታዳጊ ወጣቶችን በሞራል ስነ-ምግባራት ለማነፅ የሚያስፈልጉ መንፈሳዊና አእምሮአዊ እውቅትና ክህሎቶች ናቸው።

በተጨማሪም ለወጣቶችና ለሕፃናት አእምሮአዊና መንፈሳዊ እድገት ምቹ ሁኔታዎችን የመፍጠርና በቤተሰብ ውስጥም የመንፈሳዊና የቁሳዊ እድገት ጥምረት እውን ሊሆኑ የሚችሉበትን ሁኔታዎች የማመቻችትና በዘላቂነትም የማራመድ ብቃቶች ሁሉ በጥናት ክበባቱ አማካኝነት እንዲዳብሩና እንዲተገበሩ ጥረት ይደረጋል።

ይህ የጥናት ክበባት እድሜያቸው 15 ዓመት እና ከዚያ በላይ ያሉት ጎልማሳ ሰዎችን ያካትታል። ጥናቱ የሚካሄደውም እንደ አስጠኚ በሚሆን አንድ ግለሰብ አማካኝነት ነው። ይህ አስጠኚ ልዩ የሆነ ደረጃ የለውም። ከአጥኚዎቹ ቀደም ብሎ እንዴት የተከታታይ መፅሃፎቹ አስጠኚ መሆን እንደሚቻል ያጠና ግለሰብ ነው። ስለዚህ እያንዳንዱ አጥኚ ተከታታይ መፅሃፎችን ካጠና በኋላ እርሱ ራሱም አስጠኚ ይሆናል ማለት ነው። ሁሉ አጥኚ ትምህርቱን የመከታተል ሃላፊነት በዋነኛነት የራሱ ሲሆን የአስጠኚው ተግባር የጥናት ክፍለ-ጊዜው ሁሌ በሰመረ መልኩ መካሄዱን፥ ሁሉም በውይይቱም በጥናቱም መሳተፋቸውን ያጤናል፥ ይህም እንዲሆን ሁኔታዎችን ያመቻቻል። ተሳታፊዎቹን ሁሉ ይንከባከባል፥ ያበረታታል።

የጥናት ክበባቱ ተሳታፊዎች ከእያንዳንዱ ከሚያጠኑት መፃሕፍት ጋር የተጎዳኘ የአገልግሎት ተግባርም ለማህበረሰባቸው እንዲሰጡ ይጠበቃል። የሚያጠኗቸው ተከታታይ መፅሃፎች እያንዳንዳቸው ማለትም ወጣት፥ ጎልማሳ፥ አዛውንት፥ ወንድ፥ ሴት ሁሉም አካባቢያቸውን፥ ማህበረሰባቸውን፥ አገራቸውንና ዓለምን በተሻለ መልኩ ለማነፅ አቅም እንዳላቸው ያስገነዝቡአቸውል። የጥናት ክበባቱ እየበዙ በመጡ ቁጥር ተሳታፊዎች ለህይወት ያላቸው አመለካከት ያድጋል፥ ለማገልገል ያላቸው አቅምና መነሳሳትም ይጎለብታል፥ በማህበረሰብ ደረጃም በንቃት የሚወያዩና ማገልገልና ማምለክ የተያያዙ የሕይወታቸው ገፅታዎች እንደሆኑ ማጤን ይጀምራሉ።

READ MORE: http://www.bahai.org/

Interesting blog? Like it on Facebook, +1 on Google, Tweet it or share this article on other bookmarking websites.

የማህበረሰብ ግንባታ

  • የህፃናት ትምህርት
  • የማህበረሰብ ግንባታ
  • የታዳጊ ወጣቶች ፕሮግራም
  • የጋራ ፀሎተ-አምልኮ
  • የጥናት ክበባት
  • Follow via Facebook
  • Follow via Youtube
unity

© 2023 የኢትዮጵያ ባሃኢዎች

Go Top