የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
  • የባሃኢ ትምህርቶች
    • አምላክና ሐይማኖቶች
    • የአምላክ መልእክተኞች
    • የባሃኢ ትምህርቶች
    • ህግጋቶችና ደንቦች
    • አስተዳደር
  • ማህበረሰባዊ ተሳትፎ
    • ማህበረሰብ ግንባታ
    • የወጣቶች እንቅስቃሴ
  • የባሃኢ ማህበረሰብ
    • የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
    • የአለም ዓቀፍ ማህበረሰብ
    • የባሃኢ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ - አዲስ አበባ ጽ / ቤት
    • ባሃኢዎችን እናስተዋውቃችሁ
  • የባሃኢ መጽሐፍት
    • ቅዱሳን ጽሑፎች
    • ሌሎች
  • ለበለጠ መረጃ
    • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች
    • መልእክት ይላኩልን
    • ቪዲዮዎች
  • ENGLISH
best joomla menu module
ማህበረሰባዊ ተሳትፎ

ባሃኢዎች መንፈሳዊና ማሕበራዊ ዕድገት ለማምጣት የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ያደርጋሉ። በዚህ መሠረትም የሁሉንም ሃይማኖት ተከታዮች የሚያሳትፉ የጋራ ፀሎተ-አምልኮ ጉባዔዎች፣ የሕፃናት፣ የታዳጊ ወጣቶች፤ የወጣቶችና የጎልማሶች የስነ-ምግባር ትምህርትና የጥናት ክፍለ-ጊዜዎችን ያካሂዳሉ።

“የእግዚያብሔር ህዝቦች ሆይ! ስለራሳችሁ ብቻ አትባክኑ ፥ ስለ ዓለም መሻሻልና ስለ ህዝቦቿም መሰልጠን አስቡ” ባሃኡላህ

ባሃኢዎች በግላቸውም ሆነ ከጓደኞቻቸውና ጎረቤቶቻቸው ጋር ትከሻ ለትከሻ በመሆን መንፈሳዊና ቁሳዊ እድገት ለማህበረሰባቸው ለማምጣት የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ቅንነት በተሞላው ሁኔታ ያደርጋሉ።

ከእንቅስቃሴዎቻቸው ውስጥ ትልቁን ቦታ የሚሰጡት ትምህርትን ለህፃናት፥ ለታዳጊ ወጣቶች፥ወጣቶችና ጎልማሶች ማስፋፋትን ነው። ምክንያቱም ሰዎችን የሚያሰለጥንና የሚመራ እንዲሁም የተፈጥሮ እውቀታቸውን እንዲያሻሽሉ የሚያደርገው ትምህርት፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተላኩ ነቢያቶች ሁሉ ከፍተኛ ዓላማ ነው።

በባሃኢ ሃይማኖት ትምህርት በመሰረቱ ተፈላጊና ማለቂያ የሌለው መሆኑ በግልፅ ታውጇል። ትምህርት ለትክክለኛ ኑሮ ሁል ጊዜ ተፈላጊና ለማህበራዊ አኗኗርም መሰረቱ ነው። ትምህርት በትክክለኛው መንገድ ለሁሉም ሲሰጥ የሰው ልጅ ይለወጣል። ምድርም ገነት ትሆናለች ብለው ያምናሉ።

ከትምህርት ከፍተኛው ተፈላጊ የግብረገብ ትምህርት ነው ብለው ያምናሉ። ባሃኡላህ እንዲህ ይመክረናል “በክብር ብእር አማካይነት የተገለፀውን ለልጆቻችሁ አስተምሩ። ከታላቅነትና ከኃይል ሰማይ የወረደላችሁን አስተምሯቸው። የመሃሪውን መልእክት በቃላቸው አጥንተው፥ ጣእም በተመላው ዜማ በየቤተ መቅደሱ አዳራሽ እንዲያሰሙ አድርጋቸው።”

አስተማሪ ለስልጣኔ ከፍተኛ ኃይል ሲሆን፥ ማስተማርም ሰዎች ሊሹት የሚገባ ታላቅ ምኞት ነው ። ትምህርት የሚጀመረው በእናት ማህፀን ሲሆን፥ ህይወት ማለቂያ እንደሌለው ሁሉ ዕውቀትም ማለቂያ የለውም።

“ዕውቅት ለፍጡር (ለሰው) በክንፎችና በመወጣጫ መሰላል ይመሰላል። ዕውቅትን መፈለግ ለሁሉም ግዴታ ነው። በእርግጥ የሰው እውነተኛ ሀብቱ እውቀቱ ነው። ዕውቅቱ የክብር፥ የብልጽግና የደስታ፥ የፍስሃ፥ የሃሴትና፥ የከፍተኛ ፈንጠዝያ ማግኛ ምንጭ ነው።”

Interesting blog? Like it on Facebook, +1 on Google, Tweet it or share this article on other bookmarking websites.

  • Follow via Facebook
  • Follow via Youtube

የአብዱል ባሃ እርገት መቶኛ ዓመት መታሰቢያ 1921 - 2021

ህዳር 28 ቀን 1921 እ.ኤ.አ. አብዱል-ባሃ በቅድስት ሀገር ከዚህ አለም አለፈ  ። ህይወቱና ትሩፋቱ በዚህ መቶኛ አመት ዝክረ በዓሉ በመላው አለም ይታወሳል።ተጨማሪ ያንብቡ

 

© 2023 የኢትዮጵያ ባሃኢዎች

Go Top