የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
  • የባሃኢ ትምህርቶች
    • አምላክና ሐይማኖቶች
    • የአምላክ መልእክተኞች
    • የባሃኢ ትምህርቶች
    • ህግጋቶችና ደንቦች
    • አስተዳደር
  • ማህበረሰባዊ ተሳትፎ
    • ማህበረሰብ ግንባታ
    • የወጣቶች እንቅስቃሴ
  • የባሃኢ ማህበረሰብ
    • የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
    • የአለም ዓቀፍ ማህበረሰብ
    • የባሃኢ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ - አዲስ አበባ ጽ / ቤት
    • ባሃኢዎችን እናስተዋውቃችሁ
  • የባሃኢ መጽሐፍት
    • ቅዱሳን ጽሑፎች
    • ሌሎች
  • ለበለጠ መረጃ
    • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች
    • መልእክት ይላኩልን
    • ቪዲዮዎች
  • ENGLISH

የሐይማኖት ታዳሽነት

ዛሬ ዓለም ያለችበት ሁኔታ ከጥቂቶች በስተቀር ሰዎች የያዙትን ሃይማኖት ዕውነተኛ ትርጉም እንደገና ማጥናት የሚያስፈልጋቸው ለመሆኑ ማስረጃ ነው። ሰዎችንም እንደገና ለዚህ ጥናት መቀስቀስ ከባሃኦላህ ሥራዎች ዋና ክፍል ነው። ክርስቲያኖችን የተሻሉ ክርስቲያኖች፥ እስላሞችም እውነተኛ እስላሞች እና በጠቅላላው ሰዎችንም ሁሉ ለሚከተሉት ነቢያቸው መንፈስ እውነተኛ እንዲሆኑ ለማድረግ ነው።

‘ጊዜው ሲደርስ’ ተገልጾ ባለፉት ነቢያት የተሰጡትን ትንቢቶች ፈጽሞ፤ በበለጠ ግርማ መጥቶ፤ እነዚያ ነቢያት የደከሙበትን ሥራ በክብር እግቡ አድርሷል። ከቀድሞዎቹ በበለጠ ሁኔታ መንፈሳዊ እውነትን እያብራራ ግላዊ ወይንም ማኅበራዊ ለሆኑ የጊዜያችን ችግሮች የእግዚአብሔር ፈቃድ የሆነውን መፍትሔ ይሰጣል። ለአዲስና ለተሻለ ሥልጣኔ ጽኑ መሠረትን የሚያስገኝ ዓለም አቀፍ ትምህርት ሰጥቷል። ትምህርቱም በመጀመር ላይ ለሚገኘው ለአዲሱ ዘመን ኑሮ ተስማሚ ትምህርት ነው።


ባሃኦላህ መሠረታዊ የሆኑ መርሆዎችን፦
● የሰው ልጅ ዓለም አንድነት
● የተለያዩ የዓለም ሃይማኖቶች መወሃድ
● የሃይማኖትና የሳይንስ መስማማት
● የዓለም ሠላም መመስረት
● የዓለም አቀፍ አስታራቂ ድርጅት መቋቋም
● የዓለም አቀፍ ቤተ ፍትሕ መቋቋም
● የዓለም አቀፍ ቋንቋ መኖር
● የሴቶች ነጻነት መተግበር
● ትምህርት ለሁሉም መዳረስ
● የግልጽ ባርነት ብቻ ሳይሆን የኢንዱስትሪ ባርነትም እንዲወገድ ማድረግ
● የሰው ልጆች መብትና ነፃነት መጠበቅ

ባሃኦላህ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት መሠረታዊ የሆኑ መርሆዎችን በግልጽ ሲደነግግ ክርስቲያኖች፥እስላሞችና እንዲሁም የልዩ ልዩ ሃይማኖት ተከታዮች፥ ቀደም ሲል ሲቃወሙት ኖረዋል፤ አሁንም እየተቃወሙት ነው። ይሁን እንጂ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት መርሆዎች በተግባር ላይ ሲውሉ በእርግጥም ይህችን ዓለም ገነት ያድርጓታል።

Interesting blog? Like it on Facebook, +1 on Google, Tweet it or share this article on other bookmarking websites.

አምላክና ሐይማኖቶች

  • ተከታታይ ግልጸት
  • አምላክን እንዴት ማወቅ ይቻላል?
  • አምላክን ፍለጋ
  • የሐይማኖት ታዳሽነት
  • የሐይማኖት ታዳጊነት
  • የሐይማኖቶች አንድነት
  • Follow via Facebook
  • Follow via Youtube
unity

© 2023 የኢትዮጵያ ባሃኢዎች

Go Top