“የሰው ልጅ ሆይ! ምህረትን ብትሻ እራስህን የሚጠቅምህን አትፈልግ፤ ግን መሰል ወንድሞችህን የሚጠቅመውን እንጂ። አይንህን ወደ ፍትህ የምታዞር ከሆነ ለራስህ የምትመርጠውን ለጎረቤትህ ምረጥ።” ባሃኡላህ
ለእግዚአብሔር ማደር ለመሰል ፍጡራን ማገልገል ማለት ነው። ከዚህ በስተቀር በምንም መንገድ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ልንሆን አንችልም። ለመሰል ወንድሞቻችን ጀርባችንን ብንሰጥ ለእግዚአብሔርም እንዲሁ ማድረጋችን ነው።
በዚህ መሰረት ባሃኢዎች በግላቸውም ሆነ በጋራ በመሆን የሚኖሩባቸውን ማህበረሰብ ለማገልገል ከጓደኞቻቸውና ከጎረቤቶቿቸው ጋር ትከሻ ለትከሻ ሆነው የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ያደርጋሉ። አላማቸውም መንፈሳዊና ቁሳዊ እድገት ለማህበረሰባቸው ለማምጣት ሲሆን ይህንንም ሲያደርጉ ቅንነት በተሞላው ሁኔታ ነው።
ትምህርት
ባሃኢዎች ከእንቅስቃሴዎቻቸው ትልቁን ቦታ የሚሰጡት ትምህርትን በማስፋፋት ረገድ ነው። ምክንያቱም ሰዎችን የሚያሰለጥንና የሚመራ እንዲሁም የተፈጥሮ እውቀታቸውን እንዲያሻሽሉ የሚያደርገው ትምህርት፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተላኩ ነቢያቶች ሁሉ ከፍተኛው አላማ ነው። በባሃኢ ሃይማኖት ትምህርት በመሰሩት ተፈላጊና ማለቂያ የሌለው መሆኑ በግልፅ ታውጇል። አስተማሪ ለስልጣኔ ከፍተኛ ኃይል ሲሆን፥ ማስተማርም ሰዎች ሊሹት የሚገባ ታላቅ ምኞት ነው። ትምህርት የሚጀመረው በእናት ማህፀን ሲሆን፥ ሕይወት ማለቂያ እንደሌለው ሁሉ እውቀትም ማለቂያ የለውም። ትምህርት ለትክክለኛ ኑሮ ሁልጊዜ ተፈላጊና ለማህበራዊ አኗኗርም መሰረቱ ነው።
ትምህርት በትክክለኛው መንገድ ለሁሉም ሲሰጥ የሰው ልጅ ይለወጣል። ምድርም ገነት ትሆናለች። አብዛኛው ሰው በከንቱ ጥላቻ በአሳሳች ትምህርት ፥ በተሳሳተ ፍልስፍና እንዲሁም ከህፃንነቱ ጀምሮ በመጥፎ ፀባይ የተመረዘ በመሆኑ በአሁኑ ዘመን በእምነት ደህና እውቀት አለው የሚባል በጣም ጥቂት ነው። ስንት ናቸው፥ ገና በህፃንነታቸው እግዚአብሔርን እንዲያፈቅሩ ህይወታቸውንም ለእርሱ እንዲሰጡ የተመከሩ ! ለሰው ልጆች ማገልገልን ከፍተኛው የኑሮአቸው አላማ ያደረጉ፥ ለጠቅላላው ጥቅም እንዲውል ኃይላቸውን ያዳበሩ ስንት ናቸው! በእርግጥ እነዚህ ናቸው የመልካም ትምህርት ተፈላጊ ነገሮች። በሂሳብ ፥ በሰዋሰው ፥ በጆግራፊና በቋንቋ ጥናት ወዘተ አእምሮን ማጨቅ የተከበሩና ጠቃሚ ሰዎችን ለማስገኘት የሚሰጡት አገልግሎት የተወሰነ ነው።
የበለጠ ለማወቅ ፡ www.bahai.org
Interesting blog? Like it on Facebook, +1 on Google, Tweet it or share this article on other bookmarking websites.