ቡድሃ የተወለደው በሂማልያ ግዛት ከንጉሳዊ ቤተሰብ ነበር፡፤ ቡድሃ ሕፃን ልጅ እያ አሲ የተባለ አንድ አዋቂ ቤተመንግስቱን ጎበኘ፡፡ አሲ ለእግዚአብሔር ያደረ ሰው ነበር፡፡ ቡድሃ ሲያድግ የሰው ልጆች መድህን ይሆናል ሲል ለቡድሃ አባት ጥሩ ወሬ ነገረው፡፡
ያን ጊዜ ቡድሃ ልዑል ጉተማ ተብሎ ይጠራ ነበር፡፡ የቡድሃም አባት ለልጁ ኑሮ አስፈላጊ የሆኑትን አስደሳች ነገሮች ሁሉ ያደርግለት ነበር፡፡ የቡድሃ አባት ልጁን ጥሩ ንጉሥ ሊያደርገው ያስብ ነበር፡፡ ቡድሃ ግን ምድራዊ ደስታ ብቻውን ለኑሮ ምቾት በቂ ምክንያት አለመሆኑን ተረዳ፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ቡድሃ ከቤተመንግስቱ ውጭ አንድ አረጋዊ ሰው አየ፡፡ ቀጥሎም አንድ ሌላ የታመመ ሽማግሌ ተመለከተ፡፡ እንደገናም አንድ የሞተ ሰው አየ፡፡ በዚህም የሰው ልጆች ሁሉ በሞትና በስቃይ ቀንበር ተጠምደው እንደሚኖሩ ተገነዘበ፡፡ ስለዚህ ለሰው ልጆች እውነተኛ ደስታ ማለት መንፈሳዊ ደስታ ብቻ እንደሆነ አወቀ፡፡ ይህንኑ መንፈሳዊ ደስታን ለመሻት ሲል ቤቱን ሚስቱንና ልጁን ጥሎ ኮበለለ፡፡ በመጀመሪያ ወደ አንድ ጫካ ውስጥ ኮብልሎ ከምግብና ከምቾት ተለይቶ ኖረ፡፡ ይህ በቂ አይደለም ብሎ አሰበ፡፡ ምክንያቱም የሰውነት ሃይል ከደከመ አዕምሮም ይደክማልና፡፡ ቡድሃ የመጀመሪያወን መሎኮታዊ ትዕዛዝ የተቀበለው በህንድ አገር ቦዲሂ በተባለ አንድ ዛፍ ስር ነበር፡፡ ከዚያ ቀን ጀምሮ የሰው ልጅን የማዳን ተልዕኮውን ቀጠለ፡፡ የሰዎች ልጆች ነፍሳቸውንና አዕምሮዎቻቸውን እንዲያነጹ ነገራቸው ፡፡ ስስትና አለመታመን እንዲቀሩ አስተማረ፡፡ ይህ ዓለም ለዘለዓለማዊው ደስታ ራሳቸውን የሚያዘጋጁበት አለም መሆኑን መገንዘብ እንዳለባቸው አሳወቀ፡፡
ቡድሃ በተቀደሰው ሕይወቱ ለኛ አርአያ ሆነ፡፡ ቡድሃ በአንድ ዛፍ ስር በፀሎት ተመስጦ በተቀመጠበት ጊዜ ማራ የተባለ እርኩስ መንፈስ የዓለምን ሀብትና ደስታ እሰጥሃለሁ በማለት ሊያሳስተው ሞከረ፡፡ ቡድሃ ግን የሰይጣንን ሃይል ድል ነሳው፡፡ የእርሱ ሃይል መንፈሳዊ ሃይል ነበር፡፡
በቡድሃ አስገራሚ ትምህርት አማካኝነት በሚሊዮን የሚቆጠሩ የዓለም ሕዝቦች መንፈሳዊ ደህንነትን አግኝተዋል፡፡
በቡድሃ ዘመን ያገሩ ሰዎች በእግዚአብሔር ስም ጦርነት ያደርጉ ነበር፡፡ የተለያዩ የየራሳቸው አማልክቶች ነበሯቸው፡፡ ወደ እግዚአብሔር የሚወስደው መንገድ በእግዚአበሔር ምስክሮች በኩል ብቻ መሆኑን ቡድሃ ያውቅ ነበር፡፡ ቡድሃም የእግዚአብሔር ምስክር በመሆኑና እግዚአብሔርንም ማወቅ የሚቻለው በእርሱ በኩል ስለሆነ ያገሩ ሰዎች በእግዚአብሔር ስም የሚያደርጉትን አልደገፈም፡፡ ቡድሃ ብልህ አስተማሪ ነበር፡፡ በሕዝቡ መካከል የነበረውን ጠብ ለማብረድ ሲል ብዙ ጊዜ ስለእግዚአብሔር አያወራም ነበር፡፡ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ምስክር ለሆነው እርሱ እንዲታዘዙ ይነግራቸው ነበር፡፡ በዚህ ዓይነት ዘዴ በዘርና በሃይማኖት የተለያዩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕዝቦች አንድነትና ህብረትን እንዲመሠርቱ ረድቷል፡፡ ቡዳሃ እንዲህ ሲል ተናግሯል፡፡ ‹አንድ ሰው ከእናቱ ማሕፀን ሲወጣ ጻድቅ ወይም እርኩስ ሆኖ አይወጣም፡፡ ጻድቅ ወይም እርኩስ የሚያሰኘው ከተወለደ በኋላ የሚሠራው ሥራ ብቻ ነው፡፡
ቡድሃ ከዚች ዓለም በሞት ከመለየቱ ጥቂት ቀደም ብሎ ዓላማውን ከሱ ጋር አብሮ ይቀበራል ብለው ሲሰጉ ለነበሩት ተከታዮቹ እንዲህ ሲል ተናግሯል፡፡
‹እኔ ወደዚች ዓለም ለመምጣት የመጀመሪያወ ቡድሃ አይደለሁም፣ የመጨረሻውም አልሆንም፡፡ በጥበቡና በዕውቀቱ በአመራሩና በማስተማሩ የሚደነቅ የመልዓክት ሁሉ አለቃ የሆነ ሌላ ቡድሃ በጊዜው ይመጣል፡፡ እሱም እኔ ላደረኩላችሁም ሁሉ የእውነት ትምህርት ምስክር ይሆናል፡፡ እሱም ይህንን ገናና ሃይማኖት ይሰብካል፡፡ እኔ ሳውጀው የነበርሁትን መንፈሳዊ ህይወት እሱም ያውጃል፡፡ የእኔ ደቀመዛሙርት በብዙ መቶ ብቻ የሚቆጠሩ ሲሆኑ የሱ ግን በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ይሆናሉ፡፡›
ቡዲስቶችም በዚህ ቃልኪዳን ያገኙት ተስፋ ከቡድሃ ሞት በኋላ ብቻቸውን የማይቀሩ መሆናቸውንና ሌላ ገናና ቡድሃ በዘለዓለማዊ ቤቱ ውስጥ በደስታ ይዋኛል፡፡ ምክንያቱም ቃል ኪዳኑ በባሃኦለህ ተፈጽሟልና፡፡
Interesting blog? Like it on Facebook, +1 on Google, Tweet it or share this article on other bookmarking websites.