የኢየሱስ ክርስቶስ ታሪክ በጣም ውብ የሆነ ነው፡፡ የእግዚአብሔርና የሰው ልጀች ፍቅር ታሪክ ነው፡፡ የእግዚአብሔር መልዕክተኛ ታሪክ ነው፡ ክርስቶስ ራሱን ከመግለጹ በፈት አንድ ዮሐንስ መጥምቁ የተባለ ቅዱስ ሰው ይኖር ነበር፡፤ በቡድሃ ታሪክ ውስጥ አንደ ቅዱስ ሰው ለሰው ልጆች መድህን የሚሆን አምላክ መምጣቱን እንደተናገረ አይተናል፡፡ ከክርስቶስም መገለጽ አስቀድሞ ይህንኑ የመሰለ ታሪክ ተፈጸመ፡፡ የእግዚአብሔር መልዕክተኛ መጥቶ የሰውን ልጆች ከመከራ እንደሚያድናቸው ዮሐንስ መጥምቁ ተናግሮ ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ የነበሩት ሰዎች ግን ሃሳባቸውን ለመለወጥ አልፈለጉም ነበር፡፡ ከነርሱ በፊት የነበሩት አባቶቻቸው ሲያደርጉ የነበረውን ለመከተል ፈለጉ፡፡ ሕዝቡን ይመሩ የነበሩት ካህናት የእግዚአብሔርን መልዕክተኛ መምጣቱን አልወደዱም ነበር፡፡ ምክንያቱም የእርሱ መምጣት የእነርሱን ክብር የሚያሳጣቸው ስለመሰላቸው ነበር፡፡ ስለዚህ ዮሐንስ መጥምቁን አሰሩትና ራሱን ቀሉት፡፡ ሕይወቱን ለእግዚአብሔር እምነት በመሰዋቱ ዮሐንስ ግን ተደስቶ ነበር፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደው በአንዲት ትንሽ ጎጆ ውስጥ ነበር፡፡ የክርሰቶስ አባት ነው ተብሎ የሚታመነው ዮሴፍ ነበር፡፡ ክርስቶስ የተወለደው በቅድስት አገር እስራኤል ነበር፡፡ የክርስቶስ ቅንነትና ደግነት የተጀመረው ገና በሕፃንነቱ በ‹አባቱ› ቤት ውስጥ በአናጢነት በሚሠራበት ጊዜ ነበር፡፡ ጎልማሳ በሆነ ጊዜ ‹ የሰማይ አባቴን ሥራ መከተል የሚገባኝ ጊዜ አሁን ደርሷል› ሲል ተናገረ፡፡
ለብዙ ቀናት የህሊና ፀሎት ሊያደርግ ወጥቶ ሲመለስ እውነተኛ መልዕክቱን ለሕዝቡ ገለፀ፡፡ ስለ እግዚአብሔር መንግስት ምስክርነቱን ሰጠ፡፡ አንድ ጊዜ ወደ አንድ የተቀደሰ ስፍራ ሄዶ ነበር፡፡ ይህም ስፍራ የምናኔና የብቅአት ስፍራ ነበር፡፡ ሆኖም ስፍራውን ወደመግባቢያ ስፍራ ለውጠውታል፡፡ ክርስቶስም ሱቃቸውን አፈራርሶ አባረራቸው፡ ‹ይኽ የእግዚአብሔር ቤት ነው፡፡ በምድራዊ ፍላጎቶቻችሁ አትበክሉት፡፡› አላቸው፡፡ የእግዚአብሔር ሃይማኖት የሥጋዊ ፍላጎት ማርኪያ መሣሪያ እንዳልሆነ ነገራቸው፡፡
በክርስቶስ ጊዜ መንፈሳዊ ሕመም የታመሙና መንፈሳዊ ሞት የሞቱ አያሌ ሰዎች ነበሩ፡፡ ክርስቶስም በእግዚአብሔር ሃይል የታመሙትን አዳነ፣ የሞቱትንም አነሳ፡፡ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ተወዳጅና የታወቀ ሆነ፡፡ ካህናቱ ግን ቀኑበት፡፡ ተከታዮቻቸውንም አዲስ የሕይወት መንገድ የሚሰብከው በክርስቶስ እንዳይማረኩ አስጠነቋቋቸው፡፡ ክርስቶስ ለካህናቱ መንፈሳዊ ንጉሣቸው መሆኑን በነገራቸው ጊዜ በጣም ተቆጡ፡፡ እነርሱ ያሰቡት ንጉሥ ምድራዊ ታላቅነት ያለው እንደ ክርስቶስ ያለ ሰማያዊ ፀጋ የተጎናፀፈ አልነበረም፡፡ ሆኖም የእስራኤል ንጉሥ መሆኑን አወጀ፡፡ ‹እና እውነተኛ ንጉሣችሁ ነኝ፣ እኔ የአዲሱ መንግስት ጌታ ነኝ፡፡ ዘለዓለማዊነት ካለው ከሰማያዊው መንግሥት ጋር ሲወዳደር ምድራዊ መንግስታት ኢምንት ናቸወ፡፡› ሲል ተናገረ፡፡ አይሁዶች ግን አላመኑትም ነበር፡፡ በክርስቶስ ላይ ተነሱበት፡፡ ከሁለት ሌቦች ጋርም ሰቀሉት፡፡ ተሰቅሎ በነበረበት ጊዜ እንኳን ክርስቶስ ለጠላቶቹ ይቅርታ እንዲያደርግላቸው ወደ እግዚአብሔር ፀለየ፡፡
አይሁዶች የቅዱስ መጽሐፋቸውን እውነተኛ ትርጉም አልተረዱም፡፡ የእግዚአብሔርን መልዕክተኛ በሥጋ ቢገድሉትም ነፍሱ አለመሞቷንና ደምፁም በምድር ዙሪያ መሰማቱን አላስተዋሉም ነበር፡፡
ክርስቶስ በአረገ ጊዜ በርሱ ያመኑት ከተራው ሕዝብ ወገን ነበሩ፡፡ እነዚህ ሰዎች በክርስቶስ ቃል ከድንቁርና መቃብር ውስጥ ወጥተው አዲስ መንፈሳዊ ህይወት አግኝተው ነበር፡፡ ምንም እንኳን የቀድሞዎቹ የክርስቶስ ደቀ መዝሙሮች ዓሣ አጥማጆች፣ ተራ ፀሐፊዎችና ገበሬዎች ቢሆኑም በእርሱ ትምህርት አዲስ ሃይል አግኝተው ነበር፡፡ በኋላም በዓለም ዙሪያ ተሰራጭተው የክርስቶስን ትምህርት አሰራጩ፡፡ አብዛኛዎቹም በዚሁ ሳቢያ ሕይወታቸውን ሰውተዋል፡፡ ችግርንና መከራን ከምንም ሳይቆጥሩ የእግዚአብሔር መንግሥት በክርስቶስ አማካኝነት በምድር ላይ መመሥረቱን አስተጋቡ፡፡ አሣ አጥማጆችና ገበሬዎች ቢሆኑም የመላውን ዓለም ኃይል ተቋቋሙት፡፡ የተነሱባቸውን ሁሉ በእግዚአብሔር ቃል ድል እየመቱ ለተከታዮቻቸው አዲስ መንፈሳዊ ሕይወት ሰጡ፡፡ ይህም የክርስቶስ መለኮታዊ ኃይል ነበር፡፡
ክርስቶስ ይህንን ዓለም ከመተው በፊት ክርሽናና ሙሴ እንደተናገሩት ተመልሶ እንደሚመጣ ለሕዝቡ አረጋግጦ ነበር፡፡ በጊዜው ለነበሩት ሰዎች ብዙ የሚነግራቸው ነገር እንዳለ ነገረቸው፡፡ ግን ሊገባቸው እንደማይችል ገለጸላቸው፡፡ ሆኖም ሌላ ታላቅ የእግዚአብሔር መልክተኛ እንደሚመጣና ስለ እግዚአብሔር ና ስለሃይማኖት በበለጠ ሁኔታ እንደሚያስተምራቸው ቃል ገባላቸው፡፡
ባሃኢዎች ለክርስቲያን ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው የክርስቶስን እንደገና የመምጣቱን ጥሩ ወሬ ይነግሩዋቸዋል፡፡ ለክርስቲያን ሃይማኖት መሪዎች ባሃኦላህ እንዲህ ሲል ተናግሯል፡፡ ‹እውነት እውነት እላችኋለሁ፡፡ ታላቁ አባት መጥቶ በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ የተሰጣችሁን ቃልኪዳን ፈጽሟል፡፡››
የክርስቶስ ዳግመኛ መመለስ
ክርስቶስ ወደፊት ስለሚመጣ ክስተተ እግዚአብሔር የተናገረው ብዙውን ጊዜ በሦስተኛ ሰው ነው። ሆኖም አንዳንድ ጊዜ በአንደኛ ሰው ተናግሯል። እንዲህ ይላል፦ “... እሄዳለሁ ቦታ አዘጋጅላችሁ ዘንድ በሄድኩበትም ቦታ ባዘጋጀሁላችሁ ጊዜ ደግሞ እመጣለሁ ወደኔም እወስዳችኋለሁ። እኔ ወዳለሁበት እላንትም ዳግም ትሆኑ ዘንድ።” (ዮሐ. 14. 2-3) በሐወርያት ሥራ በመጀመሪያው ምዕራፍ ኢየሱስ ባረገ ጊዜ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ እንደተነገራቸው እናነባለን፤ “ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት እንዲሁ ይመጣል” በዚህና ይህን በመሳሰሉት አባባል ምክንያት ብዙ ክርስቲያኖች “የሰው ልጅ በደመና ተሸፍኖ በታላቅ ክብር” ሲመጣ የዛሬ ሁለት ሺህ ዓመታት በኢየሩሳሌም መንገዶች ሲመላለስ የነበረውን፥ ደሙ የፈሰሰውንና በመስቀል ላይ የተሰቃየውን ያንኑ ኢየሱስን በአካል እናየዋለን ብለው ይጠባበቃሉ። በምስማር የተቸነከሩትን እጆቹንና እግሮቹን በጣታቸው ለመጠንቆልና በጦር የቆሰለውን ጎኑን በእጃቸው ለመዳሰስ ያስባሉ።
ሆኖም በእውነት የክርስቶስን ቃላት ትንሽ አስተውለን ብንመረምር እንደዚህ ያለው አስተያየት ሊወገድልን ይችላል። በክርስቶስ ዘመን የነበሩት አይሁዶች ስለኤልያስ መመለስ ተመሳሳይ አስተያየት ነበራቸው። ሆኖም ኢየሱስ “ኤልያስ አስቀድሞ መምጣት አለበት” የሚለው ትንቢት የቀድሞው ኤልያስ በአካል መመለስ ሳይሆን “የኤልያስን መንፈስና ኃይል” ይዞ በመጣው በዮሐንስ መጥምቁ ተፈጽሟል ሲል ስህተታቸውን አብራርቶላቸዋል። ክርስቶስ እንዲህ አለ፤ “ትቀበሉት
ዘንድም ትሹ እንደሆነ እርሱ ኤልያስ ነው ይመጣ ዘንድ ያለው። ሰሚ ጆሮ ያለው ይስማ”። ስለዚህ የኤልያስ “መመለስ” ማለት አንድ የእግዚአብሔር መንፈስና ኃይል ያደረበት ከሌላ ቤተሰብ የተወለደ የሌላ ሰው መመለስ ማለት ነው። በተመሳሳይ ሁኔታ በእነዚህ በኢየሱስ ቃላቶች መሠረት የክርስቶስ መምጣት ማለት ከሌላ እናት የተወለደ፥ የእግዚአብሔር መንፈስና ኃይል ያደረበት የሌላ ሰው መገለጽ መሆኑን ልንረዳ እንችላለን። የክርስቶስ “እንደገና መመለስ” በባብ መገለጽና በራሱም መምጣት የተፈጸመ መሆኑን ባሃኦላህ ያስረዳል። እንዲህ ይላል፦
“ፀሐይን አስተውሉ ‘የትላንቱ ፀሐይ ነኝ’ ብትል እውነት ነው። እንደዚሁም የጊዜን ተለዋዋጭነት በመገንዘብ ከዚያኛው ፀሐይ የተለየሁ ነኝ ብላ ብትናገር እውነቷን ነው። እንደዚሁም ቀናት በሙሉ አንድ ናቸው ቢባል ትክክልና እውነት ነው። ደግሞም ስማቸውና ለእያንዳንዱ የተሰጠው መለያ ቢኖር የተለያዩ ናቸው ቢባል ይህም እውነት ነው። ምንም እንኳን አንድ ናቸው ቢባል እያንዳንዱ የራሱ መለያ ፥ የተለየ ስጦታና የተወሰነ ባሕርይ ይታይበታል። እንደዚሁም በስሞችና በባሕርይዎች ፈጣሪ ስለአንድነትና ስለልዩነት ምስጢር የተገለጸውንና ያ የዘለዓለማዊው ውበት በልዩ ልዩ ጊዜያት ለምን በተለያየ ስምና ማዕረግ ራሱን እንደሚጠራ ለጠየቃችሁት ጥያቄ መልስ ታገኙ ዘንድ ልዩ ልዩ የእግዚአብሔር መልእክተኞች የሚለያዩበትንና የሚመሳሰሉበትን መረዳት አለባችሁ።” (ኢቃን ገጽ 21-2)
አብዱል-ባሃ እንዲህ ይላል፦
“የክርስቶስ ዳግመኛ መምጣት ሰዎች እንደሚያምኑት ሳይሆን ከእርሱ በኋላ የመጣል ተብሎ ተስፋ ስለተሰጠው ነቢይ ነው። ከእግዚአብሔር መንግሥትና ዓለምን ከከበበው ሥልጣኑ ጋር ይመጣል። ብታውቁት ኖሮ ምድራዊው ዓለም በጌታ ፊት እንደአንዷ የዝንብ ክንፍ እንኳን ስለማይቆጠር ይህ መንግሥት በልቦችና በመንፈሶች ዓለም እንጂ በምድራዊ ዓለም አይደለም! ‘ክርስቶስ’ ማለት መጀመሪያና መጨረሻ የሌለው መለኮታዊ እውን፥ ፍጹም ባሕርይና ሰማይዊው ሕያውነት ማለት ስለሆነ በእርግጥ ክርስቶስ መጀመሪያ ከሌለው ከመጀመሪያው መንግሥቱ ጋር መጥቷል። ለዘለዓለም ዓለምም ከመንግሥቱ ጋር ይመጣል። በየአንዳንዱ ደት ይታያል፤ ይነሣል፤ ይገለጻል፤ ይጠልቃል።” (ታብሌትስ ኦፍ አብዱል-ባሃ ቮል. 1 ገጽ 138)
በነዚህ ሁለት ጥቅሶች ክርስቶስ በማያሻማ ቃላት የሰው ልጅ ከመምጣቱ አስቀድሞ መፈጸም ስለሚገባቸው ነገሮች ተንብየዋል። ክርስቶስ እነዚህን ቃላት ከተናገረ ጀምሮ ባለፉት ክፍለ ዘመናት እነዚህ ምልክቶች እያንዳንዳቸው ተፈጽመዋል። በእያንዳንዱ ምንባብ የአይሁዶችን የግዞት ዘመን ፍጻሜና የእየሩሳሌምን እንደገና መገንባትና የጌታ ወንጌል በመላ ዓለም መሰበክ ይናገራል። እነዚህ ምልክቶች ሁለቱም በዘመናችን ቃል በቃል ተፈጽመው ማየታችን በጣም የሚያስደንቅ ነው። እነዚህ የትንቢቱ ክፍሎች እንደቀሩት ሁሉ እውነት ከሆኑ የምንኖረው ክርስቶስ በተነበየለት “በፍጻሜ ዘመን” ነው ማለት ነው
Interesting blog? Like it on Facebook, +1 on Google, Tweet it or share this article on other bookmarking websites.