የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
  • የባሃኢ ትምህርቶች
    • አምላክና ሐይማኖቶች
    • የአምላክ መልእክተኞች
    • የባሃኢ ትምህርቶች
    • ህግጋቶችና ደንቦች
    • አስተዳደር
  • ማህበረሰባዊ ተሳትፎ
    • ማህበረሰብ ግንባታ
    • የወጣቶች እንቅስቃሴ
  • የባሃኢ ማህበረሰብ
    • የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
    • የአለም ዓቀፍ ማህበረሰብ
    • የባሃኢ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ - አዲስ አበባ ጽ / ቤት
    • ባሃኢዎችን እናስተዋውቃችሁ
  • የባሃኢ መጽሐፍት
    • ቅዱሳን ጽሑፎች
    • ሌሎች
  • ለበለጠ መረጃ
    • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች
    • መልእክት ይላኩልን
    • ቪዲዮዎች
  • ENGLISH

ዞሮአስተር


የመለኮታዊ የመርሆ ብርሃን በሰው ልጆች ልብ መቅረዝ ሁሌም እንደበራ ነው፡፡ ደጉ ፈጣሪያችን በፍቅሩና ምህረቱ፣ በጨለማ ውስጥ አልተወንም ወደፊትም ቢሆን አይተወንም፡፡

ዞሮአስተር ትልቅ ስፋት ያለውን የምዕራብ ኤሲያ ህዝቦችን ከአስተማሩት አንጸባራቂ መብራቶች አንዱ ነው፡፡ ልክ እንደ ክሪሽና፣ ቡድኃና ሙሴ ምዕተ ዓመታትን የዘለቀ ስልጣኔ መስርቷል፡፡በህንድ ውስጥ ጥቂት ሆኖም ግን እግዚሃብሔርን አፍቃሪዎችና የሰለጠኑ የዞራስተር ተከታዮች ማህበረሰብ አሁንም አለ፡፡

ታሪክ እንደሚያወሳው አሁን ኢራን ተብላ በምትጠራው አገር በሰሜን ምዕራብ ክልሏ ተወለደ፡፡ ወላጆቹ ከመሣፍንት ወገኖች ሲሆኑ ከሚያምር ሐይቅ አጠገብ በነበረው ቤቱ ሁሉም ነገር የተሟላለት ነበር፡፡ ከቀሰመው መጠነኛ የዘመኑ ትምህርት ውጪ ዞራስተር ግብርናን ተምሯል፡፡ በልጅነቱ እንደ ቡድሃ ይህ ጊዜያዊ የሆነው ምድራዊ ህይወታችን በራሱ አጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ተረድቶ ነበር፡፡ ስለዚህ እውነትን ፍለጋ የቤቱን ምቾት ትቶ አንድ ትልቅ ተራራ ላይ ያለ ዋሻ ውስጥ ለጸሎትና ሱባዔ ገባ፡፡ ከአስር አመታት በኋላ፣ ገና ሰላሳ ዓመቱ እያለ ከታላቁ ህያው፣ አሁራማዝዳ፣ መልዕክት አምጪ የመሆኑን አስደሳች ዜና ይዞ ተመለሰ፡፡ ዘላለማዊ ህይወት እንደሚጠብቀን አብሳሪ መልዕክቱን ሰጠን፡፡ የመልካም ሀሳብ፣ የመልካም ምግባርና የመልካም ንግግርን፣ ሶስቱን መማሪያዎችን እንዲታዘዙ ህዝቡን ጋበዛቸው፡፡ መልካምነትና ክፋት በቋሚነት በውጊያ ላይ እንደሆኑና የመልካምነት ውስጣዊ ማንነቱ የሆነው አሁራማዝዳ በስተመጨረሻው እርኩሱን አሂርማንን እንደሚያጠፋው አስተማረ፡፡ የሰዎችን ዕለት ተዕለት ኑሮን የተመለከቱ ትምህርቶችን አምጥቷል እንዲሁም የሰውነት፣ የነፍስና የቤት ንጽህና ላይ አጽንኦትም ሰጥቷል፡፡

ዞሮአስተር፣ ከእሱ በፊትም ሆነ በኋላ እንደመጡት የእግዚአብሔር መልዕክተኞች ሁሉ፣ የእርሱ ህዝቦች ክደውታል፡፡ አቬስታ በሚበላው ከቅዱስ መጽሀፍቶቹ አንዱ በሆነው እንዲህ ሲል ተቃውሟቸዋል ‹የት መሄድ እችላለሁ? መሪዎቹና መሳፍንቶቹ እያወገዙኝ ነው፡፡ ገበሬዎቹ እንኳን ሳይቀሩ ተነስተውብኛል፡፡ እንዴት በውሸት የተሸበቡ ሆኖው ህዝባችንን በሚመሩት  ደስተኛ ልሆን እችላለሁ? ኦ ማዝዳ እንዴት አንተንስ አስደስትሃለሁ?›

በተጨማሪም ዘመዶቹ ስላገለሉትና ህዝቡም ስላሳደዱትና ስለጎዱት በጣም አዘነ፡፡ ስለዚህ ቤቱን ትቶ ወደ ምስራቅ ወደ ባለክ በመሄድ ለአገሩ ንጉስ ተልዕኮውን አወጀለት፡፡ እንደሚጠበቀው እዚያም ያሉ ህዝቦች አዲስ ሃይማኖት ለመቀበል ፍላጎት አልነበራቸውም፡፡ ያሉበትን አስተሳሰብና ልማድን ማራመድን በመምረጥ ብርሃኑን ከማየት ይልቅ ጨለማ ውስት ለመቆየት መረጡ፡፡ ሆኖም ግን ንጉሱ በዚህ ሰው ጀግንነትና ቅንነት ተደንቆ ነበር፡፡ የቤተመንግስቱ አዋቂዎቸና መሣፍንቶች በህዝቡ ፊት ለሚካሄድ የክርክር መድረክ እንዲዘጋጁ አዘዘ፡፡ ክርክሩም የዞሮአስተር ኃይል ከራሱ ሳይሆን ከሁሉን ቻዩ አምላክ የታደለው እንደሆነ ክርክሩን ለታደሙት በሙሉ ግልጽ አደረገ፡፡ ከዚያም በኋላ ንጉሱና ህዝቡ ራሳቸውን ለአሁራማዝዳ አስገዙ፣ አዲስ እምነትም ብቅ አለ፡፡

በአጎራባች አገሮች የሚኖሩ ህዝቦች መልካምነት በባልክ ተመስርታ እነሱ የሚመሩትን የእርኩስ ህይወት ሊያጠፋው እንደሆነ ስለተረዱ ሰጉ፡፡ ታላቅ ጦር በማደራጀት የኢራንን መንግስት ወጉ፡፡ ዞሮአስተር በቤተመቅደስ ውስጥ እየጸለየ እያለ ተይዞ በአንድ ወታደር ሰይፍ ተወግቶ በ77 ዓመቱ ህይወቱ አለፈ፡፡ በዚህ ሁኔታ የእውነት አመጪው ህይወት አለፈ፣ ተልዕኮው ግን ዘላለማዊ ነው፡፡

ዞሮአስተር የእጅግ ታላቁ መንፈስ የማይጠፋ ዘላለማዊ እሳት ነው፡፡ በአፈ ታሪክ እንደሚወሳው በንጉሱ እልፊኝ ባደረገው ክርክር እሳት ከእጆቹ ወጥቶ፣ ሰውነቱን ሳያቃጥለው፣ ብርሃንና ሙቀት ያፈልቅ ነበር፡፡ ይህም የኃይሉ ተምሳሌት እንጂ ቃል በቃል መወሰድ የሌለበት ነው፡፡ በመልዕክተኛው የሚለኮሰው የእግዚአብሔር ፍቅር እሳት ዘላለማዊና ሊዳፈን የማይችል ነው፡፡ ይህ እሳት የሰው ዘርን የሚመራ  ሲሆን እነሱን ከማቃጠልና ከማጥፋት ይልቅ ሙቀትና ደስታን ለነፍሳቸው የሚቸራቸው ነው፡፡ እንደ እጅግ ታላቁ መንፈስ ዘላለማዊ እሳት ተምሳልትነቱ ዞራስተሪያዊያኖች በቤተመቅደሶቻቸው ውስጥ እሳት ሁሌም ያቀጣጥላሉ፤ በዚህም ምክንያት ሰዎች እሳት አምላኪዎች ናቸው የሚል የተሳሳተ አመለካከት አላቸው፡፡

ዞሮአስተር ተልዕኮውን መወጣት ብቻ ሳይሆን ጊዜው ሲደርስ የአለም አዳኝ የሆነ፣ ሱሺያንት ወይም ሻህ ባህራም የተባለ መልዕክተኛ እንደሚመጣና እርኩስ መንፈስን ድል እንደሚነሳ የምስራቹን አብስሯቸዋል፡፡ እንዲሁም አሂማን ድል ከመነሳቱ በፊት የ3060 አመታት የግጭት ዓመታት እንደሚያልፉና የመባረክና የሰላም ዘመን ዓለም ላይ እንደሚመጣ ጊዜውን ትንቢት ተናግሯል፡፡ ይህ ቀን ባሃኦላህ የሁሉም ያለፉት ነቢያት ትንቢት ማሟላቱን ካወጀበት ጊዜ ጋር ይገጣጠማል፡፡   

Interesting blog? Like it on Facebook, +1 on Google, Tweet it or share this article on other bookmarking websites.

  • Follow via Facebook
  • Follow via Youtube

የእግዚአብሔር ክስተቶች

  • ሙሴ
  • ቡድሃ
  • ባሃኡላህ (ክብረ-አምላክ)
  • ባብ
  • ነብዩ መሐመድ
  • እየሱስ ክርስቶስ
  • ክርሽና
  • ዞሮአስተር
Manifestation

© 2023 የኢትዮጵያ ባሃኢዎች

Go Top