ክሪሽና የእግዚአብሔር መልክተኛ ነበር፡፡ መልዕክቱም የፍቅር መልዕክት ነበር፡፡ እሱም የተወለደው በእስር ቤት ነበር፡፡ ይህም እያንዳንዳችን በራሳችንና በዓለም እስር ቤት ውስጥ የተወለድን ለመሆናችን ምልክት ነው፡ ክሪሽና ከእስር ቤት በተአምር አመለጠ፡፡ እኛም የደህንነትን መንገድ ከተከተልን ከራሳችን እስር ቤት ለማምለጥ እንችላለን፡፡
እንደሌሎቹ የእግዚአብሔር ምስክሮች ሁሉ ክሪሽናንም ርኩሳን ሃይሎች አጋጥመውት ነበር፡፡ ከነዚህም ርኩሳን ሃይሎች ጋር ተዋጋ፣ ድል ነሳቸውም፡፡ ርኩሳን ሃይሎች ለጊዜው ቢያደሉም በመጨረሻ ግን ድሉ የእውነት ነው፡፡
ክሪሽና የድዎርካ ንጉሥ ሆነ፡፡ ድዎርካ ማለትም ጠባቧ በር ማለት ነው፡፡ ክሪሽና የእግዚአብሔር ዕውቀት በር ነበር፡፡ ትምህርቱ ሁሉ ስለሰው በጎነት ነበር፡፡ ግን የሰው ልጆች ግን አልተቀበሉትም፡፡ ሕዝቡ ትምህርቱንና ዓላማውን ስላልተረዳለት ክሪሽና በጣም አዘነ፡፡
ሕዝቡ ያላመነበት ክሪሽና በሰው አምሳል ስለመጣ በመሆኑ በጣም ተበሳጨ፡፡ ስለ እግዚአብሔርና ስለምስክሮቹ ሕዝቡ የራሱ የሆነ የተለየ አስተሳሰብ ነበረው፡፡ ስለዚህ ክሪሽና ሕግዚአብሔርን መወከሉ በሕዝቡ ተቀባይነትን አላገኘም፡፡ ክሪሽና በጊታ ውስጥ የሚከተለውን ይናገራል፡፡
‹ከፍተኛ ፍጥረቴን ሳይመረምሩና የህልውና አምላክ መሆኔን ሳያውቁ ሥጋ ለብሼ በማየታቸው ብቻ የተታለሉት ይንቁኛል፡፡ (ጊታ 9፣ 11)
ተወዳጁ ደቀመዝሙር አርጁና እንኳን የክሪሽናን መለኮታዊ ኃይል አልተረዳም ነበር፡፡ የሰው ልጅ ቤተ መቅደስ የአምላክ መቀመጫ ሲሆን መቻሉን መረዳት ለአርጁና ተስኖት ነበር፡፡ አርጁና መለኮታው ሃይሉን እንዲገነዘብና እንዲያምንበት ክሪሽና ወደ አምላክነት መለወጥ አለበት ያሉ ነበር፡፡
ይህም ማለት አርጁና በእግዚአብሔር ከማመኑ በፊት የክሪሽናን መንፈስ ታላቅነትና ክብር እንዲገነዘብ ክሪሽና ረዳው፡፡ አርጁና ለእግዚአብሔር ለመታዘዝ ፊቱን በመለሰ ጊዜ የክረክሼትራ ጦርነት የተለየ መለክ ያዘ፡፡
ይህም ጦርነት በበጎነትና በክፋት መካከል መሆኑን ታውቃላችሁ፡፡ ጦርተነቱን የጀመሩት የፓነዳቫስ ወገን የሆኑ ኮቫሶች ነበሩ፡፤ አፓነዳቫስ ወገን ሃይለኛ የነበረው አርጁና እየተመራ ከጨላማ ጦር ሠራዊት ውጊያ ገጠሙ፡፡ ክሪሽና የአርጁና ሠረገላዎች አዛዥ ነበር፡፡ አርጁና ግን ወገኖቹን ለመውጋት አልፈለገም ነበር፡፡ ተወዳጅ አስተማሪውና ወካጆቹ በኮርባስ ጦር ሠራዊት ውስጥ ነበሩ፡፤ አርጆና ለመሟገት ሞከረ፣ ሃይለኛ ጎራዴውንም ወደ ……… መለሰ፡፡ ክሪሽና ግን አርጁና ለእግዚአብሔር እንዲገዛና እግዚአብሔርንም እንዲከተለው ጠየቀው፡፡
የእግዚአብሔር ምስክርነት ካወቅን በሱም ካመንን ትዕዛዛቱን ሁሉ ልናከብር ይገባናል፡፡ ክሪሽና በጊታ ውስጥ የሚከተለውን ያስተምረናል፡፡
‹ሃሳባችሁን ሁሉ ለኔ ብታስገዙ ታላቅነቴን ብትቀበሉና በትክክለኝነትም ሃሳባችሁነ ምንጊዜም በኔ ላይ ጣሉት፡ (ጊታ 18፣ 57)
ክሪሽና የሰላም መኖሪያ ነበር፡፡ እኛንም እንደዚሁ ሰው ወደርሱ ይጠራናል፡፡
‹ማንኛውንም ነገር ተው፤ ብቻችሁን እኔ ዘንድ ኑ፡፡ አትዘኑ፣ እኔ ከክፉ ሁሉ እጠብቃችኋለሁና፡፡› (ጊታ 18፣ 66)
የእግዚአብሔር ምስክር የሆነው ክሪሽና አዲስ ሥልጣኔ አመጣ፡፡ የሰውን ልጅ ከክፋትና ከሃዘን ነፃ አወጣ፡፡ ለተከታዮቹም እርሱ ያደረገውን ሁሉ እግዚአብሔር እንደሚመሰክርለት አረጋገጠላቸው፡፡ የዓለምን ዘላን ሕዝቦች ወደ ቀጥተኛ የእግዚአብሔር መንገድ ለመምራት ክሪሽና የሚከተለው ተናገረ፡፡
‹ባር (አርጁና) ሆይ! ትክክለኛነት ወድቆ ሥራውን ለክፋት ሲለቅ ያን ጊዜ ነው እውነትን ለመጠበቅ ክፋትን ለማጥፋትና ትክክለናነትን ለመመሥረት የምመለሰው፡፡ (ጊታ 4፣ 7. 8)
የእግዚአብሔር ቃልኪዳን መፈጸሙን በሚከተሉት ገጾች እንመለከታለን፡፡
Interesting blog? Like it on Facebook, +1 on Google, Tweet it or share this article on other bookmarking websites.