የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
  • የባሃኢ ትምህርቶች
    • አምላክና ሐይማኖቶች
    • የአምላክ መልእክተኞች
    • የባሃኢ ትምህርቶች
    • ህግጋቶችና ደንቦች
    • አስተዳደር
  • ማህበረሰባዊ ተሳትፎ
    • ማህበረሰብ ግንባታ
    • የወጣቶች እንቅስቃሴ
  • የባሃኢ ማህበረሰብ
    • የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
    • የአለም ዓቀፍ ማህበረሰብ
    • የባሃኢ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ - አዲስ አበባ ጽ / ቤት
    • ባሃኢዎችን እናስተዋውቃችሁ
  • የባሃኢ መጽሐፍት
    • ቅዱሳን ጽሑፎች
    • ሌሎች
  • ለበለጠ መረጃ
    • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች
    • መልእክት ይላኩልን
    • ቪዲዮዎች
  • ENGLISH

ሙሴ

በአንድ ሩቅ በሆነ ቦታ በጭቆና ቀንበር ስር የሚኖሩ ባሮች ነበሩ፡፡ ‹የእሥራኤል ልጆቸ‹ ተብለው ይጠሩ የነበሩት እነዚህ ባሮች የታላቁ የግብፅ ንጉሥ አገልጋዮች ነበሩ፡፡ የእነዚህ ሰዎች አገር አሁን እስራኤል በመባል የሚታወቀው ሲሆን ከቤታቸው የተወሰዱት በሃይል በመገደድ ነበር፡፡ ከመከራና ከስቃይ ሊያድናቸው ይችል የነበረው የእግዚአብሔር መልክተኛ ብቻ ነበር፡፡ ስለዚህ ሙሴ እነዚህን ባሮች ነፃ ለማውጣት ተነሣ፡፡ ውሳኔ ብቸኛ ስለነበረ የግብፁ ንጉሥ እሱን ለማጥፋት አያዳግተውም ነበር፡፡ ሆኖም በእግዚአብሔር ሃይል የታደለ ሰው ሲመጣ ሌላ ምድራዊ ሃይል እንደማይቋቋመው ጥርጣሬ የለውም፡፡ ያለአንዳች ረዳት ሙሴ ለወገኖቹ የእግዚአብሔር መንግሥት ሊያወርስ ተነሳ፡፡

ሙሴ የእግዚአብሔር መልዕክተኛ መሆኑን ባወጀ ጊዜ የእስራኤል ልጆች መከራቸውና ስቃያቸው እንዳበቃ አወቁ፡፡ ሙሴንም ተከተሉት፡፡ ወደ ቅድስት አገር ወደ እስራኤል መጥተው አዲስ ህይወት ጀመሩ፡፡ የግብፅ ንጉስ ሃይልና ገናናነት ምንም አልበገራቸውም፡፡ ንጉሡና ወታደሮቹ የእስራኤል ልጆች ወደ አገራቸው እንዳይገቡ ለመከላከል ሲሞክሩ በቀይ ባህር ውስጥ ሰጥመው ቀሩ፡፡

የእግዚአብሔር ቃላት የእስራኤልን ልጆች ህይወት ለወጡ፡፡ ምንም እንኳን ባሮች ቢሆኑም ሀብታም መንግስት መሠረቱ፡፡ ለሰው ልጆችም ታላቅ መምህራን ሆኑ፡፡ የእግዚአብሔር መልክተኛ ደስታን ከማምጣቱ በላይ የዕውቀት ሁሉ ምንጭ ነው፡፡

ሙሴ ትምህርቱን ሁሉ በአስር ሕግጋት አጠቃለለው፡፡ እነዚህም አስደናቂ ሕግጋት ነበሩ፡፡ ሙሴ እግዚአብሔርን እንድንወድ ያስተምረናል፡፡ እንዲሁም ከእግዚአብሔር አስበልጠን ሌላ ነገር እንዳንወድ ይነግረናል፡፡ ወላጆቻችንን እንድንወድና ለእነርሱም እንድንታዘዝ ይነግረናል፡፡ አትስረቁ ይለናል፣ ሌሎችን እንዳንጎዳ ይነግረናል፡፡ ንጹሐንና እውነተኛ ሁኑ ይለናል፡፡ ከነዚህ ትምህርቶች በተጨማሪ ከመከራቸው ነፃ የሚያወጣቸው ሌላ መልዕክተኛ አምላክ እንደሚልክላቸው ለተከታዮቹ ይነግራቸው ነበር፡፡ ይህ ታላቅ ጌታ በመጣም ጊዜ የእስራኤል ልጆች ለብዙ ዓመታት ወደ ተለዩዋት ወደ ቅድስተ ሀገራቸው እንደሚመለሱ ሙሴ ለተከታዮቹ ቃል ገባላቸው፡፡

ጌታ መጥቷል፡፡ ባለፉት መጻሕፍት እንደተነገው ሁሉ የእግዚአብሔር መምጫ ቀን መድረሱን ባሃኦላህ ተናግሯል፡፡ ቃልኪዳኑ የተፈጸመ መሆኑን ለሙሴ ተከታዮች ነገራቸው፡፡ ለብዙ ጊዜ ተለያይተው የነበሩትና በስቃይ አለንጋ የተገረፉት አይሁዶች አሁን በአንድ ላይ ተሰብስበው ወደ ቅድስት አገር ተመልሰዋል፡፡ እሥራኤል ተብሎ የሚጠራ የተለየ አገር ለራሳቸው መስርተዋል፡፤ በሙሴ ቃልኪዳን መሠረት ይህ ሁሉ እግዚአብሔር በፍርድ ዙፋኑ ላይ በተቀመጠ ጊዜ መፈጸም ነበረበት፡፡ በቃል ኪዳኑ መሠረት የእስራኤል ልጆች በቅድስት ሀገር እንዴት እንደተሰበሰቡ ባዩ ጊዜ ብዙ አይሁዶች የእግዚአብሔርን መምጣትን አወቁ፡፡ እግዚአብሔር ባይመጣ ኖሮ የእነርሱ በአንድ ስፍራ መሰብሰብ አዳጋች በሆነም ነበር፡፡

Interesting blog? Like it on Facebook, +1 on Google, Tweet it or share this article on other bookmarking websites.

  • Follow via Facebook
  • Follow via Youtube

የእግዚአብሔር ክስተቶች

  • ሙሴ
  • ቡድሃ
  • ባሃኡላህ (ክብረ-አምላክ)
  • ባብ
  • ነብዩ መሐመድ
  • እየሱስ ክርስቶስ
  • ክርሽና
  • ዞሮአስተር
Manifestation

© 2023 የኢትዮጵያ ባሃኢዎች

Go Top