የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
  • የባሃኢ ትምህርቶች
    • አምላክና ሐይማኖቶች
    • የአምላክ መልእክተኞች
    • የባሃኢ ትምህርቶች
    • ህግጋቶችና ደንቦች
    • አስተዳደር
  • ማህበረሰባዊ ተሳትፎ
    • ማህበረሰብ ግንባታ
    • የወጣቶች እንቅስቃሴ
  • የባሃኢ ማህበረሰብ
    • የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
    • የአለም ዓቀፍ ማህበረሰብ
    • የባሃኢ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ - አዲስ አበባ ጽ / ቤት
    • ባሃኢዎችን እናስተዋውቃችሁ
  • የባሃኢ መጽሐፍት
    • ቅዱሳን ጽሑፎች
    • ሌሎች
  • ለበለጠ መረጃ
    • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች
    • መልእክት ይላኩልን
    • ቪዲዮዎች
  • ENGLISH

የሴቶችና የወንዶች እኩልነት


ባሃኦላህ ታላቅ ደረጃ ከሚሰጣቸው ማኅበራዊ ትምህርቶቹ አንዱ ሴቶች ከወንዶች እኩል መታየት እንዳለባቸው፥ እኩል ሥልጣንና መብት፥ እኩል ትምህርት እና እድል እንዲሰጣቸው የሚለው ነው።የሴቶችን ነፃነት ለማስገኘት ዓይነተኛ መንገድ ይሆናል ብሎ ያመነበት ለጠቅላላው ሰው ትምህርት እንዲዳረስ ማድረግ ነው። ልጃገረዶች እንደ ወንዶች ልጆች ሁሉ መልካም ትምህርት ሊያገኙ ይገባል። እንዲያውም ልጃገረዶች እናቶች በሚሆኑበት ጊዜ የሚመጣው ትውልድ የመጀመሪያ አስተማሪዎች ስለሚሆኑ ከወንዶች የበለጠ ትምህርት ማግኘት ይገባቸዋል። ህፃናት እንደአረንጓዴና እንደለስላሳ ቅርንጫፎች ናቸው። በአፍላ ጊዜያቸው፥ ሥልጠናቸው ልክ ከሆነ ቀጥ ብለው ያድጋሉ። አስተዳደጋቸው ትክክል ካልሆነ ግን ጠማማ ሆነው ያድጋሉ። እስከ ሕይወታቸውም መጨረሻ ድረስ ይኸው የልጅነት አመራራቸውና አስተዳደጋቸው ይከተላቸዋል። ስለዚህ የልጃገረዶች በሥርዓትና በጥበብ መማር በጣም አስፈላጊ ነው!

አብዱል-ባሃ በምዕራብ አገር ጉብኝቱ ጊዜ በዚህ ጉዳይ ላይ የባሃኢን አስተያየት ለመናገር ብዙ አጋጣሚ ምክንያት ነበረው እ.ኤ.አ. በጥር ወር 1913 ዓ.ም. በሎንዶን የሴቶች ነፃነት ድርጅት ስብሰባ ላይ እንዲህ አለ፦

 

“የሰው ዘር እንደባለ ሁለት ክንፎች ወፍ ይመሰላል። አንዱ ክንፍ ወንዱ ሲሆን ሌላው ሴት ነው። ሁለቱም ክንፎች ጠንካራ ካልሆኑና በአንድ ኃይል ካልተመሩ ወፊቱ ወደሰማይ ልትበር አትችልም። በዚህ በአዲሱ ዘመን መንፈስ ሴቶች ወደፊት በመራመድ ስለ ልዩ ልዩ የሕይወት ጉዳዮች ተልዕኳቸውን ከወንዶች እኩል መወጣት አለባቸው። ከወንዶች ጋር በአንድ ደረጃ በመሆን የእኩልነትን መብት መካፈል አለባቸው። ይህ ጥብቅ ጸሎቴ ነው፥ ከባሃኦላህም መሠረታዊ ሕጎች አንዱ ነው።
“አንዳንድ የሳይንስ ሊቃውንት የወንዶች አንጎል ክብደት ከሴቶች አንጎል ይበልጣል ብለው ስለሚያምኑ ይህንኑ እምነት ወንዶች የበላይነት ማስረጃ ምክንያት አድርገውታል። ሆኖም በአካባቢያችን ስንመለከት ብዙ ትናንሽ ጭንቅላት ያላቸው የአንጎላቸውም ክብደት በዚያው መጠን ሊያንስ የሚችል ግን የመረዳትና የማወቅ ችሎታቸው በጣም የላቀ ብዙ ሰዎች እናያለን። ሌሎችም ትልልቅ ጭንቅላት ያላቸው በዚያም መጠን አንጎላቸው ሊከብድ የሚችል፥ ግን የመረዳት ችሎታቸው ዘገምተኛ የሆኑ ሰዎች እናገኛለን። ስለዚ የአንጎል ክብደት መለያየት የእውቀትና የበላይነት ትክክለኛ መለኪያ አይደለም።

 

“ወንዶች ለበላይነታቸው ሁለተኛ መረጃ የሴቶችን እንደወንዶች ምንም ነገር አለማበርከት ወይም አለመሻሻል ሲያቀርቡ ታሪክን ቦታ የሚያሳጣ የማይረባ ክርክር ያመጣሉ። ስለታሪክ በበለጠ ቢመራመሩና ቢያውቁ ብዙ ታላላቅ ሴቶች እንደነበሩና አያሌም ሥራዎች ቀደሞ እንደሠሩ አሁንም ብዙዎች እንዳሉና ብዙ ታላላቅ ሥራዎችን እንደሚያከናውኑ ሊረዱ ይችሉ ነበር።”

እዚህ ላይ አብዱል-ባሃ የዚኖቢያንንና የሌሎችንም የቀድሞ ታላላቅ ሴቶች ሥራ በማውጋት የልበ ሙሉዋንና፥ የሐዋርያት ሁሉ እምነት በአጠራጠረበት ጊዜ በእምነቷ ጸንታ የቆየቸውን የማርያም መቅደላዊትን ዝና ልብ በሚነካ አንደበት ተናግሯል። እንዲህም ሲል ቀጠለ፦

“በዘመናችን ከነበሩት ሴቶች አንዷ የእስላም ቄስ ልጅ የሆነችው ኩራቱል-ዓይን የተባለችው ነች። ባብ በተገለጠበት ዘመን ባሳየችው ታላቅ ድፍረትና ኃይል የሰሟት ሁሉ በጣም ይደነቁባት ነበር። አያሌ ዘመናት ያለውን የኢራንን የሴቶች መሸፋፈን ባህል የራሷን ሽፋን አውልቃ በመጣል እንዲሁም ከወንዶች ጋር መነጋገር ነውር በነበረበት ጊዜ ይህች ጀግና ሴት ከታላላቅና ከተማሩ ወንዶች ጋር በመጋፈጥ ስትከራከርና በየስብሰባውም ስታሳፍራቸው ነበር። የኢራን መንግሥትም እሥረኛ አድርጓት ነበር። በየመንገዱም በድንጋይ ትወገር፥ ትወገዝ፥ ከከተማ ወደ ከተማ ትጋዝ፥ በሞትም ያስፈራሯት ነበር። ግን ለእህቶቿ ነፃነት ከመሥራት ፍላጎቷ ከቶ አልታገደችም። ጥላቻንና ሥቃይን በታላቅ ጀግንነት ተቀበለች። በእሥር ቤት እንኳ አማኞች ታስገኝ ነበር። ከቤቱ ታሥራ በነበረው ለአንድ ኢራንያን ሚኒስትር እንዲህ አለችው። ‘በፈለጋችሁ ጊዜ ልትገድሉኝ ትችላላችሁ የሴቶችን ነፃነት ግን ልታግዱት አትችሉም’። በመጨረሻም የአሳዛኝ ሕይወቷ ፍጻሜ ደረሰ። ወደ አንድ አትክልት ሥፍራ ተወስዳ ታፍና ተገደለች። የሆነ ሆኖ ወደሞቷ ስትሄድ ወደ ሠርግ ቤት እንደሚሄድ ሰው አዳዲስ ልብሶቿን ለብሳ ሄደች። በዚህ ዓይነት ጀብዱና ድፍረት የአያትን ሁሉ በማስገረምና በማስደነቅ ሕይወቷን አሳልፋ ሰጠች። በእርግጥ አንዲት ታላቅ ጀግና ነበረች። ዛሬ በኢራን በባሃኢዎች መካከል የማይበገር ልብ ያላቸውና ታላቅ የቅኔ ተሰጥዎ የታደሉ ሴቶች ይገኛሉ። በጣም አንደበተ ርቱኦችና በታላላቅ ስብሰባዎች መካከልም የመናገር ችሎታ ያላቸው ናቸው።

“ሴቶች የመሻሻል እርምጃቸውን መቀጠል አለባቸው። ስለሰው ዘር እድገት የሳይንስ፥ የስነጽሑፍ፥ የታሪክ ዕውቀታቸውን ማስፋፋት አለባቸው። በአጭር ጊዜም መብታቸውን ያገኛሉ። ሴቶች ክብራችውን ጠብቀው የማኅበራዊውንና የፖለቲካን ጉዳይ አሻሽለው ጦርነትን ተቃውመው የመምረጥ መብትና እኩልነት ለማግኘት ሲጥሩ ወንዶች ያዩአቸዋል። በማንኛቸውም የኑሮ መስመር ተራምዳችሁ እንዳያችሁ እመኛለሁ። በዚያን ጊዜም እራሳችሁ ዘለዓለማዊ የክብር አክሊል ይጎናጸፋል።”
ሴቶችና አዲሱ ዘመን የሴቶች ሃሳብ ተቀባይነትን ሲያገኝና ማኅበራዊ ኑሮን በማደራጀት ረገድ በቂ መብት ሲሰጣቸው ወንዶች የበላይ በነበሩበት ዘመን በአሳዛኝ ሁኔታ ተንቀው ቀርተው በነበሩ ጤንነትን፥ እራስ መግታትን፥ ሰላምንና የግላዊ መልካም ኑሮን ዋጋ በሚመለከቱ ነገሮች ሁሉ ታላቅ መሻሻል ልናገኝ እንችላለን። በዚህ መስመር የሚደረግ መሻሻል በጣም ከፍ ያለ ጠቃሚ ውጤትን ያስገኛል።

አብዱል-ባሃ እንዲህ ይላል፦
“በአለፉት ዘመናት ዓለም በኃይል ተገዝቷል። ወንዶች በጉልበትም ሆነ በሃሳብ፥ በማስገደድና በመቃወም መልክ በሴቶች ላይ የበላይነትን አግኝተው ኖሩ። ዛሬ ግን ሚዛኑ አዘንብሏል። ኃይል የበላይነትን እያጣ፥ ሴቶች ብርቱ የሆኑበት የአእምሮ ንቃት፥ የሰውን ፍላጎት የማወቅ ችሎታ፥ ፍቅርና ማገልገልን የመሰሉ መንፈሳዊ ባሕርይዎች በመጠናከር ላይ ናቸው። ስለዚህ አዲሱ ዘመን ከወንዶች ይልቅ የሴቶችን አስተያየት በብዛት የሚቀበል ነው። ወይንም በትክክል ስንናገር ይህ ዘመን ሴቶችና ወንዶች ሥልጣኔን እኩል የሚመዝኑበት ዘመን ይሆናል።” (ስታር ኢፍ ዘ ዌስት ቮልዩም 8 ቁ. 3 ገጽ 4)

Interesting blog? Like it on Facebook, +1 on Google, Tweet it or share this article on other bookmarking websites.

አስተምሮቶች

  • ትምህርት ለሁሉም
  • ነፍስና ሥጋ
  • አምላክን መውደድ
  • አንድ ዓለም አቀፋዊ ቋንቋ
  • አጉል ጥላቻን ማስወገድ
  • እውነትን መመርመር
  • ከልክ ያለፈ ሀብትና ድህነትን ማስቀረት
  • ከሞት በኋላ ሕይወት
  • የሰው ዘር አንድነት
  • የሳይንስና ሐይማኖት ተደጋጋፊነት
  • የሴቶችና የወንዶች እኩልነት
  • የእርኩስ መንፈስ አለመኖር
  • ገነትና ሲኦል
  • Follow via Facebook
  • Follow via Youtube
unity

© 2023 የኢትዮጵያ ባሃኢዎች

Go Top