የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
  • የባሃኢ ትምህርቶች
    • አምላክና ሐይማኖቶች
    • የአምላክ መልእክተኞች
    • የባሃኢ ትምህርቶች
    • ህግጋቶችና ደንቦች
    • አስተዳደር
  • ማህበረሰባዊ ተሳትፎ
    • ማህበረሰብ ግንባታ
    • የወጣቶች እንቅስቃሴ
  • የባሃኢ ማህበረሰብ
    • የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
    • የአለም ዓቀፍ ማህበረሰብ
    • የባሃኢ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ - አዲስ አበባ ጽ / ቤት
    • ባሃኢዎችን እናስተዋውቃችሁ
  • የባሃኢ መጽሐፍት
    • ቅዱሳን ጽሑፎች
    • ሌሎች
  • ለበለጠ መረጃ
    • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች
    • መልእክት ይላኩልን
    • ቪዲዮዎች
  • ENGLISH

ከልክ ያለፈ ሀብትና ድህነትን ማስቀረት

በሀብታምና በድሃ መካከል ስላለው የሀብት ምጣኔ ልዩነት መሻሻል አስፈላጊነት የባሃኢ ትምህርቶች አጥብቀው ያስረዳሉ።

አብዱል-ባሃ እንዲህ ይላል፦

“የሕዝቦች የኑሮ ሁኔታ መደርጀት ያለበት፥ ድህነት እንዲጠፋና ሁሉም በተቻለ መጠን እንደየማዕረጉና እንደየደረጃው ድሎትንና ደህንነትን እንዲጋራ በሚያስችል ሁኔታ መሆን አለበት። በመካከላችን ባንድ በኩል ሃብት የተጫናቸውን ሰዎች፥ በሌላ በኩል ደግሞ የሚቀምሱት አጥተው የሚራቡትን እድለ ቢሶች እንዲሁም ደግሞ ባለብዙ የተንጣለሉ መኖሪያ ቤቶችና ምንም መጠለያ የሌላቸውን ሰዎች ጎን ለጎን እናያለን። ... እንደዚህ ያለው ሁኔታ ስህተት ሰለሆነ መታረም አለበት። ፈውሱም አህኑኑ በጥንቃቄ መወሰድ አለበት። ይህም ሊደረግ የሚቻለው በሰዎች መካከል ፍጹም እኩልነትን በማስገኘት አይደለም። ፍጹም እኩልነት በሥራ ሊውል የማይችል ሕልም ነው። እኩልነት ቢገኝም ዘለቄታ የለውም። ሊኖር ቢችል እንኳን የዓለም ሥርዓት በሙሉ ይጠፋል። የዓለም ሥርዓት ሕግ በሰዎች ዘንድ ለሁልጊዜ መኖር አለበት።

 

እግዚአብሔር የሰውን ዘር ሲፈጥር ይህንን ደንግጓል

... የሰው ዘር እንደ አንድ ታላቅ ሠራዊት እያንዳንዳቸው የተወሰነላቸውን ተግባር የሚያከናውኑ ጄኔራል፥ ሻምበሎች፥ እንደየማዕረጋቸው የበታች ሹማምንትና ወታደሮች ያስፈልጉታል። ትክክለኛ መስመር የያዘ ሥነ ሥርዓትን ለማስገኘት የደረጃ ልዩነት ፍጹም አስፈላጊ ነው። አንድ ሠራዊት የበላይ ባለሥልጣን ሳይኖረው ሠራዊቱ በሙሉ በጄኔራሎች ብቻ፥ በሻምበሎች ብቻ ወይንም በተራ ወታደሮች ብቻ የተወሰነ ሊሆን አይችልም።

“በእርግጥ ጥቂቶች ከመጠን በላይ ሀብታም ሆነው ሌሎች ደግሞ በሚያሳዝን ሁኔታ ድሆች በመሆናቸው እንደዚህ ያለውን ሁናቴ የሚቆጣጠርና የሚያሻሽል ተቋም መኖር አስፈላጊ ነው። ሀብትን በመጠኑ ማድረግ አስፈላጊ እንደመሆኑ መጠን ድህነትንም መቀነስ ተገቢ ነው። በሁለቱም ከመጠን ማለፍ ጥሩ አይደለም። ... ድህነት ከረሀብ ደረጃ ላይ ደርሶ ስናይ አንድ ቦታ ጭቆና ለመኖሩ ትክክለኛ ምልክት ነው። ሰዎች በዚህ ጉዳይ ላይ አስበውበት ሳይዘገዩ ብዙዎችን ሰዎች የሚያስጨንቃቸውን የድህነት ሁኔታ ለመለወጥ መንቀሳቀ አለባቸው።

“ሀብታሞች ከጸጋቸው መለገስ አለባቸው። ሩኅሩኅ ልብና አዛኝ ኅሊና ኖሯቸው ለነዚያ ለኑሮ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች እንኳን አጥተው ለሚጨነቁት ሐዘንተኞች ማሰብ ይኖርባቸዋል።

“ከመጠን በላይ የሆኑ ሀብትንና ድህነትን የሚያሻሽሉ ልዩ ሕጎች መደንገግ አለባቸው። ... የየሐገሩ መንግሥታት ለሁሉም እኩል ፍትሕ ከሚሰጡት ከመለኮታዊ ሕጎች ጋር መስማማት አለባቸው። ... ይህ ካልተፈጸመ የእግዚአብሔር ሕግ ተቀባይነትን ሊያገኝ አይችልም። ” (ዊስደም ኦፍ አብዱል-ባሃ ፤ ገጽ 140)

Interesting blog? Like it on Facebook, +1 on Google, Tweet it or share this article on other bookmarking websites.

አስተምሮቶች

  • ትምህርት ለሁሉም
  • ነፍስና ሥጋ
  • አምላክን መውደድ
  • አንድ ዓለም አቀፋዊ ቋንቋ
  • አጉል ጥላቻን ማስወገድ
  • እውነትን መመርመር
  • ከልክ ያለፈ ሀብትና ድህነትን ማስቀረት
  • ከሞት በኋላ ሕይወት
  • የሰው ዘር አንድነት
  • የሳይንስና ሐይማኖት ተደጋጋፊነት
  • የሴቶችና የወንዶች እኩልነት
  • የእርኩስ መንፈስ አለመኖር
  • ገነትና ሲኦል
  • Follow via Facebook
  • Follow via Youtube
unity

© 2023 የኢትዮጵያ ባሃኢዎች

Go Top