የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
  • የባሃኢ ትምህርቶች
    • አምላክና ሐይማኖቶች
    • የአምላክ መልእክተኞች
    • የባሃኢ ትምህርቶች
    • ህግጋቶችና ደንቦች
    • አስተዳደር
  • ማህበረሰባዊ ተሳትፎ
    • ማህበረሰብ ግንባታ
    • የወጣቶች እንቅስቃሴ
  • የባሃኢ ማህበረሰብ
    • የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
    • የአለም ዓቀፍ ማህበረሰብ
    • የባሃኢ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ - አዲስ አበባ ጽ / ቤት
    • ባሃኢዎችን እናስተዋውቃችሁ
  • የባሃኢ መጽሐፍት
    • ቅዱሳን ጽሑፎች
    • ሌሎች
  • ለበለጠ መረጃ
    • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች
    • መልእክት ይላኩልን
    • ቪዲዮዎች
  • ENGLISH

አጉል ጥላቻን ማስወገድ

የሃይማኖት ከንቱ ጥላቻ
እጅግ ታላቁ ሰላም የሚመሠረትበትን መንገድ በግልጽ እንድናይና ስለአፈጻጸሙ ባሃኦላህ የሚሰጠንን ዘዴ እንድናውቅ በአለፉት ዘመናት ለጦርነት ምክንያት የሆኑትን ዋና ዋና መነሻዎችን እንመርምር።

ለጦርነት ምክንያት ከሆኑት ነገሮች አንዱ፥የሃይማኖት ጥላቻ ነበር። የባሃኢ ሃይማኖት ይህንን ሲያብራራ በሃይማኖት ክፍሎች መካካል ጥላቻንና ግጭትን የፈጠረ፥ እውነተኛ ሃይማኖት ሳይሆን፥ የእውነተኛ ሃይማኖት መታጣትና፥ ያለማስረጃ አንዱ ሌላውን በመከተልና ትክክለኛ ያልሆነ ትርጉም ማግኘት ነው።
አብዱል-ባሃ በፓሪስ ካደረጋቸው ንግግሮች አንዱ እንዲህ ይላል፦

“ሃይማኖት ሁሉን ልቦች የሚያስተሳስር፤ ጦርነትንና ጥላቻን ከምድር ገጽ የሚያስወግድ መሆን ይገባዋል። መንፈሳዊነትን የሚፈጥርና ለእያንዳንዱ ሰው ሕይወትንና ብርሃንን የሚያስገኝ መሆን አለበት። ሃይማኖት የጥላቻና የመለያየት ምክንያት ከሆነ ባይኖር ይሻላል። ይህንን ከመሰለ ጥላቻና የመለያየት እምነት መራቅ ከሃይማኖት ይቆጠራል። የመድኃኒት ጥቅሙ የሚታወቀው ከሕመም ሲያድን በመሆኑ፥ እያደረ የሚያብስ ከሆነ መቅረቱ ይመረጣል። ፍቅርንና አንድነትን የማያስገኝ ሃይማኖት፥ ሃይማኖት አይደለም።” (ዊስደም ኦፍ አብዱል-ባሃ)

ደግሞም እንዲህ ይላል፦
“የሰው ልጅ ታሪክ ከተጀመረ እስከአለንበት ጊዜ ድረስ ያሉት ልዩ ልዩ ሃይማኖቶች፥ አንዱ ሌላውን የተሳሳተ አድርጎ በመገመት እርስ በራሳቸው ሲረጋገሙ ቆዩ። ... በጠላትነትና በጥላቻ በመተያየት በፍጹም ተራራቁ። በሃይማኖት ምክንያት የተደረጉትን ጦርነቶች ታሪክ ብንመለከት፥ ክሩሴድ (የመስቀል ጦርነት) የተባለው ከታላላቆቹ የሃይማኖት ጦርነቶች አንዱ ከሁለት መቶ ዓመታት በላይ እንደቆየ እንረዳለን። ... አንዳንዴ የክርስቲያን ሃይማኖ ተከታዮቹ እስላሞችን በመግደልና ማርከው በመውሰድ ሲያሸንፉ በሌላው ጊዜ ደግሞ እስላሞቹ በወራሪዎቹ ላይ ትልቅ አደጋን በማድረስ ድል ይነሱዋቸውና ብዙ ደም ያፈሱ ነበር።

“የአውሮፓ ሃይማኖታውያን ወደየአገራቸው እስከተመለሱ ድረስ በኃይል እየተዋጉና በመሐከሉም በድካም ምክንያት እያቋረጡ የምሥራቅ አገሮች ፈርሰው ትቢያ እስኪሆኑ ድረስ ሕዝቦቻቸው ሲተራመሱና ሲንጫጩባቸው ለሁለት መቶ ዓመታት ያህል ሲዋጉ ቆዩ። ... ሆኖም ይህ ‘ከሃይማኖት ቅዱስ ጦርነቶች’ አንዱ ብቻ ነበር።
“የሃይማኖት ጦርነቶች ብዙዎች ነበሩ። በካቶሊክና በፕሮቴስታንት ሃይማኖት ልዩነት ምክንያት በተደረገው ግጭት ዘጠኝ መቶ ሺህ ፕሮቴስታንቶች እንደተሰው ታሪክ ይመሰክራል … ። በእስር ቤቶች የተሰቃዩ ስንቶች ነበሩ! ምርኮኞቹስ በምን ዓይነት የጭካኔ ሁኔታ ይያዙ ነበር! ይህ ሁሉ የሆነው በሃይማኖት ስም ነበር!
“ክርስቲያኖችና እስላሞች አይሁዶችን እንደ እግዚአብሔር ጠላቶችና እንደ ሰይጣን ወገኖች ይመለከቱዋቸዋል። ከዚያም የተነሣ ይረግሙዋቸውና ያሳድዱዋቸውም ነበር። ቁጥራቸው እጅግ የበዛ አይሁዶች ተገደሉ፥ ተዘረፉ፥ ቤቶቻቸውም ተቃጠሉ፥ ልጆቻቸው ተማረኩ። አይሁዶችም በበኩላቸው ክርስቲያኖችን እንደ አረመኔ ይቆጥሯቸው ነበር። እስላሞችንም ደግሞ የሙሴ ጠላቶችና የሕጉም አፍራሾች አድርገው ይመለከቷቸው ነበር። ከዚህም የተነሳ ይጠሷቸውና እስከዛሬም ድረስ ይረግሟቸዋል።

“ነገር ግን የባሃኦላህ ፀሐይ ከወደ ምሥራቅ በወጣ ጊዜ የሰው ልጆች አንድነትን አወጀ። የሰውን ልጅ በጠቅላላው እንዲህ ሲል ጠራ ‘እናንት የአንድ ዛፍ ፍሬዎች ናችሁ፥ የሁለት ዛፍ፥ ይኸውም አንደኛው የመለኮታዊ ምህረት ዛፍ ሌላው ደግሞ የሰይጣን ዛፍ ፍሬዎች ልትሆኑ አትችሉም...’ ስለዚህ እርስ በራሳችን በፍጹም መፋቀርን መማር ይገባናል። ማንኛውንም ሕዝብ ከሰይጣን ወገን አድርገን በማሰብ ፈንታ ሁሉም የአንድ እግዚአብሔር አገልጋይ መሆኑን ማወቅና መማር ይገባናል። እርግጥ ነው ጥቂቶች ባለማወቅ ይሳሳታሉ። እነዚህ መመከርና መማር ይገባቸዋል … ። አንዳንዶች ደግሞ ምንም የማያውቁ ናቸው። በአስተሳሰባቸው የበሰሉ እንዲሆኑ ዕርዳታን ይሻሉ። ግብረገብነትም የሚያንሳቸው አሉ። እነዚህም እስኪያሻሽሉ ድረስ በትዕግስት መያዝ ይገባቸዋል። ነገር ግን በሽተኛው ሰው በሕመሙ ምክንያት መጠላት የለበትም፤ ሕፃኑም፥ ልጅ በመሆኑ ሊርቁት አይገባም፤ ያልተማረው ዕውቀት በማጣቱ ሊናቅ አይችልም። ሁሉ ተፋቅረው እንዲኖሩ መማር፥ መመከርና በፍቅር መረዳት አለባቸው። የሰው ልጅ በሙሉ በፍጹም ደስታና በሰላም በእግዚአብሔር ጥላ ሥር ለመኖር ይችል ዘንድ ተገቢው ሁሉ መደረግ አለበት።” (ስታር ኦፍ ዘ ዌስት ቮልዩም 8 ገጽ 76)

የዘርና የአገር ፍቅር አድልዎ
ስለሰው ዘር አንድነት ከሚያስተምረው ከባሃኢ እምነት ትምህርት መካከል አንዱ፥ ለጦርነት መነሾ ሊሆኑ ከሚችሉት አንዱ የሆነውን ማለትም የዘር አድልዎን ከሥሩ የሚነቅል ነው። አንዳንድ ጎሣዎች ከሌሎቹ የበላይ ነን በማለት ‘ጉልበተኛ ብቻ ይኑር’ የሚለውን መርህ ይከተላሉ። ይህም ብልጫ ለራሳቸው ጥቅም ማዳበሪያና እንዲያውም ደካማውን ጎሣ ለመደምሰስ መብት የሰጣቸው ይመስላቸዋል። ከዓለም ታሪክ ውስጥ እጅግ ጨለማ የሆኑት ገጾች በዚህ መርህ ያለርኅራኄ መጠቀምን የሚገልጹ ናቸው። እንደባሃኢዎች አስተያየት የሁሉም ጎሣ ሕዝቦች በእግዚአብሔር ፊት እኩል ዋጋ አላቸው። ሁሉም ተገቢ ትምህርት ካገኙ ለመሻሻል የሚችሉ አስደናቂ የተፈጥሮ ችሎታ አላቸው። እያንዳንዳቸውም መላውን የሰው ዘር አካል ክፍሎችን በማደኅየት ፋንታ ለማበልጸግና ሕይወቱንም የተሟላ ለማድረግ አስፈላጊ ናቸው።

አብዱል-ባሃ እንዲህ ይላል፦
“እግዚአብሔር አንድ ነገድ አድርጎ ስለፈጠረን የዘር አድልዎ ቅዠትና ከንቱ አምልኮ ነው።... ከመጀመሪያውም በልዩ ልዩ ሃገሮች መካከል ድንበር አልነበረም፤ ማንኛውም የምድር ክፍል በይበልጥ ተለይቶ ለአንድ ሕዝብ ብቻ አልተሰጠም። በእግዚአብሔር ዘንድ በጎሣዎች መካከል ልዩነት የለም። እንግዲያውስ ሰው ይህንን አድልዎ የፈጠረው ለምን ይሆን? ከእንደዚህ ያለው ቅዠት የተነሣውን ጦርነትስ እንዴት እንደግፋለን? እግዚአብሔር ሰዎችን የፈጠረው እርስ በርሳቸው እንዲተላለቁ አይደለም። ሁሉም ጎሣዎች፥ ነገዶች፥ የሃይማኖት ክፍሎችና ልዩ ልዩ ደረጃ ያላቸው ሰዎች የሰማያዊ አባታቸውን ልግስና እኩል ይካፈላሉ።
“ሊኖር የሚችለው እውነተኛው ልዩነት የእምነትና ለእግዚአብሔር ሕግጋት የመታዘዝ መጠን ብቻ ነው። አንዳንዶች በተቀጣጠለ ችቦ የሚመሰሉ አሉ፤ ሌሎች ደግሞ በሰው ዘር ሰማይ ውስጥ እንደከዋክብት የሚያንጸባርቁ ይገኛሉ።

“ከየትኛውም አገር ፥ ከማንኛውም እምነት ሆነ ቀለም የሰውን ዘር የሚወዱ ከሰዎች ሁሉ ከፍተኞች ናቸው።” (ዊዝደም ኦፍ አብዱል-ባሃ ገጽ 137)
ከዘር አድልዎ የሚነጻጸር ጥፋትን ሊያስከትል የሚችል የፓለቲካ ወይንም የሀገር ፍቅር አድልዎ ነው። ጠባቡ የሀገር ፍቅር ስሜት ዓለም በመላ አገሩ በሆነው ሰፊ ዓለም አቀፋዊ ፍቅር ስሜት ጋር መዋሐጃ ጊዜው መጥቷል።

ባሃኦላህ እንዲህ ይላል፦
“በቀድሞው ዘመናት እንዲህ ይባል ነበር ‘የራስን አገር መውደድ እምነት ነው፤’ ታላቁ አንደበት ... በዚህ ግልጸቱ ዘመን እንዲህ አውጇል፦ ‘መኩራራት የራሱን አገር ለሚወድ አይደለም። ይልቁንስ መላውን የሰውን ልጅ ለሚወድ እንጂ።’ በነዚህ በተከበሩ ቃላት አዲስ ስሜት በመፍጠር የልቦች አዕዋፋትን አዲስ በረራን አስተማረ፤ መወሰንና በጭፍን ማመንንም ከመጽሐፉ ፋቀ።” (ታብሌት ኦፍ ዘ ወርልድ)

 

Interesting blog? Like it on Facebook, +1 on Google, Tweet it or share this article on other bookmarking websites.

አስተምሮቶች

  • ትምህርት ለሁሉም
  • ነፍስና ሥጋ
  • አምላክን መውደድ
  • አንድ ዓለም አቀፋዊ ቋንቋ
  • አጉል ጥላቻን ማስወገድ
  • እውነትን መመርመር
  • ከልክ ያለፈ ሀብትና ድህነትን ማስቀረት
  • ከሞት በኋላ ሕይወት
  • የሰው ዘር አንድነት
  • የሳይንስና ሐይማኖት ተደጋጋፊነት
  • የሴቶችና የወንዶች እኩልነት
  • የእርኩስ መንፈስ አለመኖር
  • ገነትና ሲኦል
  • Follow via Facebook
  • Follow via Youtube
unity

© 2023 የኢትዮጵያ ባሃኢዎች

Go Top