የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
  • የባሃኢ ትምህርቶች
    • አምላክና ሐይማኖቶች
    • የአምላክ መልእክተኞች
    • የባሃኢ ትምህርቶች
    • ህግጋቶችና ደንቦች
    • አስተዳደር
  • ማህበረሰባዊ ተሳትፎ
    • ማህበረሰብ ግንባታ
    • የወጣቶች እንቅስቃሴ
  • የባሃኢ ማህበረሰብ
    • የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
    • የአለም ዓቀፍ ማህበረሰብ
    • የባሃኢ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ - አዲስ አበባ ጽ / ቤት
    • ባሃኢዎችን እናስተዋውቃችሁ
  • የባሃኢ መጽሐፍት
    • ቅዱሳን ጽሑፎች
    • ሌሎች
  • ለበለጠ መረጃ
    • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች
    • መልእክት ይላኩልን
    • ቪዲዮዎች
  • ENGLISH

ትምህርት ለሁሉም

ሰዎችን የሚያሠለጥንና የሚመራ እንዲሁም የተፈጥሮ እውቀታቸውን እንዲያሻሽሉ የሚያደርገው ትምህርት፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተላኩ ነቢያቶች ሁሉ ከፍተኛው ዓላማ ነው። በባሃኢ ሃይማኖትም እንደዚሁ ትምህርት በመሠረቱ ተፈላጊና ማለቂያ የሌለው መሆኑ በግልጽ ታውጇል። አስተማሪ ለሥልጣኔ ከፍተኛ ኃይል ሲሆን፥ ማስተማርም ሰዎች ሊሹት የሚገባ ታላቅ ምኞት ነው። ትምህርት የሚጀመረው በእናት ማሕጸን ሲሆን፥ ሕይወት ማለቂያ እንደሌለው ሁሉ ዕውቀትም ማለቂያ የለውም። ትምህርት ለትክክለኛ ኑሮ ሁልጊዜ ተፈላጊና ለማኅበራዊ አኗኗርም መሠረቱ ነው።

ትምህርት በትክክለኛው መንገድ ለሁሉም ሲሰጥ የሰው ልጅ ይለወጣል። ምድርም ገነት ትሆናለች። አብዛኛው ሰው በከንቱ ጥላቻ በአሳሳች ትምህርት፥ በተሳሳተ ፍልስፍና እንዲሁም ከህፃንነቱ ጀምሮ በመጥፎ ጠባይ የተመረዘ በመሆኑ በአሁኑ ዘመን በእምነት ደህና እውቀት አለው የሚባል በጣም ጥቂት ነው። ስንት ናቸው፥ ገና በሕፃንነታቸው እግዚአብሔርን እንዲያፈቅሩ ሕይወታቸውንም ለእርሱ እንዲሰጡ የተመከሩ! ለሰው ልጆች ማገልገልን ከፍተኛው የኑሮአቸው ዓላማ ያደረጉ፥ ለጠቅላላው ጥቅም እንዲውል ኃይላቸውን ያዳበሩ ስንት ናቸው! በእርግጥ እነዚህ ናቸው የመልካም ትምህርት ተፈላጊ ነገሮች። በሂሣብ፥ በሰዋሰው፥ በጂኦግራፊና በቋንቋ ጥናት ወዘተ አዕምሮን ማጨቅ የተከበሩና ጠቃሚ ሰዎችን ለማስገኘት የሚሰጡት አገልግሎት የተወሰነ ነው።

ትምህርት ለሁሉም እንዲሰጥ ባሃኦላህ ያዛል፦
“እያንዳንዱ አባት ሴቶችና ወንዶች ልጆቹን ማስተማርና በቅዱሳን መልእክቱ የተሰጡትንና እንዲሁም ሌላውን ሁሉ እንዲያስተምር ታዟል። እያለው ይህንን ትዕዛዝ ለመፈጸም የማይፈቅድ ካለ የባሃኢ ቤተ - ፍትሕ ለማስተማር ያህል የሚበቃ ገንዘብ ከወላጁ መቀበል ይገባዋል። ወላጆች ለማስተማር የማይችሉ ከሆነ፥ ጉዳዩ የባሃኢ ቤተ- ፍትሕን ይመለከታል። በእውነት ይህንን ቤተ ፍትሕ ለድሆችና ለችግረኞች ተገን አድርገናል።

“ልጁን ወይንም የማንንም ልጅ ያስተማረ ከልጆቼ መሀከል አንዱን እንዳስተማረ እቆጥረዋለሁ። ዓለምን የከበበው ጸጋዬ፥ የደግነት ፍቅሬና ምህረቴ በእርሱ ላይ ይረፍ። ... ” (ኪታቢ-አቅዳስ)

“ሴቶችም ሆኑ ወንዶቹ በእርሻ፥ በንግድ እንዲሁም በማንኛውም ዓይነት ሥራ ካገኙት ሃብታቸው ለልጆቻቸው ማሰልጠኛ የሚበቃ ሀብት በሁነኛ ሰው እጅ ማኖር ይገባቸዋል። ተቀማጩ ገንዘብ በባሃኢ ቤተ - ፍትሕ እውቅና ለልጆቹ ማሰልጠኛ አገልግሎት ይውላል።” (ታብሌት ኦፍ ዘ ዎርልድ)

 

የተፈጥሮ ልዩነት
በባሃኢ አስተያየት የሕፃናት ተፈጥሮ እንደሰም በአስተማሪው ፈቃድ እንደ ተፈለገ ቅርጽ የሚሰጠው አይደለም። ነገር ግን አንዱ ከሌላው የሚለይበት አብሮት የተወለደ ከእግዚአብሔር የተሰጠው ባህርይና ግለኝነት ሲኖረው ይህም በተወሰነ መንገድ ቢሰለጥን በበለጠ ጥቅምን ለማስገኘት የሚችል ነው። ይህም መንገድ ለእየአንዳንዱ የተለየ ነው። ሁለት ሰዎች አንድ ዓይነት ችሎታና ተሰጥዎ ሊኖራቸው አይችልም። ስለዚህ እውነተኛ አስተማሪ ሁለቱን ተፈጥሮ እኩል ለማደርግ መሞከር አይገባውም። እንዲያውም አንድን ተፈጥሮ ሌላ ቅርጽ ለማስያዝ ፈጽሞ አይሞክርም። ይልቁንም በማደግ ላይ ያለውን የወጣቱን ተፈጥሮ ኃይል በአክብሮት በመያዝ እየተሻሻለ እንዲሄድ ማበረታታትና መጠበቅ እንዲሁም ተገቢውን እርዳታና እንክብካቤ መስጠት። ሥራው ልዩ ልዩ አዝርእቶችን እንደሚንከባከብ አትክልተኛ ይመሰላል። አንዱ አትክልት  ፀሐይን ይወዳል። ሌላው ደግሞ ጥላን ይፈልጋል። አንዱ የወንዝ ዳርን ይወዳል፥ ሌላው ደግሞ ጉብታ ቦታን ይመርጣል። አንዱ በአሸዋማ ቦታ ላይ በይበልጥ ይፀድቃል፥ ሌላው ዓይነት ዋልካ አፈርን ይፈልጋል። እያንዳንዱ እንደፍላጎቱ ካላገኘ ፍጹምነቱ በግልጽ ሊታይ አይችልም።

አብዱል-ባሃ እንዲህ ይላል፦
“ትምህርት በሰው ዘር ላይ ከፍተኛ ውጤት እንዳለው ነቢያት ያውቁታል። ነገር ግን አእምሮና የመረዳት ችሎታ በመሠረቱ የተለያየ መሆኑን ያስተምራሉ። በዕድሜ፥በጎሳና በዘር እንዲያውም ከአንድ ቤተሰብ የሆኑ በአንድ አስተማሪ የሰለጠኑ ልጆች በአእምሮና በመረዳት ችሎታ የተለያዩ መሆናቸውን እናያለን። ቅርፊቱ ምንም ያህል ቢወለወል እንደ አንጸባራቂው ሉቁ፥ ጥቁሩ ድንጋይ ዓለምን እንደሚያበራው ዕንቁ ፥ እሾሃማው ቁልቋል በትምህርትና በመሻሻል የተባረከውን ዛፍ ሊሆኑ አይችሉም። ይህም ማለት ትምህርት የሰውን መሠረታዊ ተፈጥሮ አይለውጥም፥ ሆኖም አስደናቂ ውጤትን ያስገኛል። በዚህ ኃይል አማካይነት እምቅ የሰው የተፈጥሮ ችሎታና ኃይል ሊገለጥ ይችላል።” (ታብሌት ኦፍ አብዱል-ባሃ ቮልዩም 31 ገጽ 587)

 

 

ግብረገብነት (የባህርይ ሥልጠና)

ከትምህርት ከፍተኛው ተፈላጊ የግብረገብነት ትምህርት ነው። በዚህ ረገድ ከትምህርት ይልቅ፥ ምሳሌነት በይበልጥ ይጠቅማል። የቤተሰቦች፥ የአስተማሪዎችና አብረዋቸው የሚውሉ ሰዎች ምሳሌነት በጣም ጠቃሚ ነው። የእግዚአብሔር ነቢያት ለሰው ልጆች ታላቅ አስተማሪዎች ስለሆኑ ምክራቸውንና አኗኗራቸውን ሕፃናት ነፍስ ሲያውቁ በአእምሮአቸው እንዲቀረጽ ማድረግ ይገባል። የወደፊት የዓለም ሥልጣኔ መሠረት የሆኑትን ሕጎች የገለጸው የታላቁ አስተማሪ የባሃኦላህ ቃላቶች በተላይ ጠቃሚ ናቸው። እርሱም እንዲህ ይላል፦

“በክብር ብዕር አማካይነት የተገለጸውን ለልጆቻችሁ አስተምሩ። ከታላቅነትና ከኃይል ሰማይ የወረደላችሁን አስተምሯቸው። የመሐሪውን መልእክት በቃላቸው አጥንተው፥ ጣዕም በተመላው ዜማ በየቤተ መቅደሱ አዳራሽ (ማሽሪቁል አስካር) እንዲያሰሙ አድርጉአቸው።” (ስታር ኦፍ ዘ ዌስት ቮልዩም 9 ቁጥር 7 ገጽ 81

 

ሥነ-ጥበብ፣ ሳይንስ፣ እና የእጅ ሙያ

በእጅ ሙያ በሳይንስና በመሳሰሉትም ሁሉ መሠልጠን ጠቃሚና አስፈላጊ ነው። ስለዚህ ባሃኦላህ እንዲህ ይላል፦

“ዕውቀት ለፍጡር (ለሰው) በክንፎችና በመወጣጫ መሰላል ይመሰላል። ዕውቀትን መፈለግ ለሁሉም ግዴታ ነው። ሆኖም በቃል ተጀምሮ በቃል የሚያልቅ ሳይንስ ሳይሆን ለሰው ልጆች ሁሉ የሚጠቅም ሳይንስ መሆን አለበት። የሳይንስና የእጅ ሙያ አዋቂዎች በሰው ልጆች መካከል ታላቅ ክብር አላቸው። በእርግጥ የሰው ዕውነተኛው ሀብቱ ዕውቀቱ ነው። ዕውቀቱ የክብር፥ የብልጽግና የደስታ፥ የፍስሐ፥ የሐሴትና የከፍተኛ ፈንጠዝያ ማግኛ ምንጭ ነው።” (ታብሌት ኦፍ ታጃሊያት)

Interesting blog? Like it on Facebook, +1 on Google, Tweet it or share this article on other bookmarking websites.

አስተምሮቶች

  • ትምህርት ለሁሉም
  • ነፍስና ሥጋ
  • አምላክን መውደድ
  • አንድ ዓለም አቀፋዊ ቋንቋ
  • አጉል ጥላቻን ማስወገድ
  • እውነትን መመርመር
  • ከልክ ያለፈ ሀብትና ድህነትን ማስቀረት
  • ከሞት በኋላ ሕይወት
  • የሰው ዘር አንድነት
  • የሳይንስና ሐይማኖት ተደጋጋፊነት
  • የሴቶችና የወንዶች እኩልነት
  • የእርኩስ መንፈስ አለመኖር
  • ገነትና ሲኦል
  • Follow via Facebook
  • Follow via Youtube
unity

© 2023 የኢትዮጵያ ባሃኢዎች

Go Top