የባሃኢ ሃይማኖት ስለ ነፍስና ሥጋ እንዲሁም ከሞት በኋላ ስለ አለው ሕይወት፥ የረቂቅ ኃይሎች (ሳይኪክ) ጥናት ምርምር ካስገኘው ውጤት ጋር ይስማማል። እንደአየነው ሞት አዲስ እንደመወለድ የሚቆጠር፥ ከሥጋዊ ኑሮ እስረኛነት አምልጦ ሰፋ ወደ አለው ኑሮ መሸጋገር መሆኑንና ከዚያም በኋላ ያለው የኑሮ ዕድገት ወሰን እንደሌለው ያስተምራሉ።
ነፍስ ከሥጋ ከተለየች በኋላ ስለአለው ሕይወትና ስለማያቋርጠው የነፍስ ተግባር፥ በቂ ማስረጃ ይሆናል ብለው ያለ አድልዎ በታላቅ ጥንቃቄ ሊቃውንት ያዘጋጁት ሣይንሳዊ ማብራሪያ በብዛት በመሰብሰብ ላይ ይገኛል። ኤፍ ደብልዩ ኤች ሚየርስ ስለ ነፍስ ጥናት ምርምር ድርጅቶች ሂውማን ፔርሶናሊቲ በተባለው መጽሐፍ እንደሚከተለው ጽፏል፦
“የአንዳንድ ምርምር ውጤት፥ ብዙዎችን ተመራማሪዎች እኔንም ጨምሮ የቴሌፓቲክ ግንኙነት በምድር ላይ ባሉት ሰዎች መሀከል ብቻ ሳይሆን ወደ ሰማይ በአረጉ ሰዎችና በምድር ላይ ባሉትም ሰዎች መሀከል መሆኑን አሳምኗል። ይህን የመሰለው የምርምር ውጤት ለአዲስ ራዕይ በር ከፋች ሊሆን ይችላል። …
“ብዙ መታለል ፥ ቁም ቅዠት፥ መጭበርበር ወ.ዘ.ተ. ባሉበት ሁኔታ፥ እራስን ማታለል እንኳ ቢኖር፥ ሐቁ ግን ከመቃብር ማዶ ካሉት መንፈሳዊ መልእክቶች እንደሚደርሱን አሳይተናል።.
“በፍልስፍና ሆነ በራዕይ ሁኔታ አንዳንድ ጊዜያዊ መግለጫዎች ከዚህ ዓለም ስለተለዩ ነፍሶች መሰጠታቸውን አይተናል። እኔ እንዳየሁት፥ ቢያንስ ቢያንስ የነፍስ ሁኔታ በጥበብና በፍቅር መጨረሻ የሌለው ኢቮሊሽን (አዝጋሚ ለውጥ) እንዳለው በቅድሚያ ለማወቅ ምክንያት አግኝቻለሁ። ለምድር ያላቸው ፍቅር፥ በይበልጥም በአድናቆትና በስግደት መልክ የሚገለጸውን ከፍተኛ ፍቅራቸውን የሚያግደው የለም። … መጥፎ መንፈስ በነርሱ ዘንድ ከባሪያነት ሁኔታ ያነሰ ነው። ራሱን በቻለ ከፍተኛ ኃይል አልታቀፈም ይልቁንም ቀና የሆኑ ከፍተኛ መናፍስት ብቸኛ ከሚያደርገው አበይት የተሳሳቱትን ነፍሳት ነፃ ለማውጣት የሚጥሩበት ሂደት ነው። በእሳት የመቃጠል ቅጣት ሊኖር አይገባም። ለሰው ቅጣቱ ወይንም ወሮታው ራሱን ማወቁ ነው። ወሮታ፥ ራስን ማወቅ ወይንም ወደሚወዱት ነፍስ መቅረብ ነው። ቅጣት ማለትም ይህንን ፀጋ መነፈግ ነው። በዚያ ዓለም ፍቅር ማለት ራስን ከጥፋት ማዳን ነው። የቅዱሳን መቀራረብ ራስን ከማጌጥ በተጨማሪ ዘላለማዊ ህይወትን ይሰጣል። የመንፈስ ግንኙነት (ቴሌፓቲ) ሕግ ከቅዱሳን ጋር ያለን ግንኙነት ዛሬም እዚህ ሆነ አይጓደልብንም። ዛሬም ቢሆን የተለዩን ነፍሳት በፍቅር ለጸሎታችን መልስ ይሰጣሉ። ፍቅር ጸሎት እንደመሆኑ መጠን ዛሬም ቢሆን ፍቅር የተመላበት ትዝታችን የተለዩንን ሰዎች ነፍስ ወደ ላይ በሚያደርጉት ጉዞ የሚያበረታታና የሚደግፍ ይሆናል።”
በጥንቃቄ በተደረገ የሳይንስ ጥናት ላይ በተመሠረተው በዚህ አስተያየትና በባሃኢ ሃይማኖት መካከል ያለው ስምምነት ከፍ ያለ ግምት የሚሰጠው ነው።
Interesting blog? Like it on Facebook, +1 on Google, Tweet it or share this article on other bookmarking websites.