የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
  • የባሃኢ ትምህርቶች
    • አምላክና ሐይማኖቶች
    • የአምላክ መልእክተኞች
    • የባሃኢ ትምህርቶች
    • ህግጋቶችና ደንቦች
    • አስተዳደር
  • ማህበረሰባዊ ተሳትፎ
    • ማህበረሰብ ግንባታ
    • የወጣቶች እንቅስቃሴ
  • የባሃኢ ማህበረሰብ
    • የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
    • የአለም ዓቀፍ ማህበረሰብ
    • የባሃኢ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ - አዲስ አበባ ጽ / ቤት
    • ባሃኢዎችን እናስተዋውቃችሁ
  • የባሃኢ መጽሐፍት
    • ቅዱሳን ጽሑፎች
    • ሌሎች
  • ለበለጠ መረጃ
    • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች
    • መልእክት ይላኩልን
    • ቪዲዮዎች
  • ENGLISH

ገነትና ሲኦል

ባሃኦላህና አብዱል-ባሃ ስለገነትና ሲኦል በቀደምት የሃይማኖት መጽሐፍት የተሰጡት መግለጫዎች እንደ ዘፍጥረት የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ሁሉ ምሳሌዎች እንጂ ቃል በቃል የሚተረጎሙ እውነቶች አለመሆናቸውን ያስተምራሉ። እንደነርሱም ትምህርት ገነት የፍጹምነት፥ ሲኦል የኢ-ፍጹምነት ሁኔታ ነው። ገነት ከእግዚአብሔር ፈቃድና ከመሰሎቻችን ጋር መጣጣም ሲሆን ሲኦል ግን እነዚህ ሁኔታዎችን ማጣት ነው። ገነት የመንፈሳዊ ሕይወት ሁኔታ ሲሆን ፥ ሲኦል የመንፈሳዊ ሞት ሁኔታ ነው። ሰው በሕይወት እያለ በገነት ወይንም በሲኦል ሊገኝ ይችላል። የገነት ፍስሐዎች መንፈሳዊ ደስታዎች ናቸው። የሲኦልም ስቃይ እነዚህን ደስታዎች አለማግኘት ነው።

አብዱል-ባሃ እንዲህ ይላል፦
“በእውነት ብርሃን አማካይነት ከእነዚህ መጥፎ ምግባራት ጨለማ ነጻ ወጥተው በእውነት ፀሐይ ብርሃን ሲያንጸባርቁ፥ በመልካም ምግባሮች ሁሉ ሲቀደሱ፥ ይህን እንደ እጅግ በጣም ታላቅ ዋጋ ይቆጥሩታል፤ እውነተኛ ገነትም እንደሆነ ያውቃሉ። በዚሁ ሁኔታ የመንፈስ ቅጣት፥ ይህም ማለት የሕይወት ስቃይና ቅጣት፥ በፍጥረት ዓለም መገዛት፥ ከእግዚአብሔር መጋረድ፥ ጨካኝና ደንቆሮ መሆን፥ ወደ ክፉ የሥጋዊ ስሜት መውደቅ፥ በእንስሳዊ ድክመት መዋጥ፥ እንደ ውሸት፥ አጥቂነትና ጭካኔ፥ ከዓለማዊ ነገር ጋር እንደ መጣበቅ፥

በሰይጣናዊ ሃሳቦች ውስጥ እንደመነከር የመሳሰሉ የጨለሙ ባሕርያት መያዝ እንደሆነ ይቆጥሩታል፤ ለእነርሱ እነዚህ እጅግ በጣም ከባድ ቅጣትና ስቃይ ናቸው።
“የዚህ ዓለም ዋጋዎች የሰውን ሰውነት የሚያስጌጡ መልካም ምግባሮችና ፍጹም የሆኑ ባሕርያት ናቸው። ለምሳሌ ጨላማዊ ነበር፥ ብሩህ ሆነ፤ ያላወቀ ነበር፥ ጥበበኛ ሆነ፤ ቸልተኛ ነበር፥ ንቁ ሆነ፤ አንቀላፍቶ ነበር፥ ከእንቅልፍ የነቃ ሆነ፤ ሙት ነበር፥ ሕይወት ያለው ሆነ፤ እውር ነበር፥ የሚያይ ሆነ፤ ደንቆሮ ነበር፥ ሰሚ ሆነ፤ ምድራዊ ነበር፥ የመንግሥተ ሰማያት ሆነ፤ ቁስ አካል ነበር፥ መንፈሳዊ ሆነ። በእነዚህ ዋጋዎች አማካይነት በመንፈስ መወለድን ይቀዳጃል፤ አዲስ ፍጡርም ይሆናል። በወንጌል ስለ ደቀ መዛሙርቱ ‘በደም ወይም በሥጋ ፈቃድ፥ ወይም በሰው ፈቃድ አልተወልዱም፤ በእግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ’ ተብሎ የተጻፈው ጥቅስ መገለጫ ይሆናል፤ ይህም ማለት፥ የሰው ጠባይና ባሕርይ ከሆነው ከእንስሳዊ ጠባይና ባሕርይ ነፃ ወጥተው፥ የእግዚአብሔር ስጦታ የሆኑትን መለኮታዊ ጠባዮች አገኙ ማለት ነው። የዳግም ልደትም ትርጉም ይህ ነው። እንዲህ ላሉት ሰዎች ከአምላክ ከመጋረድ የበለጠ ስቃይ የለም፤ ከሥጋዊ ክፉ ምግባር፥ ከጨለሙ ባሕርያት፥ ከዝቅተኛ ጠባይ፥ በሥጋዊ ፍላጎት ስሜት ከመዋጥ ይበልጥ የከፋ ቅጣት የለም። በእውነት ብርሃን አማካይነት ከእነዚህ መጥፎ ምግባራት ጨለማ ነፃ ወጥተው በእውነት ፀሐይ ብርሃን ሲያንጸባርቁ፥ በመልካም ምግባሮች ሁሉ ሲቀደሱ፥ ይህን እንደ እጅግ በጣም ታላቅ ዋጋ ይቆጥሩታል፤ እውነተኛ ገነትም እንደሆነ ያውቃሉ። በዚሁ ሁኔታ የመንፈስ ቅጣት፥ ይህም ማለት የሕይወት ስቃይና ቅጣት፥ በፍጥረት ዓለም መገዛት፥ ከእግዚአብሔር መጋረድ፥ ጨካኝና ደንቆሮ መሆን፥ ወደ ክፉ የሥጋዊ ስሜት መውደቅ፥ በእንስሳዊ ድክመት መዋጥ፥ እንደ ውሸት፥ አጥቂነትና ጭካኔ፥ ከዓለማዊ ነገር ጋር እንደመጣበቅ፥ በሰይጣናዊ ሃሳቦች ውስጥ እንደመነከር የመሳሰሉ የጨለሙ ባሕርያት መያዝ እንደሆነ ይቆጥሩታል፤ ለእነርሱ እነዚህ እጅግ በጣም ከባድ ቅጣትና ስቃይ ናቸው።

“እንደዚሁም የሌላው ዓለም ዋጋዎች ፥ በሁሉም ቅዱሳት መጻሕፍት የተጠቀሱት ዘለዓለማዊ ሕይወት፥ መለኮታዊ ፍጹም ባሕርያት፥ ዘለዓለማዊ በረከቶችና ለዘለዓለም የማያልፍ ደስታ ናቸው። የሌላው ዓለም ሽልማቶች፥ ከዚህ ዓለም ከተለዩ በኋላ የሚገኙ ፍጹምነቶችና ሰላም ሲሆኑ፥ የዚህ ዓለም ሽልማቶች ደግሞ ለዘለዓለማዊ ሕይወት የሚሆኑ፥ በዚህ ዓለም የተደረሰባቸው እውነተኛ አንጸባራቂና ፍጹም ባሕርያት ናቸው፤ ምክንያቱም የሕያው እውነተኛ ዕድገት ማለት እነዚህ ናቸውና። ይህም ለአንድ ሰው ከእንጭጭነት ወደ ብስለት እንደመድረስና ‘ከፈጣሪዎች ሁሉ እጅግ በጣም የላቀው ፈጣፊ፥ እግዚአብሔር የተባረከ ይሁን’ የሚሉት ቃላት መገለጫ እንደመሆን ነው። የሚቀጥለው ዓለም ዋጋዎች ሰላም፥ መንፈሳዊ ጸጋዎች፥ በእግዚአብሔር መንግሥት ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ስጦታዎች፥ የልብና የነፍስን ፍላጎት ማግኘትና በዘለዓለማዊው ዓለም ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘት ናቸው። በዚሁ መንገድ የሚቀጥለው ዓለም ቅጣት፥ ይኸውም ማለት የሚቀጥለው ዓለም ስቃይ፥ ልዩ መለኮታዊ ቡራኬዎችንና ፍጹም የሆኑ በረከቶችን ማጣት፥ እጅግ በጣም ዝቅተኛ ደረጃ ላይ መውደቅን የሚያጠቃልል ነው። እነዚህን መለኮታዊ ስጦታዎች ያጣ፥ ከሞት በኋላ የሚቀጥል ቢሆንም፥ በእውነት ሰዎች ዘንድ ግን እንደሞተ ይቆጠራል።

“የሚቀጥለው ዓለም ብልጽግና ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ነው። በዚህ ምክንያት እነዚያ ወደ መለኮታዊ መንበር የቀረቡት እንደሚያማልዱ፦ ይህም ማማለድ በእግዚአብሔር የተፈቀደ እንደሆነ የተረጋገጠ ነው። የእነዚያ በኃጢአትና በአለማመን የሞቱት ሰዎች ሁኔታ እንኳ ሊለወጥ ይችላል፤ ይህም ማለት በእግዚአብሔር ፍርድ ሳይሆን በጸጋው ምሕረት ሊያገኙ ይችላሉ፤ ምክንያቱም ጸጋ ያለዋጋ መስጠት ሲሆን፥ ፍርድ ግን እንደ ሥራው መስጠት ነውና። ለእነዚህ ነፍሶች እዚህ ሆነን ለመጸለይ እንደምንችል ሁሉ፥ የኢግዚአብሔር መንግሥት በሆነው በሚቀጥለው ዓለምም ልንጸልይላቸው ይኸው ኃይል አለን። በዚያ ዓለም የሚገኙ ሰዎች ሁሉ የእግዚአብሔር ፍጡራን አይደሉምን? ስለዚህ በዚያም ዓለም ደግሞ ዕድገት ለማድረግ ይችላሉ። እዚህ በመማጸን ተግባራቸው ብርሃን እንደሚያገኙ ሁሉ፥ እዚያም ደግሞ ለይቅርታ ሊማጸኑ ይችላሉ፤ በመለመን፥ ልባዊ ጸሎት በማድረግና በመማጸን ብርሃን ሊቀበሉ ይችላሉ። እንዲሁም በዚህ ዓለም ያሉ ነፍሶች ፥ በቅዱሳን ልመናና ፀሎት አማካይነት እንደሚሻሻሉ ሁሉ፥ ከሞት በኋላም እንዲሁ ነው። ደግሞም በራሳቸው ፀሎትና መማፀን አማካይነት ፥ ከሁሉም በላይ የቅዱሳን ክስተቶች ማማለድ ተቀባዮች ከሆኑ፥ሊያድጉ ይችላሉ።

“ይህንን ቁሳዊ ቅርጽ ከመተዋችን በፊትም ሆነ ከተውነው በኋላ ወደ ፍጹምነት ዕድገት አለ፥ ነገር ግን የሁኔታ (የዓይነት) ዕድገት የለም። ስለዚህ የፍጡሮች ሁኔታ በፍጹም ሰው ደረጃ ላይ ሲደርስ ይፈጸማል። ከፍጹም ሰው በላይ ከፍተኛ የሆነ ሌላ ፍጡር የለም። ነገር ግን ሰው በዚህ ሁኔታ ላይ ከደረሰ በኋላም በፍጹምነት ረገድ ሊያድግ ይችላል፤ ነገር ግን በሁኔታ ሊያድግ አይችልም፥ ምክንያቱም ሰው ካለበት ሁኔታ ራሱን የሚያሸጋግርበት ከፍጹም ሰው የላቀ ሁኔታ የለምና። የሰው ፍጹምነቶች ማለቂያ የሌላቸው በመሆናቸው መሻሻል የሚችለው በሰብአዊ ፍጡርነት ሁኔታ ውስጥ ብቻ ነው። ስለዚህ አንድ ሰው ምንም ያህል የተማረ ቢሆን፥ ሌላ ከእርሱ በላይ የተማረ እንደሚኖር ለማሰብ እንችላለን። ስለዚህ የሰው ፍጹምነቶች ማለቂያ የሌላቸው እንደመሆናቸው መጠን፥ ሰው ከዚህ ዓለም ከተለየ በኋላም በፍጹምነት ረገድ ሊሻሻል ይችላል።” (ሳም ንሰርድ ኩዌስሽንስ፡ ገጽ235፡ አንቀጽ ከ6-7)

Interesting blog? Like it on Facebook, +1 on Google, Tweet it or share this article on other bookmarking websites.

አስተምሮቶች

  • ትምህርት ለሁሉም
  • ነፍስና ሥጋ
  • አምላክን መውደድ
  • አንድ ዓለም አቀፋዊ ቋንቋ
  • አጉል ጥላቻን ማስወገድ
  • እውነትን መመርመር
  • ከልክ ያለፈ ሀብትና ድህነትን ማስቀረት
  • ከሞት በኋላ ሕይወት
  • የሰው ዘር አንድነት
  • የሳይንስና ሐይማኖት ተደጋጋፊነት
  • የሴቶችና የወንዶች እኩልነት
  • የእርኩስ መንፈስ አለመኖር
  • ገነትና ሲኦል
  • Follow via Facebook
  • Follow via Youtube
unity

© 2023 የኢትዮጵያ ባሃኢዎች

Go Top