የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
  • የባሃኢ ትምህርቶች
    • አምላክና ሐይማኖቶች
    • የአምላክ መልእክተኞች
    • የባሃኢ ትምህርቶች
    • ህግጋቶችና ደንቦች
    • አስተዳደር
  • ማህበረሰባዊ ተሳትፎ
    • ማህበረሰብ ግንባታ
    • የወጣቶች እንቅስቃሴ
  • የባሃኢ ማህበረሰብ
    • የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
    • የአለም ዓቀፍ ማህበረሰብ
    • የባሃኢ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ - አዲስ አበባ ጽ / ቤት
    • ባሃኢዎችን እናስተዋውቃችሁ
  • የባሃኢ መጽሐፍት
    • ቅዱሳን ጽሑፎች
    • ሌሎች
  • ለበለጠ መረጃ
    • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች
    • መልእክት ይላኩልን
    • ቪዲዮዎች
  • ENGLISH

የሳይንስና ሐይማኖት ተደጋጋፊነት

ከባሃኦላህ መሠረታዊ ትምህርቶች አንዱ እውነተኛ ሳይንስና እውነተኛ ሃይማኖት ተደጋጋፊ መሆናቸውን ያስተምራል። እውነት አንድ ነው። ያለመግባባት የሚፈጠረው ከእውነት ሳይሆን በስህተት ምክንያት ነው። በሳይንስና በሃይማኖት ስም ከጥንት ጀምሮ ከባድ ግጭቶች ተደርገዋል። ይሁን እንጂ የነዚያን ግጭቶች ሁኔታ በእውነተኛ መንገድ ብንመረምር ምክንያቱ አለማወቅ፥ ከንቱ ጥላቻ፥ ግብዝነት፥ ስግብግብነት፥ ጠባብ አስተሳሰብ፥ የትዕግሥት ጉድለት፥ ሃሳበ ግትርነትና ወይም ከመሳሰሉት የተነሳ ሆኖ እናገኘዋለን። የሳይንስና የሃይማኖት መንፈስ አንድ ሆኖ እያለ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ባዕድ አስተሳሰቦች ግን ከሁለቱም መንፈስ የራቁ ናቸው። ሐክስሌይ እንደሚነግረን “የፈላስፎች ታላቅ ሥራዎች ፍሬ የተገኙ በእነርሱ አእምሮ ድካም ሳይሆን አእምሮቻቸውን ወደ ታላቅ መንፈሳዊ አስተሳሰብ በመምራታቸው ነው። በብልህነታቸው ሳይሆን በትዕግሥታቸውና በፍቅራቸው ራሳቸውን ረስተው በአንድ ልብ በመድከማቸው እውነት ልትገለጽላቸው ትችላለች።”

 

ቦል የተባለው የሂሳብ አዋቂ “የጂኦሜትሪ ጥናት ከጸሎት የሚቆጠር ነው፤ የተወሰነው አእምሮ ወሰን ከሌለው የተወሰነው ለማግኘት ብርሃንን ይሻል።” ታላላቅ የሃይማኖት ነቢያትና የሳይንስ ጠበብት እርስ በርሳቸው አይነቃቀፉም። አዲስ የሚመጣውን ነቢይ ሁልጊዜ የሚያሳድዱና ለሥልጣኔ ጠንቅ የሆኑ፥ ለነቢያት ትምህርት መንፈስ ሳይሆን ለቃላቶቹ የሚሰግዱ የነዚህ የታላላቅ ነቢያት ዋጋ-ቢስ ተከታዮች ናቸው። ቅዱስ ነው ብለው የያዙትን አንዱን የሃይማኖት ክፍል ብርሃን አጥንተው በተወሰነ አእምሮአቸው በጥንቃቄና በትክክል ዓይነቱን በመለየት ትርጉም ሰጥተውታል። ይህ ነው ለእነርሱ አንዱና እውነተኛው ብርሃን። እግዚአብሔር በማያልቀው ቸረነቱ ከሌላ ዘንድ የበለጠ ብርሃን ሲልክና የቅድስናም ብርሃን ከተለየ ፋና ያዥ አዲስ ብርሃንን ሲሰጥ በደስታ ተቀብሎ ለብርሃኖች ሁሉ አምላክ በመስገድ ፈንታ ሲቆጡና ሲሸበሩ ይታያሉ። ምክንያቱም ይህ አዲሱ ብርሃን ከአተረጓጎማቸው ጋር ስለማይመሳሰል ነው። እነርሱ ያሰቡትን መልክ ስለአልያዘ፤ እነርሱ ካሰቡትም ሥፍራ ስለአላበራ፥ ሰዎችን ያሳስታልና በምንም ሁኔታ መደምሰስ አለበት ይላሉ! ብዙዎች የነቢያት ተቃዋሚዎች እነዚህን ይመስላሉ። ዕውሮች፥ የዕውር መሪዎች፥ እነርሱ እውነት ነው ብለው የያዙትን ለመጠበቅ ሲሉ አዲስና የተሟላውን እውነት ይቃወማሉ። ሌሎች ደግሞ ከነዚህ ያነሱ ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ እውነትን የሚቃወሙ ወይንም በመንፈስ የሞቱ እውነት እንዳይሰለጥን እንቅፋት የሚሆኑ ናቸው።

Interesting blog? Like it on Facebook, +1 on Google, Tweet it or share this article on other bookmarking websites.

አስተምሮቶች

  • ትምህርት ለሁሉም
  • ነፍስና ሥጋ
  • አምላክን መውደድ
  • አንድ ዓለም አቀፋዊ ቋንቋ
  • አጉል ጥላቻን ማስወገድ
  • እውነትን መመርመር
  • ከልክ ያለፈ ሀብትና ድህነትን ማስቀረት
  • ከሞት በኋላ ሕይወት
  • የሰው ዘር አንድነት
  • የሳይንስና ሐይማኖት ተደጋጋፊነት
  • የሴቶችና የወንዶች እኩልነት
  • የእርኩስ መንፈስ አለመኖር
  • ገነትና ሲኦል
  • Follow via Facebook
  • Follow via Youtube
unity

© 2023 የኢትዮጵያ ባሃኢዎች

Go Top