የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
  • የባሃኢ ትምህርቶች
    • አምላክና ሐይማኖቶች
    • የአምላክ መልእክተኞች
    • የባሃኢ ትምህርቶች
    • ህግጋቶችና ደንቦች
    • አስተዳደር
  • ማህበረሰባዊ ተሳትፎ
    • ማህበረሰብ ግንባታ
    • የወጣቶች እንቅስቃሴ
  • የባሃኢ ማህበረሰብ
    • የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
    • የአለም ዓቀፍ ማህበረሰብ
    • የባሃኢ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ - አዲስ አበባ ጽ / ቤት
    • ባሃኢዎችን እናስተዋውቃችሁ
  • የባሃኢ መጽሐፍት
    • ቅዱሳን ጽሑፎች
    • ሌሎች
  • ለበለጠ መረጃ
    • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች
    • መልእክት ይላኩልን
    • ቪዲዮዎች
  • ENGLISH

አንድ ዓለም አቀፋዊ ቋንቋ

ለጦርነት መነሾ የሆኑትን ዋና ዋናዎቹን ምክንያቶችና እነርሱንም ለማስወገድ እንዴት እንደሚቻል ከተመለከትን ዘንዳ እጅግ ታላቁን ሰላም ለመመሥረት እንዲቻል በባሃኦላህ የቀረቡትን አንዳንድ መሠረታዊ ሃሣቦች እንመርምር።

የመጀመሪይው ሃሳብ አንድ የዓለም ረዳት ቋንቋ እንዲመሠረት ነው። ባሃኦላህ ‘መጽሐፈ አቅዳስ’ በተባለው መጽሐፉና በብዙ መልእክቶቹ ስለዚህ ጉዳይ ይጠቅሳል። በዚህም መሠረት ‘ታብሌት ኦፍ ኢሽራቃት’ በተባለው መልእክቱ እንዲህ ይላል፦

“ከጥንት ጀምሮ የዓለም ክፍሎች በሙሉ በመለኮታዊ አንድነት ብርሃን በርተዋል። የዚህም አንድነት መስፋፊያ ትልቁ መንገድ የዓለም ሕዝቦች መግባብያ የሆኑትን ቋንቋና ጽሑፎችን መረዳት ነው። ዓለም እንደ አንድ አገርና እንደ አንድ ቤተሰብ ትሆን ዘንድ አሁን ካሉት ቋንቋዎች አንድ እንዲመርጡ ወይንም ሌላ አዲስ ቋንቋ እንዲፈጥሩ፤ እንደዚሁም የወል በሆነ ጽሑፍ እንዲጠቀሙና እነዚህንም በመላው ዓለም ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች እንዲያስተምሩ ከዚህ በፊት በመልእክቶቻችን የቤተ ፍትሕን ባለአደራዎች አዘናቸዋል።

ይህ ሃሣብ ለመጀመሪያ ጊዜ በባሃኦላህ ለዓለም በተሰጠበት ወቅት በሥራ ላይ የሚውልበትን መንገድ ለማግኘት የታደለ ሉዶቪክ ዛመኖፍ የተባለ አንድ ሕፃን በፖላንድ አገር ተወለደ። ከሕፃንነቱ ጀምሮ አንድ የዓለም ቋንቋ አስፈላጊነት የዛመኖፍ ዋናው የሕይወቱ ዓላማ ነበር። የጥረቱም ውጤት ኤስፐራንቶ የተባለውን ቋንቋ ለመፈልሰፍ ሲያስችለው፥ ይህም ቋንቋ ከብዙ ዓመታት በላይ ሙከራ ላይ ከዋለ በኋላ ለዓለም አቀፍ የቋንቋ ግንኙነት በቂ ግልጋሎት ለመስጠት የሚችል መሆኑ ተረጋግጧል። እንደ እንግሊዝኛ፥ ፈረንሳይኛ ወይንም ጀርመንኛ ያሉትን ቋንቋዎች ለማጥናት ከሚያስፈልገው ጊዜ በአንድ ሃያኛው ለመጠናት ስለሚቻል ይህ ቋንቋ ታላቅ ጥቅም አለው

እ.ኤ.አ. በየካቲት ወር 1913 ዓ.ም. በፓሪስ ውስጥ በተደረገው በአንድ የኤስፐራንቶ ማኅበር ግብዣ ላይ አብዱል-ባሃ እንዲህ አለ፦
“በአሁኑ ጊዜ በአውሮፓ ውስጥ አለመግባባትን ከፈጠሩት ምክንያቶች አንዱ የቋንቋዎች መለያየት ነው። ይህ ሰው ጀርመናዊ ነው፥ ሌላው ደግሞ ኢጣልያዊ ነው እንላለን። እንዲሁም አንድ እንግሊዛዊና አንድ ፈረንሳዊ እናገኛለን። ዘራቸው አንድ ቢሆንም ቅሉ በመሐከላቸው ያለው ታላቁ መሰናክል ቋንቋ ነው። አንድ ዓለም አቀፍ የሆነ ረዳት ቋንቋ በሥራ ላይ ውሎ ቢሆን ኖሮ ሁሉም እንደ አንድ ይቆጠሩ ነበር።

“ከዛሬ አርባ ዓመት በፊት ባሃኦላህ ስለዓለም አቀፍ ቋንቋ አስፈላጊነት ጽፏል። ዓለም አቀፍ ቋንቋ ተቀባይነት እስኪያገኝ ድረስ በዓለም ክፍሎች መካከል ፍጹም አንድነት ይገኛል ብሎ ለማመን ያዳግታል። ምክንያቱም አለመግባባት ሰዎች እርስ በርሳቸው እንዳይቀራረቡ ያደርጋቸዋል። ይህም አለመግባባት አንድ ረዳት ዓለም አቀፍ ቋንቋ ካልተገኘ በስተቀር ሊወገድ አይችልም

“በአጠቃላይ አነጋገር የምሥራቅ ሕዝብ በሙሉ በምዕራባውያን ዘንድ ስለሚደረጉት ነገሮች አጣርተው አያውቁም። ምዕራባውያንም እንዲሁ ለምሥራቃዊያን ቅን አስተያየት የላቸውም። አስተያየታቸው በሳጥን ውስጥ ተቆልፏል፤ የሳጥኑም መክፈቻ ዓለም አቀፍ ቋንቋ ነው። ዓለም አቀፍ ቋንቋ ቢኖረን ኖሮ የምዕራባውያን መጻሕፍት በቀላሉ ወደዚህ ቋንቋ ሊተረጎሙ ስለሚችሉ ምሥራቃውያን ሊጠቀሙባቸው ይችሉ ነበር። በተመሳሳይ ምዕራባዊያን ይገለገሉባቸው ዘንድ የምሥራቃዊያን መጻሕፍት ወደዚሁ ቋንቃ በቀላሉ ሊተረጎሙ ይችሉ ነበር። የምዕራብንና የምሥራቅን አንድነት ለማስገኘት የሚያስችለው ታላቁ መንገድ አንድ የወል ቋንቋ ነው። ዓለምን በሞላ እንደ አንድ ቤተሰብ ያደርገዋል። ለሰው ልጅም መሻሻል ጠንካራ ኃይል ይሆናል። የሰውን ልጅ የአንድነት ዓላማ ከፍ ያደርገዋል። ምድርን በሞላ አንድ ዓለም አቀፋዊ የጋራ ብልጽግና ድርጅት ያደርገዋል። በሰው ልጆች መከል የፍቅር ምክንያት ይሆናል። በልዩ ልዩ ነገዶችም መሐከል ወዳጅነትን ያስገኛል።

“ለእግዚአብሔር ምስጋና ይድረሰውና ዶክቶር ዛማንሆፍ የኤስፕራንቶን ቋንቋ ፈልስፏል። ለዓለም አቀፍ መገናኛ ለመሆን የሚያስችለውን መንገድ ሁሉ ይዟል። በዚህ ዓይነት መንገድ ወገኖቹን የሰውን ልጆች በማገልገሉ ሁላችንም ለዚህ ከፍተኛ ሥራው ልናመሰግነው ይገባናል። ተከታዮቹ ያለድካምና ያለ መሰልቸት ከሠሩ ኤስፔራንቶ ዓለም አቀፍ ቋንቋ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ በየእለቱ በሰፊው እንዲታወቅ በየአገሩ በየመንግሥታቱ ዘንድ ተቀባይነትን እንዲያገኝ በየትምህርት ቤቶችም የሥርዓተ ትምህርቱ አካል ሆኖ እንዲሰጥ ሁላችንም ማጥናትና ማስፋፋት አለብን። ሰዎች አንድ ብሔራዊ፥አንድ ሌላ ዓለም አቀፍ ቋንቋ ብቻ እንዲኖራቸውና ለወደፊቱም በዓለም አቀፍ ስብሰባዎችና ጉባኤዎች ላይ ኤስፔራንቶ እንደሚሠራበት ተስፋ አደርጋለሁ። ይህም ሲሆን በዓለም ሕዝቦች መሐከል ፍጹም አንድነት ይመሠረታል። በአሁኑ ጊዜ ከልዩ ልዩ አገር ሕዝቦች ጋር ለመግባባት እንዴት አስቸጋሪ እንደሆነ አስቡ። አንድ ሰው ሃምሳ ቋንቋ ቢያጠናና ወደ አንድ አገር ቢሄድእንኳ የዚያን አገር ቋንቋ ላያውቅ ይችላል። ስለዚህ ይህ የኤስፔራንቶ ቋንቋ እንዲስፋፋ ከፍተኛ ጥረት እንደምታደርጉ ተስፋ አደርጋለሁ።”
እነዚህ ስለኤስፔራንቶ የተነገሩት ቃላት የተወሰኑና የሚያበረታቱ ቢሆኑም በባሃኦላህ ትዕዛዝ መሠረት የዓለም አቀፍ ቤተ ፍትሕ አንድ ውሳኔ እስከሚሰጥበት ድረስ የባሃኢ ሃይማኖት ኤስፔራንቶንም ሆነ ሌላ አሁን የሚሠራበትን ወይንም አዲስ የሚፈለሰፍ ቋንቋ ለመቀበል ግዴታ የለበትም።

አብዱል-ባሃ እራሱ እንዲህ ብሏል፦
“በኤስፐራንቶ ላይ የዋለው ፍቅርና ጥረት እንዳለ ሆኖ፤ አንድ ሰው ብቻውን አንድ ዓለም አቀፍ ቋንቋ ለመፍጠር አይችልም።” ( አብዱል-ባሃ ኢን ሎንደን ገጽ 9

የትኛው ቋንቋ እንደሚመረጥ ወይም የተመረጠው ቋንቋ ተፈጥሮአዊ ወይም ካሉት የተቀነባበረ እንዲሆን የዓለም ሕዝቦች የሚወስኑት ይሆናል።

Interesting blog? Like it on Facebook, +1 on Google, Tweet it or share this article on other bookmarking websites.

አስተምሮቶች

  • ትምህርት ለሁሉም
  • ነፍስና ሥጋ
  • አምላክን መውደድ
  • አንድ ዓለም አቀፋዊ ቋንቋ
  • አጉል ጥላቻን ማስወገድ
  • እውነትን መመርመር
  • ከልክ ያለፈ ሀብትና ድህነትን ማስቀረት
  • ከሞት በኋላ ሕይወት
  • የሰው ዘር አንድነት
  • የሳይንስና ሐይማኖት ተደጋጋፊነት
  • የሴቶችና የወንዶች እኩልነት
  • የእርኩስ መንፈስ አለመኖር
  • ገነትና ሲኦል
  • Follow via Facebook
  • Follow via Youtube
unity

© 2023 የኢትዮጵያ ባሃኢዎች

Go Top