የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
  • የባሃኢ ትምህርቶች
    • አምላክና ሐይማኖቶች
    • የአምላክ መልእክተኞች
    • የባሃኢ ትምህርቶች
    • ህግጋቶችና ደንቦች
    • አስተዳደር
  • ማህበረሰባዊ ተሳትፎ
    • ማህበረሰብ ግንባታ
    • የወጣቶች እንቅስቃሴ
  • የባሃኢ ማህበረሰብ
    • የኢትዮጵያ ባሃኢዎች
    • የአለም ዓቀፍ ማህበረሰብ
    • የባሃኢ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ - አዲስ አበባ ጽ / ቤት
    • ባሃኢዎችን እናስተዋውቃችሁ
  • የባሃኢ መጽሐፍት
    • ቅዱሳን ጽሑፎች
    • ሌሎች
  • ለበለጠ መረጃ
    • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች
    • መልእክት ይላኩልን
    • ቪዲዮዎች
  • ENGLISH

እውነትን መመርመር

እውነትን በምንሻበት ጊዜ ፍለጋችን ከሳይንስ ጋር የተዛመደ መሆን እንዳለበት የባሃኢ ትምህርቶች ያስረዱናል። አንድ ሰው ሳይሰናከል እውነትን ይፈልግ ዘንድ ከማናቸውም ከንቱ ጥላቻ እራሱን ማላቀቅ አለበት።

አብዱል-ባሃ እንዲህ ይላል፦
“እውነትን ለማግኘት ስንሻ ከከንቱ ጥላቻችንና ከጥቃቅን እምነቶቻችን ተላቀን ነፃ የሆነ አእምሮ እንዲኖረን ይገባል። ጽዋችን በግል ፍላጎት ከተሞላ ለሕይወት ውሃ ምንም ሥፍራ አይኖረውም። እኛ እራሳችን ትክክለኞች ሌሎች ሁሉ የተሳሳቱ አድርገን ማሰባችን ብቻ ለአንድነት ጎዳና ትልቁ እንቅፋት ነው፥ ወደ እውነት ከደረስን አንድነት አስፈላጊ ነው፥ እውነት አንድ ስለሆነ።

“ማንኛውም እውነት ሌላውን እውነት አይቃረንም። ብርሃን በማንኛውም ምቅረዝ ቢበራ ጥሩ ነው! ጽጌረዳ በማንኛውም ሥፍራ ብትፈካ ታምራለች! ኮከብ ከምሥራቅም ሆነ ከምዕራብ ብትወጣ የምትሰጠው ብርሃን ያው አንድ ዓይነት ነው! ከከንቱ ጥላቻ ነጻ ሁኑ፤ የእውነት ፀሐይ ከየትኛውም አድማስ ቢዘልቅ ትወዱት ዘንድ፤ የእውነት መለኮታዊ ብርሃን በክርስቶስ ላይ ሲያበራ ካያችሁ በሙሴና በቡድሃም ላይ መብራቱን ለመገንዘብ ትችላላችሁ። እውነትን መፈለግ ማለት ይህ ነው።

“ደግሞም ከዚህ በፊት የተማርነውንና ማናቸውንም በእውነት ጎዳና ላይ እንቅፋት ሊሆን የሚችለውን ነገር ሁሉ ለማስወገድ ፈቃደኛ መሆን ማለትም ነው፤ ቢያስፈልግም ትምህርቱን እንደገና አንድ ብለን ከመጀመር ወደኋላ ማለት የለብንም። ስለአንድ ሃይማኖት ወይንም ስለአንድ ሰው ያለን ፍቅር ዓይናችንን በመጋረድ የከንቱ እምነት እሥረኞች እንዳያደርገን ያስፈልጋል። ከነዚህ ሁሉ ችግሮች ስንላቀቅና በነፃ አእምሮ ስንሻ የዚያን ጊዜ ወደግባችን ለመድረስ እንችላለን።” (ዊዝደም ኦፍ አብዱል-ባሃ ገጽ 127)

 

እውነትን መሻት

ባሃኦላህ ተከታዮቹን ፍትህን አጥብቀው እንዲይዙ ሲያዝ እንደሚከተለው ያስረዳል፦
“የእግዚአብሔርን ክስተቶች ሁሉ በእኩልነት ለማየትና ሁሉንም ነገሮች በብሩህ ሕሊና ለማመዛዘን የሰው ልጅ ከከንቱ እምነትና በጭፍን ከመከትል ነፃ መሆን አለበት።” (ዎርድስ ኦፍ ዊዝደም)

እያንዳንዱ ሰው የእግዚአብሔር ጸጋ በባሃኦላህ ሰብዓዊ አካል መከሰቱን ማየትና መገንዘብ ይኖርበታል። ይህንን ካልተገነዘብን ግን የባሃኢ እምነት ለማንም ትርጉም የሌለው ባዶ ስም ነው። ነብያት ሁልጊዜ ሰውን አጥብቀው የሚያስተምሩት ሰው ዓይኑን እንዲከፍት እንጂ እንዲጨፍርን፥ ማመዛዘኛውን እንዲጠቀምበት እንጂ እንዳይጨቁኑት ነው። የከንቱ ጥላቻን ደመና ለመግፈፍና በጭፍን የመከተልን ሰንሰለት በመበጣጠስ የአዲስ እምነትን እውነታ ለመቀበል የሚያስችላቸው ግልጽ አመለካከትና ነፃ አስተሳሰብ እንጂ በግድ ማሳመን አይደለም።

እርሱ ባሃኢ የሚሆን የማይፈራና እውነትን ፈላጊ መሆን አለበት፥ ግን ፍለጋውን በቁስ ዓለም ብቻ መወሰን የለበትም። መንፈሳዊ የማስተዋል ኃይልና የሥጋዊ ንቃት ሊኖረው ይገባል። እውነትን ያለ ተገቢና በቂ ምክንያት ላለመቀበል እግዚአብሔር የሰጠውን ህዋሳት ሁሉ መጠቀም ያስፈልጋል። ልቡ ንጹህ፥ አእምሮው ከከንቱ ጥላቻ የነጻ፥ ቅን ተመራማሪ የእግዚአብሔር ጸጋ በማንም አካል ቢገለጥ ለመቀበል አያዳግተውም። ባሃኦላህ በተጨማሪ እንዲህ ይላል፦
“ሰው እራሱን ማወቅ አለበት፥ እንዲሁም ወደ ከፍተኝነት ወይንም ወደዝቅተኝነት፥ ወደ ሃፍረት ወይም ወደ ክብር፥ ወደ ሀብት ወይም ወደ ድኅነት የሚመሩትን ነገሮች ማመዛዘን አለበት።” (ታብሌት ኦፍ ታራዛት)

“የእግዚአብሔር ስሙ ይቀደስ! የትምህርት ሁሉ ምንጭ እግዚአብሔርን ማወቅ ነው። ይህም ሊደረስበት የሚችለው በእርሱ መለኮታዊ ክስተቶች በኩል ነው።” (ወርድስ ኦፍ ዊዝደም)

የእግዚአብሔር ክስተት ፍጹም ሰው፥ ታላቅ የሰው ልጅ አርአያና የሰብዓዊነት ተክል የመጀመሪያ ፍሬ ነው። ክስተትን እስክናውቀው ድረስ በውስጣችን ያለውን ድብቅ ኃይል ልንገነዘብ አንችልም። ክርስቶስ የመስክ አበቦች እንዴት እንደሚያድጉ እንድናስብ ሲያስታውሰን ሰሎሞን በዚያ ሁሉ ክብሩ ከእነርሱ እንደ አንዷ እንኳ እንዳልፈካ ይነግረናል። የመስክ አበባ ከአንድ ውብት አልባ እምቡጥ ውስጥ ታድጋለች። የመስክ አበባ ፈንድታ ተወዳዳሪ የሌለውን አበባዋንና ግርማ ሞገስዋን ተጎናጽፋ ካላየን በዚያች ውበት አልባ እምቡጥ ውስጥ ያለውን እውነት እንዴት ልናውቅ እንችላለን? ያንን እምቡጥ ለመመርመር ልንቆራርጠው፥ ልንከፋፍለው በጥንቃቄም በረቀቀ ሁኔታ ልንመረምረው ብንችልም ያንን በውስጡ የተደበቀ ውበት ለመቀስቀስ የሚችል አትክልተኛው ብቻ ሆኖ እናገኘዋለን። በተመሳሳይ ሁኔታ የእግዚአብሔርን ጸጋ በክስተቱ ላይ እንደተገለጸ ካላስተዋልን በእራሳችን ተፈጥሮና በመሰሎቻችን ውስጥ ስለአለው ድብቅ መንፈሳዊ ውበት ምንም ዓይነት ግምት ሊኖረን አይችልም። የእግዚአብሔርን ክስተት በማወቅና በመውደድ ትምህርቱንም በመከተል ቀስ በቀስ በውስጣችን ያለውን ድብቅ ፍፁምነት ልንገነዘበው እንችላለን። የዚያን ጊዜ ነው የሕይወት ትርጉምና ዓላማ፥ የሁለንተን ዓለምም ሚስጢር ግልጽ የሚሆንልን። እስከዚያ ድረስ ግን አይደለም።

Interesting blog? Like it on Facebook, +1 on Google, Tweet it or share this article on other bookmarking websites.

አስተምሮቶች

  • ትምህርት ለሁሉም
  • ነፍስና ሥጋ
  • አምላክን መውደድ
  • አንድ ዓለም አቀፋዊ ቋንቋ
  • አጉል ጥላቻን ማስወገድ
  • እውነትን መመርመር
  • ከልክ ያለፈ ሀብትና ድህነትን ማስቀረት
  • ከሞት በኋላ ሕይወት
  • የሰው ዘር አንድነት
  • የሳይንስና ሐይማኖት ተደጋጋፊነት
  • የሴቶችና የወንዶች እኩልነት
  • የእርኩስ መንፈስ አለመኖር
  • ገነትና ሲኦል
  • Follow via Facebook
  • Follow via Youtube
unity

© 2023 የኢትዮጵያ ባሃኢዎች

Go Top